About Us Financial Service Publication Branches News Forms Contact Us Articles FAQ
 

Side Menu



Proposal Forms
-----------------------
Proposal With Medical Certificate
Proposal Without  Medical Certificate
Proposal for Medical Insurance 

Claim Forms 
------------------------
Medical Claim Notification
Accident and Disease Notification
Medical Attendance Certificate
Death Confirmation Form

 
የባንክ ቀሪ ዕዳ ማወራረጃ የሕይወት ዋስትና

 

የባንክ ቀሪ ዕዳ ማወራረጃ የሕይወት ዋስትና ከባንክ ገንዘብ ተበድረው የመኖሪያ ቤት ለሚሰሩ የሚሰጥ ሲሆን ዋስትና የተገባለት ቤት ባለቤት ከባንክ የተበደሩትን ዕዳ አጠናቀው ሳይከፍሉ ከዚህ ዓለም በሞት በሚለዩበት ወቅት ቤተሰብ ዕዳ በመክፈል ወይም ቤቱ ተሸጦ ለዕዳ ተከፋይ እንዳይሆን ቤተሰብና ልጆች ያለመጠጊያ እንዳይቀሩ የሚያደርግ መጠለያ የሚሰጥ ዋስትና ነው፡፡
የባንክ ቀሪ ዕዳ ማወራረጃ የሕይወት ዋስትና አንድ ተበዳሪ ከባንኩ ለሚበደረው ገንዘብ ለሕይወት ዋስትና የሚገባ ሲሆን የባንኩ ተበዳሪ ወይም ተበዳሪዎች ለባንኩ መክፈል የሚገባቸውን የብድር ገንዘብ ከፍለው ከማጠናቀቃቸው በፊት ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በብድሩ ውል መሠረት ቀሪ ዕዳውን የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ሟችን በመተካት ለባንኩ ክፍያውን ይፈፅማል፡፡

የባንክ ቀሪ ዕዳ ማወራረጃ ዋስትና ተጠቃሚ ለመሆን፡-
1. ተበዳሪው የመድን መግቢያ ማመልከቻ ቅፅ መሙላት፣
2. በብድሩ መጠን ላይ በመመስረት አስፈላጊ ሲሆን በድርጅቱ ክሊኒክ ወይም ከአዲስ አበባ ውጪ ከሆነ ከግል ክሊኒክ ወይም ሆስፒታል የጤና ምርመራ ማቅረብ፣
3. ለዋስትናው የሚከፈለውን የረጅም ጊዜ አረቦን በአንድ ጊዜ መክፈል ያስፈልጋል፡፡
ይህን የባንክ ቀሪ ዕዳ ማወራረጃ የሕይወት ዋስትና በጣምራ ከባለቤት ጋር ባልና ሚስት በመሆን ለመግዛት ይቻላል፡፡ ቀሪው ዕዳ ከመጠናቀቁ በፊት ከሁለት አንዳቸው ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ ቀሪውን ዕዳ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ለባንክ ይከፍላል፡፡












   

Home  About Us Financial Indicator Life Insurance Non-Life Insurance Main Branch Forms Contact Us