አጠቃላይ መግለጫ፤
የትላልቅ ቡድን የሕይወት ዋስትና ቢያንስ 200 አባላትን ያቀፈ ቡድን ሊጠቀምበት የሚችል የዋስትና ዓይነት ነው፡፡
ይህ የሕይወት መድን ውል ለተፈጥሮ ሞት ብቻ ወይም ከአደጋ ለመነጨ ሞት ጭምር ሊሆን ይችላል፡፡ ቅንጅቱን መራጩ ተጠቃሚው ቢሆንም ለተፈጥሮ ሞት ብቻ ሲባልና በአደጋ ለመነጨ ሞት ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ግልጽ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ለተፈጥር ሞት ብቻ ማለት ሀ. አደጋ ቢደርስ በአደጋው ምክንያት ለሚደርስ ጉዳት ክፍያ አይፈፀምም፡፡ ለ. አደጋው ሞት ከአስከተለ በውሉ መሠረት ለሕጋዊ ወራሾች የዋስትናው ገንዘብ ክፍያ የሚፈፀምበት፣ ሐ. ሞት የተከሰተው ክፍያ አይፈፀምባቸውም ተብለው ከተጠቀሱት የሞት ዓይነቶች ካልሆነ በስተቀር ካሣ የሚፈፀምበት ማለት ነው፡፡
በአደጋ የመነጨ ሞት ማለት ከተፈጥሮ ሞት በተጨማሪ በአደጋ ሳቢያ ለሚመጣ ሞት ወይም የአካል መጉደል ተጨማሪ ወይም ሌላ የካሣ ክፍያ የሚደረግበት ዋስትና ዓይነት ማለት ነው፡፡ ለሞት ብቻ ዋስትና የገዙ፣ በአደጋ ቢሞቱ የሞት ካሣ በውሉ መሠረት ሲከፈላቸው፣ የሞትና የአደጋ ዋስትና የገዙ እንዲሁ በአደጋ ምክንያት ቢሞቱ ለሞቱ አንድ ክፍያ አሟሟቱ በአደጋ በመሆኑ ለአደጋው ሌላ ተጨማሪ ክፍያ ይደረግላቸዋል ማለት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር የአደጋ ዋስትና መጨመሩ ተጨማሪ የካሣ ክፍያ ያስገኛል ማለት ነው፡፡ ይህም ስለተባለ በትላልቅ ቡድን መድን ላይ ለአደጋ ተጨማሪ አረቦን አይጠየቅም፡፡ ለምሣሌ ከላይ በተጠቀሰው የትላልቅ ቡድን የሕይወት ዋስትና ውል ዓይነት በየወሩ አንድ ብር ከሠላሣ ሣንቲም መክፈል የሚችሉ የቡድን አባላት የሚከተለውን ዓይነት የካሣ ክፍያ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡
ለተፈጥሮ ሞት ብቻ የተገዛ ውል ከሆነ ሞት ካልደረሰ በቀር በአካል መጉደል የካሣ ክፍያ አያስገኝም፣ ለመሞቱ ግን የአንድ ብር ከሠላሣ ሣንቲም ወርሃዊ አረቦን የሚያስገኘውን ብር 625 ይከፈላል፡፡
የተገዛው ውል ለተፈጥሮ ሞት ብቻ ሳይሆን ከአደጋ ለመነጨ ሞት ጭምር ከሆነና የሚከፈለው አረቦን በየወሩ አንድ ብር ከሠላሣ ሣንቲም ከሆነ የሚከተለው የካሣ ክፍያ ይደረጋል፡፡
• ሞት• ብር 450 የዋስትናውን ሙሉ ገንዘብ • የሁለት እግሮች ወይም የሁለት እጆች መቆረጥ ብር 450 የዋስትናውን ሙሉ ገንዘብ • የሁለት የዓይኖች መጥፋት ብር 450 የዋስትናውን ሙሉ ገንዘብ • የአንድ እግርና የአንድ እጅ መታጣት ብር 450 የዋስትናውን ሙሉ ገንዘብ • የአንድ እጅና የአንድ ዓይን መታጣት ብር 450 የዋስትናውን ሙሉ ገንዘብ • የአንድ የአካል ክፍል ብቻ መታጣት ማለት አንድ ዓይን ወይም አንድ እጅ ወይም እግር መታጣት ብር 225 ዋስትናውን ግማሽ ገንዘብ
ሆኖም ከሁለት አካል በላይ ቢታጣ ክፍያው መጠን ከዋስትናው ገንዘብ ብር 450 ምሳሌውን በተመለከተ ሊበልጥ አይችልም፡፡
የዋስትናው መጠን በየወሩ በአንድ ብር ከሠላሣ ሣንቲም ሂሣብ ተሠራ እንጂ የአረቦኑ ገንዘብ ከጨመረ የዋስትናውም ገንዘብ በዘያው መጠን እያደገ ይሄዳል፡፡
በየወሩ ሁለት ብር ከስድሣ ሣንቲም በነፍስ ወከፍ የሚከፍል ቡድን የዋስትናው ገንዘብ እላይ ከተጠቀሰው እጥፍ ይሆናል ማለት ነው፡፡ የዋስትናው ጣሪያ የሚወሰነው በዋስትና ፈላጊው የመክፈል አቅም ቢሆንም ከብር 50‚000 በላይ ከሆነ ለውል አሠራሩ የሐኪም ምርመራ ያስፈልጋል፡፡
የአረቦኑ አከፋፈል በየወሩ ብር አንድ ከሠላሣ ሣንቲም ወይም ብር ሁለት ከስልሣ ሣንቲም ወይም ከዚያ በላይ ከሆነ የዋስትናው ገንዘብ ለሕይወት ሞት ብቻ ወይም ለሕይወት ሞት እና አደጋ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
|
|
የዋስትናው ዓይነትና የካሣው መጠን |
|
የወር አረቦን |
ለሕይወት/ ሞት/ ብቻ |
ለሕይወትና ለአደጋ |
|
በሕመም |
በአደጋ |
|
ብር 1.3ዐ |
ብር 625 |
ብር 450 |
ብር 900 |
|
ብር 2.6ዐ |
ብር 1250 |
ብር 900 |
ብር 1800 |
|
ብር 3.9ዐ |
ብር 1875 |
ብር 1350 |
ብር 2700 |
|
ብር 5.2ዐ |
ብር 2500 |
ብር 1800 |
ብር 3600 |
|
|
|
|
|
የአረቦን አከፋፈሉ በየወሩ አንድ ብር ከሰላሣ ሣንቲም መሆኑ ቀርቶ ለደመወዝተኞች በተለይ በየወሩ የደመወዛቸውን መቶኛ ከሆነ የሚከተለውን የካሣ ክፍያ ማግኘት ይቻላል፡፡ አሁንም ቢሆን የዋስትና አመራረጡ ለሞት ብቻ ወይም ለሞትና ለአደጋ መሆኑ ልዩነት ያመጣልና አመራረጡ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ጠቃሚ ነው፡፡
በየወሩ የደመወዝ መቶኛ ማለት 1%' 2%' 3%) ወዘተ ማለት ነው፡፡
|
|
የዋስትና መጠን |
|
የወር ክፍያ ከደመወዝ የሚቆረጠው u% |
ለሕይወት መድን ወይም ለሞት ብቻ |
ለሕይወትና ለአደጋ ሞት |
|
በሕመም |
በአደጋ |
|
1.3ዐ% |
የ6 ወር ደመወዝ |
¾4½ወር ደመወዝ |
የ9 ወር ደመወዝ |
|
2.6ዐ% |
የ12 ወር ደመወዝ |
የ9 ወር ደመወዝ |
የ18 ወር ደመወዝ |
|
3.9ዐ% |
የ18 ወር ደመወዝ |
¾13½ ወር ደመወዝ |
የ27 ወር ደመወዝ |
|
5.2ዐ% |
የ24 ወር ደመወዝ |
የ18 ወር ደመወዝ |
የ36 ወር ደመወዝ |
የውሉ ልዩነት
ለትላልቅ ቡድኖች አገልግሎቶች እንዲውል የተደረገው ውል ከቀድሞው መደበኛ የቡድን የሕይወት መድን ውል ያለው ልዩነት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
o የዚህ ውል የአረቦኑ ክፍያ የአያሌ ደንበኞችን የመክፈል አቅም በእጅጉ ያገናዘበ በመሆኑ በአብዛኛው ሠርተው ገቢ የሚያገኙ ሁሉ በሥራ ወይም በሙያ ማህበር የተደራጁ አባላት የሚጠቀሙበት ዓይነተኛ የቡድን የሕይወት መድን ነው፡፡ o በዚህ የቡድን ውል ለመጠቀም የአባላት ምርጫ ያልተዘበራረቀ ወይም ከፍና ዝቅ የማይል አንድ ዓይነት ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡ ይህም ማለት ለምሳሌ በአንድ ቡድን ውስጥ የተወሰኑ አባላት በወር የተወሰነ የአረቦን መጠን፣ ሌሎች የተለየ የአረቦን መጠን ወይም ከዚያ በላይ በመክፈል ዋስትናውን ለመግዛት አይችሉም፡፡
የአባላቱ ብዛት እንደውሉ አገዛዝ ይለያያል፡፡ አባላቱ ራሳቸው የአረቦን ክፍያውን የማያዋጡ ከሆነ ብዛታቸው ከ250 ማነስ የለበትም፡፡ በአባላቱ መዋጮ የሚገዛ ከሆነ ቁጥራቸው 2ዐዐ ቢሆንም ይቻላል፡፡ ከአባላቱ ውስጥ ያለመዋጮ 100% የሆኑት ወይም በመዋጮ ከሆነ 80% የሆኑት እንኳን ፈቃደኛ ቢሆኑ ውሉን መግዛት ይችላሉ፡፡ ዋስትናውን ለመግዛት የጤና ምርመራ አያስፈልግም፡፡
ከላይ እንደተጠቀሰው የጤና ምርመራ የሚያስፈልገው የዋስትና መጠን ከብር 50‚000 የበለጠ እንደሆነ ነው፡፡ እንደመደበኛው የቡድን ሕይወት መድን አባላቱ የመድን መጠየቂያ ቅጽ እንዲሞሉ አይጠየቁም፡፡
ዕድሜአቸው እስከ 65 ዓመት የሆኑት የቡድን አባላት በሙሉ በዋስትናው ይታቀፋሉ፡፡ በመደበኛው የቡድን የሕይወት መድን ካሣ የማይከፈልባቸው ግን የትላልቅ ቡድኖች የሕይወት ዋስትና ሽፋን የሚሰጥባቸው ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡ o የሚሞላ መጠይቅ ባለመኖሩ በእድሜ ልዩነት የሚቀነስ ገንዘብ አይኖርም፡፡ o የጤና ሁኔታን በሚመለከት ጥያቄ ስለማይቀርብ በጤንነት ምክንያት ካሣ አይከለከልም፡፡ o እራስን በራስ በማጥፋት ካሣ አይከለከልም፡፡ o ውሉ ሲገዛ በነበሩበት ድርጅት ውስጥ እስካሉ ድረስ የሥራ ለውጥ ቢደረግም ከቡድን አባልነቱ እስካልወጡ ካሣ ይከፈላል፡፡ o በተለየ አውሮፕላን ማለት በመደበኛ የትራንስፖርት አገልግሎት በታወቀ ፕሮግራም የበረራ መስመር ከሚበሩት በተጨማሪ ለማንኛውም አይነት አውሮፕላን በተሳፋሪነት መጓጓዝን ሙሉ ሽፋን ይሰጣል፡፡ ሆኖም የሥራ ጠባያቸው ሙሉ ለሙሉ ከበረራ ጋር የተያያዘ እንደ ኢትዮጰያ አየር መንገድ፣ አድማስ አየር አገልግሎት፣ የኢትዮጰያ አየር ኃይል ... ወዘተ የመሳሰሉት በተለየ ሁኔታ አረቦን እንዲከፍሉ ተደርጎ ውሉ ይሰጣቸዋል፡፡
ውሉ የካሣ ክፍያ የማይፈፅምባቸው ሁኔታዎች
ለሕይወት ለተፈጥሮ ሞት በተገዛ ውል ካሣ የማይከፈልባቸው ሁኔታዎች በጦርነት ሳቢያ ወይም ጦርነት መሰል እንቅስቃሴ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ሲደረግ በሚያስከትለው ሞት ወይም የአካል መጉደል ውሉ ካሣ አይከፍልም፡፡ ሆኖም ተጨማሪ አረቦን በመክፈል በጦርነት ለሚደርስ አደጋ ሽፋን ዋስትና ማግኘት ይቻላል፡፡ ዕድሜያአቸው ከ65 ዓመት በላይ ከሆኑም ካሣ አይከፈልም፡፡ ዕድሜያቸው ከስድሣ አምስት ዓመት በላይ ለሆኑ አባላት አረቦን መቀበል ዋስትና አያስገኝም፡፡ ሆኖም ሁኔታው እንደታወቀ ድርጅቱ የተቀበለውን አረቦን ይመልሳል፡፡
ማብራሪያ
o ይህን ውል በተመለከተ የእጅ መታጣት ወይም መቆረጥ የእግር መታጣት መይም መቆረጥ ማለት ከመዳፍ ወይም ከዚያ በላይና ከቁርጭምጭሚት ወይም ከዚያ በላይ የመቆረጥ አደጋ ሲደርስ ብቻ ነው፡፡
o የዓይን መጥፋት ማለት ምንም ዓይነት ብርሀን አለመኖር ማለት ነው፡፡
o መድን የተገባለት ወይም የዋስትናው ገንዘብ ልክ ማለት በዋናው የሕይወት መድን ውል ሠንጠረዥ ለእያንዳንዱ አባል የተሰጠው የዋስትና መጠን ማለት ነው፡፡
|