About Us Financial Service Publication Branches News Forms Contact Us Articles FAQ
 

Side Menu



Proposal Forms
----------------------------
Motor Insurance
Fire Insurance
Personal Accident Insurance 
Workmens Compesation 
Burglarly and House Breaking
Contractors All Risk
Contractors Plant & Machinery
Deterioration of Stock
Electronic Equipment Insurance
Erection All Risk
Inland Carriers Liability
Machinary Loss of Profit
Machinary Insurance
Public Liability
Professional Indemenity
Product Liability 
Fidelity Guaranty
Money Insurance

Claim Notification Forms 
-----------------------------
Motor Insurance
Marine Insurance
Accedent and Disease

 
የቦንድ መድን

መግቢያ

የቦንድ መድን ከሁለት ወይም ከዚያ በላይ ቁጥር ባላቸው ወገኖች መካከል የተደረገ የውል ስምምነት ሳይፈፀም ቢቀር ሽፋን የሚሰጥ ነው፡፡ በተለያዩ ወገኖች መካከል የሚደረግ ሕጋዊ ውል ደግሞ በበርካታ ምክንያቶች ላይሳካ ይችላል፡፡ ስለዚህ ተጎጂውን ወገን ለመካስ ጉዳቱን የሚሸፍን ኃላፊ ዋስ መኖር የግድ ያስፈልጋል፡፡ በመሆኑም ቀጥለን ቦንድ ማስያዝ የሚያስፈልጋቸው ሥራዎች በሚከናወኑበት ወቅት ስለሚሰጡ የቦንድ መድን ሽፋኖች እንመለከታለን፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ15 ዓይነት በላይ የቦንድ የመድን ሽፋኖች አሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ሰባት ዓይነት የቦንድ የመድን ሽፋኖችን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ እነሱም የመልካም ሥራ አፈፃፀም፣ የአቅርቦት፣ የጨረታ ማስከበሪያ፣ የቅድሚያ ክፍያ፣ የጉምሩክ ቀረጥ፣ የጥገናና የማስያዣ ቦንድ ናቸው፡፡

በመሆኑም ይህ ብሮሸር ድርጅቱ ለደንበኞቹ የሚሰጣቸውን የቦንድ የመድን ዓይነቶች በሙሉ ያብራል፡፡

I.የመልካም ሥራ አፈፃፀም እና የአቅርቦት ቦንድ በመልካም ሥራ አፈፃፀምና በአቅርቦት ቦንድ የመድን የውል ይዘቶች ተመሳሳይ ናቸው

ጠቅላላ

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ዋስ እና የሥራ ተቋራጩ በነዚህ ቦንዶች ውል ላይ እስከተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ድረስ ለአሰሪው የመክፈል ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ዋሱና ተቋራጩ፣ ተተኪዎቻቸውና የሚመድቧቸው አካላት ለቀረቡት ስምምነቶች በጋራና በተናጠል ተገዢ ይሆናሉ፡፡

ተቋራጩ ከአሰሪው ጋር በፅሑፍ ውል ከገባና በውሉ ውስጥ የሚካተቱት ቃል ኪዳኖችና የሚሟሉ ሁኔታዎች በሚመለከተው አማካይነት ታይተው ከፀደቁ በኋላ ከያዙት ዓላማ ጭምር የዚህ ውል የዋናው ውል አካል እንደሆኑ ይቆጠራል፡፡

የሚሟሉ ሁኔታዎች

1.የሥራ ተቋራጩ ሁሉንም በውሉ ውስጥ የሚገኙ ስምምነቶች፣ ቃል ኪዳኖችና የሚሟሉ ሁኔታዎች በሚገባ፣ በታማኝነትና በትክክል ከፈፀመ፤ ወይም የሥራ ተቋራጩ እነዚህን ሁኔታዎች ሳይፈፅም ቢቀርና ዋሱ በአሰሪው ላይ ለደረሰው ጉዳት በውሉ ውስጥ ስምምነት እስከተደረሰበት የገንዘብ መጠን ድረስ ክፍያ ከፈፀመ፤ በውሉ የተገባው ግዴታ ሙሉ ለሙሉ እንደተጠናቀቀ ይቆጠራል፡፡ ነገር ግን ከላይ የተጠቀሱት ሁኔታዎች ካልተፈፀሙ ውሉ እንደፀና ይቆይና የተጠቀሱትንም ጥቅሞች ያስገኛል፡፡

2.ይህ ቦንድ ከዚህ በታች በተዘረዘሩትና በውሉ መሠረት ለአሰሪው የሽፋን መብት እንደቅድመ ሁኔታ በሚታዩትና በዋሱ በድርጅቱ በኩል ተገላጭ በሆኑት ሁኔታዎች መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

አሰሪው ወይም የአሰሪው ተጠሪ ወይም ተወካይ የማንኛውንም ጉዳት ወይም ግድፈት የሚያስከትል ድርጊትን መኖር እንደአወቁ፣ በወቅቱ የአገኙትን መረጃ በተሟላ መልኩ በማጠናቀር ለዋሱ ለድርጅቱ ዋና መ/ቤት ወይም ቅርንጫፍ ወዲያው በፅሑፍ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡

ተቋራጩ በውል ስምምነቱ ደንብ መሠረት ሳይፈፅም ቢቀር ውሉ ይቋረጣል፡፡ ኃላፊነቱን የወሰደው ዋስ በውሉ መሠረት የሚቀረውን ሥራ በተቋራጩ እግር ምትክ ተተክቶ የመሥራት ወይም በሌላ ተቋራጭ የማሰራት መብት አለው፡፡

ተቋራጩ የውል ግዴታውን በሚጥስበት ወቅት ዋሱ የመዳረግ መብቱን በመጠቀም ከውሉ የመነጨው የማንኛውም የተቋራጩ መብትና ንብረት ተጠቃሚ ይሆናል፡፡ በውሉ መሠረት ለተቋራጩ የሚተላለፍ ማንኛውም ክፍያ፣ ገንዘብና ንብረት አሰሪው ለዋሱ ለሚያቀርበው ማንኛውም ዕዳና የይገባኛል ጥያቄ ይተላለፋል፡፡

II.የጨረታ ማስከበሪያ ቦንድ

በዚህ ቦንድ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ዋስ እና ሥራ ተቋራጩ በውሉ ላይ እስከተገለፀው መጠን ድረስ ለተጎጂው ለመክፈል የግዴታ ስምምነት ገብተዋል፡፡ ዋሱ እና ሥራ ተቋራጩ፣ ተተኪዎቻቸውና ተወካዮቻቸው ለዚህ ውል ተገዢ ይሆናሉ፡፡

ሥራ ተቋራጩ የገባውን ውል እና ውሉ የተፈፀመበትን ዓላማ፣ ውሉ የተፈፀመበትን ቀንና ዝርዝር መረጃዎችን የሚያሳዩ ከጨረታው ጋር የተያያዙ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

የሚሟሉ ሁኔታዎች

ተቋራጩ ሥራ ተቋራጩ ይህን ውል ለመፈፀም ባይችል ሳይችል ቢቀር ዋሱ ራሱ ወይም ተተኪዎቹ ሥራ ተቋራጩ ለሥራውና ለቁሳቁስ ባቀረበው የጨረታ ዋጋና አሰሪው ለተጠቀሰው ሥራና ቁሳቁስ ከሌሎች ተቋራጮች ጋር በተስማማበት ዋጋ መካከል ያለውን ልዩነት ለአሰሪው ለመክፈል ይገደዳሉ፡፡ ለዚህም በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ የተወሰነ የጊዜ ገደብ ባይኖር የጨረታው አሸናፊ መሆኑ በታወቀ በአሥር ቀናት ውስጥ ቦንድ ክፍያው ይፈፀማል፡፡ አሰሪው ከሌሎች ተቋራጮች ጋር የተስማማበት ዋጋ ከመጀመሪያው ዋጋ የበለጠ ሆኖ ቢገኝ የዋሱ ኃላፊነት በምንም መንገድ ከዋስትናው መጠን ሊበልጥ አይችልም፡፡


III.የቅድሚያ ክፍያ ቦንድ

በዚህ ቦንድ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ዋስ እና የሥራ ተቋራጩ በውሉ ላይ እስከተጠቀሰው መጠን ድረስ ለአሰሪው ለመክፈል የግዴታ ስምምነት ገብተዋል፡፡ ዋሱና ሥራ ተቋራጩ፣ ተተኪዎቸቸውና ተወካዮቻቸው ለዚህ ውል ተገዢ ይሆናሉ፡፡

የሥራ ተቋራጩ ከአሰሪው ጋር በፅሑፍ በገባው ውልና አሠሪው ገንዘቡን ለመክፈል ለተስማማበት ዓላማ ብቻ ለሚከፍለው የቅድሚያ ክፍያ መጠን ተቋራጩ የቦንድ መድን ሲያመጣ የተስማሙበትን ክፍያ አሰሪው ይፈፅማል፡፡ ይህ የቦንድ ስምምነት የቅድሚያ ክፍያው ስምምነት ከተፈፀመ ቀን ጀምሮም ሆነ ከዛ በኋላ የሚደረጉትን የህግ ማስተካከያዎች ጨምሮ የፀና ይሆናል፡፡

የሚሟሉ ሁኔታዎች

1.የሥራ ተቋራጩ ሁሉንም የቅድሚያ ክፍያውን የተመለከቱ ስምምነቶች፣ ቃል ኪዳኖች እና የሚሟሉ ሁኔታዎች በሚገባ፣ በእውነትና በትክክል ከፈፀመ፣

2.ወይም የሥራ ተቋራጩ እነዚህን ሁኔታዎች ሳይፈፅም በመቅረቱ ዋሱ በተቋራጩ እግር ተተክቶ በስምምነቱ ውስጥ የተጠቀሰውን የክፍያ መጠን ለአሰሪው ከፈፀመ፣ በዚህ ውል የተገባው ግዴታ እንደተሟላ ይቆጠራል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ውሉ የፀና ሆኖ የተጠቀሱትንም ጥቅሞች ያስገኛል፡፡

3.ይህ ቦንድ ለአሰሪው መብት መከበር በቅድመ ሁኔታነት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሁኔታዎች መሠረት በዋሱ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

የውሉ ዘመን ካበቃ በኋላ ዋናው ውል ለዋሱ ይመለሳል፡፡ የውሉ ዘመን ከማብቃቱ በፊትም ሆነ በማብቂያው ቀን ከአሰሪው ለዋሱ የቀረበ ምንም ዓይነት የካሣ ጥያቄ ከሌለ ይህ ቦንድ ለዋሱ ቢመለስም ባይመለስም የተሰረዘና ዋጋ የሌለው ይሆናል፡፡

አሰሪው ወይም የአሰሪው ተጠሪ ወይም ተወካይ የማንኛውንም ጉዳት ወይም ግድፈት የሚያስከትል ድርጊትን መኖር እንደአወቁ፣ በወቅቱ የአገኙትን መረጃ በተሟላ መልኩ በማጠናቀር ለዋሱ ለድርጅቱ ዋና መ/ቤት ወይም ቅርንጫፍ ወዲያው በፅሑፍ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡

ተቋራጩ የውል ግዴታውን በሚጥስበት ወቅት ዋሱ የመዳረግ መብቱን በመጠቀም ከውሉ የመነጨው የማንኛውም የተቋራጩ መብትና ንብረት የተጠቃሚ ይሆናል፡፡ በውሉ መሠረት ለተቋራጩ የሚተላለፍ ማንኛውም ክፍያ፣ ገንዘብና ንብረት አሰሪው በማስቀረት ለዋሱ ከሚያቀርበው ማንኛውም ዕዳና የይገባኛል ጥያቄ ላይ ይቀንሳል፡፡

ማግለያዎች

በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በሚከተሉት ሁኔታዎች ለሚፈጠሩ ክስተቶች ዋሱ በዚህ ቦንድ ኃላፊነት አይኖርበትም፡፡

-በጦርነት፣ በወረራ፣ በውጭ ጠላት ድርጊት፣ በጥላቻና በጦርነት መሰል ድርጊት ጦርነት ቢታወጅም ባይታወጅም፣ በእርስ በርስ ጦርነት፣
- በወታደራዊ አመፅ፣ በሕዝብ ብጥብጥ፣ በሕዝባዊ አመፅ፣ በወታደራዊ አመፅ፣ በውንብድና፣ በአብዮትና በሥልጣን ንጥቂያ፣ በወታደራዊ ሕግ ወይም ለረዥም ጊዜ በተደረገ ወታደራዊ ከበባ ወይም መተዳደሪያ ደንብን ወይም ወታደራዊ ሕግን ለማስጠበቅ በሚካሄድ ወይም ማንኛውም የሽብር ድርጊት፣
- በመሬት መንቀጥቀጥ፣ በጎርፍ በሌላ የተፈጥሮ ክስተት፣

የግልግል ዳኝነት

ከዚህ ቦንድ የመነጨ ማንኛውም ልዩነት በተዋዋዮች አማካይነት በፅሑፍ ለተመረጠ አስታራቂ የግልግል ዳኛ ውሣኔ ይቀርባል፡፡ ሁለቱ ወገኖች በአንድ ብቸኛ የግልግል ዳኛ ላይ ሊስማሙ ካልቻሉና ከሁለቱ ወገኖች አንዳቸው በፅሑፍ ከጠየቁ ወይም የግልግል ዳኞቹ ወደ መረጃ ከመግባታቸው በፊት በግልግል ዳኞች በተመረጠው ዳኛ ላይ ካልተስማሙ እና በሁለት የግልግል ዳኞች ጉዳዩ እንዲታይ ካስፈለገ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በሁለቱም ወገኖች በፅሑፍ ምርጫው ይካሄዳል፡

የተመረጠው ዳኛ ከግልግል ዳኞች ጋር በመሆንና በሰብሳቢነት በመምራት ለማንኛውም መብትም ሆነ ተግባር ቅድመ ሁኔታ ያወጣል፡፡

የተመረጠው ዳኛ ከግልግል ዳኞች ጋር በመሆንና በሰብሳቢነት በመምራት የሚሰጠው ውሣኔ ከማንኛውም መብትም ሆነ ተግባር በፊት ተፈፃሚ መሆን ይኖርበታል፡፡

IV.ቀረጥና ግብር ሳይከፈልባቸው በጊዜያዊነት ወደ አገር ውስጥ ለገቡና ተመልሰው ለሚወጡ ዕቃዎች የሚሆን የተለየ የቀረጥ ቦንድ

መድን ገቢው ከዚህ በኋላ ..ባለቤት.. እየተባለ የሚጠራው ይህ አገላለፅ የዋናውን አካል ተተኪዎች/ወራሾች፣ ሥራ አስኪያጆቹን አስተዳዳሪዎቹን እና፣ ሕጋዊ ወኪሎቹን ያካትታል፡ እና መድን ሰጪው ከዚህ በኋላ ..ዋስ.. እየተባለ የሚጠራው ይህ አገላለፅ የዋሱን ተተኪዎች/ወራሾች፣ ሥራ አስኪያጆች፣ አስተዳዳሪዎችና ሕጋዊ ወኪሎችን ያካትታል ለኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለሥልጣን ከዚህ በኋላ ..ባለሥልጣን.. እየተባለ ለሚጠራው ይህ አገላለፅ የባለሥልጣኑን ተተኪዎች እና የሚመድባቸውን አካላት ያካትታል በትክክል እንዲከፈል ስምምነት ለተደረገበት የክፍያ መጠን ማንኛውም ጉዳዩ የሚመለከተው አካልና ወራሾች፣ ጉዳይ ፈፃሚዎች፣ አስተዳዳሪዎችና ሕጋዊ ተወካዮች ሁሉ በዚህ ውል መሠረት ለባለሥልጣኑ ተገቢውን ክፍያ የመፈፀም ግዴታ አለባቸው፡፡


የሽፋን መጠን

ከላይ የተጠቀሰው ግዴታ ገቢ ባለቤት የኢንቮይስ ቁጥር ፣ ቀን፣ የተጫነበት ዝርዝር፣ የተጫነበት አየር መንገድ፣ ቢል፣ ትራክ ዌይ ቢል፣ የቀረጥ ቁጥሩ በዝርዝር ተገልፆ የተቀመጠበት ዕቃ በጊዜያዊነት ወደ ኢትዮጵያ ሲያስገባ፡-


ሀ.ወደ አገር ውስጥ ለሚገቡ ዕቃዎች የሚከፈለውን ቀረጥና ግብር አይከፍልም፡፡

ለ. ከላይ የተጠቀሰው ግዴታ ገቢ የተጠቀሰውን ዕቃ ስምምነት በተገባበት ጊዜ ውስጥ ወይም ባለሥልጣኑ በሚፈቅደው የጊዜ ገደብ ውስጥ መልሶ ማውጣት ይኖርበታል፡፡ ይህን በሚያደርግበት ጊዜ በባለሥልጣኑ ትዕዛዝ መሠረት የተጠቀሰውን ዕቃ መልሶ ለማውጣቱ ማረጋገጫ እንዲሆን በጉምሩክ የመውጫ ቢሮ የተረጋገጠ የጉዞ ዲክላራሲዮን እና የወጪ ሰነዶችን ማሟላቱን የሚያረጋግጥበት የመላኪያ ዲክላራሲዮን ማግኘት ይኖርበታል፡፡

ሐ.ወይም የተጠቀሰውን ዕቃ ከሚመለከተው አካል በተፈቀደለት መሠረት መልሶ ወደ ውጪ አገር የማይልክ ከሆነ ሙሉውን ግብርና ቀረጥ ለባለሥልጣኑ ይከፍላል፡፡
የሚሟላ ሁኔታዎች

ከላይ የተጠሰው ዝርዝር የቀረጥ ቦንድ የሚከተሉት የሚሟሉ ሁኔታዎች ይኖሩታል፡፡

1.ከላይ የተጠቀሰው ግዴታ ገቢ ባለቤት የተጠቀሰውን ዕቃ መልሶ ወደውጭ የማይልክ ከሆነ ሙሉ ግብሩንና ቀረጡን ለባለሥልጣኑ ይከፍላል፡፡ ከድርጅቱ በፅሑፍ የተረጋገጠ ፈቃድ እስካልተሰጠው ድረስ የተጠቀሰውን ዕቃ በከፊል ወይም በሙሉ መሸጥ ወይም ለሦስተኛ ወገን ማስተላለፍ ወይም ከጥቅም ውጭ ማድረግ ማስወገድ አይችልም፡፡

2.የተጠቀሰውን ዕቃ መልሶ ከአገር በሚያስወጣበት ጊዜ የመላኪያ ሰነዶችን ማሟላቱን የሚገልፅ የመላኪያ ዲክላራሲዮን እና በባለሥልጣኑ ትዕዛዝ መሠረት የተጠቀሰውን ዕቃ መልሶ ለመላኩ በጉምሩክ ቢሮ የተረጋገጠ የጉዞ ዲክላራሲዮን መያዝ አለበት፡፡ ከዚህ በኋላ ይህ የጠቅላላ የቀረጥ ቦንድ ይሰረዛል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ሙሉ በሙሉ እንደፀና ይቆያል፡፡

3.በመሆኑም በሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች መካከል በሚከተለው ሁኔታ ተፈፃሚ የሚሆን ስምምነት ተደርሷል፡፡


ሀይህ የጠቅላላ ቀረጥ ቦንድ በቀረጥ አዋጅ ቁጥር 6ዐ/1997 ምዕራፍ ሰባት መሠረት የተሰጠ ነው፡፡
ለይህ የጠቅላላ ቀረጥ ቦንድ ከላይ እንደተጠቀሰው የቀረጥ ቦንድ ሠራተኛወይም የሚመለከተከው ኃላፊ ከፈረመበት ቀን አንስቶ አስቀድሞ እስከተጠቀሰው ቀን ድረስ በጊዜያዊነት ወደ ኢትዮጵያ ለገቡ ዕቃዎች ሽፋን ይሰጣል፡፡
ሐዋሱ ይህንን የጠቅላላ ቀረጥ ቦንድ ካለምንም መዘግየት ለባለሥልጣኑ የመስጠት ሥልጣንና ግዴት አለበት፡፡ ስለዋሱ ሆኖ በዋሱ ስም ቦንድ የሚፈርም አካል ይህን ቦንድ የመፈረም ሙሉ ሥልጣን አለው፡፡

V.በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚተላለፉ ዕቃዎች የሚሆን የተለየ የቀረጥ ቦንድ

ጠቅላላ

መድን ገቢው ከዚህ በኋላ ..ባለቤት.. እየተባለ የሚጠራው ይህ አገላለፅ የዋናው አካል ተተኪዎች/ወራሾች፣ ሥራ አስኪያጆች፣ አስተዳዳሪዎችንና ሕጋዊ ወኪሎችን ያካትታል እና መድን ሰጪው ከዚህ በኋላ ..ዋስ.. እየተባለ የሚጠራው ይህ አገላለፅ ተተኪዎቹን/ወራሾቹን፣ ሥራ አስኪያጆቹን፣ አስተዳዳሪዎቹንና ሕጋዊ ወኪሎቹን ያካትታል ለኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለሥልጣን ከዚህ በኋላ ባለሥልጣን እየተባለ ለሚጠራው ይህ አገላለፅ የባለሥልጣኑን ተተኪዎች እና የሚመድባቸውን አባላት ያካትታል ለመክፈል ስምምነት የተደረሰበትን መጠን ለባለሥልጣኑ ለመክፈል ግዴታ ገብተዋል፡፡

ሽፋን

ሽፋን የሚሰጠው ከላይ የተጠቀሰው ግዴታ ገቢ ባለቤት ቀረጥ ያልተከፈለባቸውን ዕቃዎቹን ካሉበት የመነሻ ጉምሩክ የዕቃዎቹ መድረሻ ወደአለበት ጉምሩክ በመንገድ/በየብስ በሚያስተላልፍበት ጊዜ ነው፡፡

የሚሟሉ ሁኔታዎች

ከላይ የተገለፀው የተለየ የቀረጥ ቦንድ የሚከተሉትን ሁኔታዎች ማሟላት አለበት፡፡

1.ዕቃው በጉምሩክ ባለሥልጣን በታዘዘው የመተላለፊያ መስመር ላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በተገቢው ሁኔታ ከተላለፈና በጉምሩክ ማስተላለፊያ መድረሻ ቦታ በተገቢው ሁኔታ ደርሶ ለሚመለከተው የጉምሩክ ኦፊሰር ከቀረበ፣

2.ዕቃው በሚተላለፍበት ወቅት በማስተላለፊያው ፈቃድ ማመልከቻና በጉዞ ዲክላራሲዮን ቅፅ ከተገለፀው ውጪ በጥራትና በመጠን መቀነስ በባለሥልጣኑ ትዕዛዝ ካልሆነ በስተቀር በተጠቀሰው ዕቃ ላይ ካልተከሰተ፣

3.ከላይ የተጠቀሰው ግዴታ ገቢ በባለሥልጣኑ ፍላጎት መሠረት ለዕቃዎቹ እንዲከፈል የታዘዘውን ቀረጥ በ9ዐ ቀናት ውስጥ ጉዳዩ ለሚመለከተው የጉምሩክ ኃላፊ ካላቀረበ ወይም ለማቅረብ የሚያስፈልገውን ሂደት ካላከናወነ፣ ለአገር ውስጥ አገልግሎት የሚውሉ ካልሆነ ወይም ወደግምጃ ቤት መጋዘን በሚገቡበት ደንብ መሠረት ያልገቡ ዕቃዎችን በተመለከተ ባለሥልጣኑ በሚያዘው መሠረት ማንኛውንም በዕቃዎቹ ላይ የጣለውን ግብርና ቀረጥ ወይም በተጠቀሱት ዕቃዎች ላይ ያለበትን ዕዳ ይከፍላል፡፡ ዕዳው በመከፈሉም ይህ የቀረጥ ቦንድ ውል ይሰረዛል፡፡ ዕዳው ካልተከፈለ ግን ውሉ እንደፀና ይቆያል፡፡ በመሆኑም ሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች


ሀይህ ልዩ የቀረጥ ቦንድ በጉምሩክ ማቋሚያ አዋጅ ቁጥር 6ዐ/1997 ምዕራፍ ሰባት መሠረት የተሰጠ መሆኑን፣

ለይህ የቀረጥ ቦንድ ዋጋ የሚኖረው የሚፀናው ለአንድ ግዢ ግብይት ብቻ መሆኑን፣

ሐለባለሥልጣኑ ጥቅም ሲባል ዋሱ ካለምንም መዘግየት ይህንን የቀረጥ ቦንድ የመስጠት ኃላፊነትና ግዴታ ያለበት መሆኑንና ዋሱን በመወከል በዋሱ ስም ይህን ቦንድ የፈረመው አካል ቦንዱን የመፈረም ሙሉ ሥልጣን ያለው መሆኑን በመቀበል ስምምነት አድርገዋል፡፡

VI. የማስያዣ ቦንድ (Retention Bond)

ጠቅላላ

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ዋስ እና የሥራ ተቋራጩ በነዚህ ቦንዶች ውል ላይ እስከተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ድረስ ለአሰሪው የመክፈል ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ዋሱና ተቋራጩ፣ ተተኪዎቻቸውና የሚመድቧቸው አካላት ለቀረቡት ስምምነቶች በጋራና በተናጠል ተገዢ ይሆናሉ፡፡

የሥራ ተቋራጩ በመድን ውሉ ውስጥ የተጠቀሱትን ጠቃሚ መረጃዎች በማካተት ከአሰሪው ጋር በፅሑፍ የተደገፈ ውል ይፈፅማል፡፡ የሥራ ተቋራጩ ከአሠሪው ጋር በሚገባው ውል መሠረት አሠሪው ውሉን በጊዜያዊነት በመቀበሉ የዚህ ውል አካል የሆነውንና የጥገና ሥራው ከመጠናቀቁ በፊት በማስያዣነት የተያዘውን ገንዘብ ለሥራ ተቋራጩ ለመልቀቅ የሚያስችለውን ስምምነት ያደርጋል፡፡ ይህም ሥራ ላይ የሚለውንና ማስተካከያ እዲደረግበት የተፈቀደውን ኮንትራት ጨምሮ በማንኛውም መንገድ የተቀመጡ፣ የሚሟሉ ሁኔታዎችና የተገቡ ቃል ኪዳኖች የዚህ ቦንድ አካል እንደሆኑ ይቆጠራል፡፡

የሚሟሉ ሁኔታዎች

1.የሥራ ተቋራጩ አዲስ በተፈፀመው ውል ውስጥ የሚገኙ ሁሉንም ስምምነቶች፣ ቃልኪዳኖችና የሚሟሉ ሁኔታዎች በሚገባ፣ በታማኝነትና በትክክል ከፈፀመ ወይም ዋሱ አሰሪው የሚጠይቀውን ስምምነት የተደረገበትን ክፍያ ከፈፀመ በዚህ ውል የተገባው ግዴታ እንደተሟላ ይቆጠራል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ውሉ እንደፀና ይቆያል፤ የተጠቀሱትንም ጥቅሞች ያስገኛል፡፡

2.ይህ ቦንድ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የአሰሪው መብት በሆኑት ሁኔታዎች መሠረት በዋሱ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

አሰሪው ወይም የአሰሪው ተጠሪ ወይም ተወካይ ማንኛውንም ጉዳት ወይም ግድፈት የሚያስከትል ድርጊት መከሰቱን እንደአወቁ በወቅቱ የአገኙትን መረጃ በተሟላ መልኩ በማጠናቀርና ለዋሱ ዋና መ/ቤት ወይም ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ወዲያውኑ በፅሑፍ ያሳውቃል፡፡

ተቋራጩ የውል ግዴታውን በሚጥስበት ወቅት ዋሱ የመዳረግ መብቱን በመጠቀም ከውሉ የመነጨው ማንኛውም የሥራ ተቋራጩ መብትና ንብረት ተጠቃሚ ይሆናል፡፡ በውሉ መሠረት ለተቋራጩ የሚተላለፍ ማንኛውም ክፍያ፣ ገንዘብና ንብረት አሰሪው ለዋሱ ለሚያቀርበው ማንኛውም ዕዳና የይገባኛል ጥያቄ ይተላለፋል፡፡


ማግለያዎች

ዋሱ በብጥብጥ ወይም ሠራተኞች በፈጠሩት ችግር፣ ወይም በረብሻ፣ በእሳት፣ በተፈጥሮ ክስተት ወይም አንድን ሥራ ለመጠገን ወይም እንደገና ለመገንባት በሚፈፀም ድርጊት በደረሰ የንብረት ውድመት ወይም በሰዎች ላይ ለደረሰ ጉዳት ወይም የማንኛውም የሥራ አፈፃፀም ወይም የጥራት ጉድለት ኃላፊነት አይኖርበትም፡፡

VII.የጥገና ቦንድ (Maintenance Bond)

ጠቅላላ

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ዋስ እና የሥራ ተቋራጩ በነዚህ ቦንዶች ውል ላይ እስከተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ድረስ ለአሰሪው የመክፈል ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ዋሱና ተቋራጩ፣ ተተኪዎቻቸውና የሚመድቧቸው አካላት ለቀረቡት ስምምነቶች በጋራና በተናጠል ተገዢ ይሆናሉ፡፡

የጥገና ቦንድ የሚሰጠው የሥራ ተቋራጩ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ጥገና ለማካሄድ ከአሰሪው ጋር በፅሑፍ ውል ሲገባ ነው፡፡ ከዚህ በኃላ በሥራ ላይ በሚውለው የጥገና ውል ስምምነት ላይ የሚደረገውን ማሻሻያ ማስተካከያ ጨምሮ የሥራ ተቋራጩና አሰሪው የፈፀሙት ስምምነት ከተገባው ቃል እና ከሚሟሉ ሁኔታዎች ጋር የዚህ ቦንድ አካል እንደሆኑ ይቆጠራል፡፡

የሚሟሉ ሁኔታዎች

1.የሥራ ተቋራጩ የተጠቀሰውን የጥገና ስምምነት ውል የተመለከቱ ሁሉንም ስምምነቶች፣ ቃል የተገቡና የሚሟሉ ሁኔታዎችን በተገቢው ሁኔታ፣ በታማኘነት፣ በትክክል ከፈፀመ፣

2.ወይም የሥራ ተቋራጩ እነዚህን ሁኔታዎች ሳይፈፅም ቢቀርና ዋሱ በጥገና ውሉ መሠረት በተቋራጩ እግር ተተክቶ በአሰሪው ላይ ለደረሰው ጉዳት በስምምነቱ ውስጥ እስከተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ድረስ ክፍያ ከፈፀመ፣

የውል ግዴታው የተሟላ በመሆኑ ቦንዱ ይሰረዝና ዋጋ እንዳይኖረው ይደረጋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ውሉ እንደፀና ቆይቶ የተጠቀሱትንም ጥቅሞች ያስገኛል፡፡

3.ይህ ቦንድ ከዚህ በታች በተዘረዘሩትና በውሉ መሠረት ለአሰሪው የሽፋን መብት እንደቅድመ ሁኔታ በሚታዩትና በዋሱ በድርጅቱ በኩል ተገላጭ በሆኑት ሁኔታዎች መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡


3.1አሰሪው ወይም የአሰሪው ተጠሪ ወይም ተወካይ ማንኛውንም ጉዳት ወይም ግድፈት የሚያስከትል ድርጊት መከሰቱን እንደአወቁ በወቅቱ የአገኙትን መረጃ በተሟላ መልኩ በማጠናቀር፤ ለዋሱ ዋና መ/ቤት ወይም ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ወዲያውኑ በፅሑፍ ያሳውቃሉ፡፡

3.2ተቋራጩ የውል ግዴታውን በሚጥስበት ወቅት ዋሱ የመዳረግ መብቱን በመጠቀም ከውሉ የመነጨው ማንኛውም የሥራ ተቋራጩ መብትና ንብረት ተጠቃሚ ይሆናል፡፡ በውሉ መሠረት ለተቋራጩ የሚተላለፍ ማንኛውም ክፍያ፣ ገንዘብና ንብረት አሰሪው ለዋሱ ለሚያቀርበው ማንኛውም ዕዳና የይገባኛል ጥያቄ ይተላለፋል፡፡

3.3የውሉ ደንብ አንቀፅ በሚጣስበት ወቅት ዋሱ ከውሉ የመነጨውን ማንኛውንም የሥራ ተቋራጩን መብትና ንብረት የመዳረግ መብት ያገኛል፡፡
3.4በውሉ መሠረት ለተቋራጩ የተላለፈ ማንኛውም ክፍያ ገንዘብና ንብረት አሰሪው በዋሱ ላይ ለሚያነሳው (ለሚያቀርበው ማንኛውም የዕዳና የካሣ ጥያቄ ይተላለፋል፡፡

ማግለያዎች

ዋሱ በብጥብጥ ወይም ሠራተኞች በፈጠሩት ችግር፣ ወይም በረብሻ፣ በእሳት፣ በተፈጥሮ ክስተት ወይም አንድን ሥራ ለመጠገን ወይም እንደገና ለመገንባት በሚፈፀም ድርጊት በደረሰ የንብረት ውድመት ወይም በሰዎች ላይ ለደረሰ ጉዳት ወይም የማንኛውም የሥራ አፈፃፀም ወይም የጥራት ጉድለት ኃላፊነት አይኖርበትም፡፡

የግልግል ዳኝነት

ከዚህ ቦንድ የመነጨ ማንኛውም ልዩነት በተዋዋዮች አማካይነት በፅሑፍ ለተመረጠ አስታራቂ የግልግል ዳኛ ውሣኔ ይቀርባል፡፡ ሁለቱ ወገኖች በአንድ ብቸኛ የግልግል ዳኛ ላይ ሊስማሙ ካልቻሉና ከሁለቱ ወገኖች አንዳቸው በፅሑፍ ከጠየቁ ወይም የግልግል ዳኞቹ ወደ መረጃ ከመግባታቸው በፊት በግልግል ዳኞች በተመረጠው ዳኛ ላይ ካልተስማሙ እና በሁለት የግልግል ዳኞች ጉዳዩ እንዲታይ ካስፈለገ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በሁለቱም ወገኖች በፅሑፍ ምርጫው ይካሄዳል፡

የተመረጠው ዳኛ ከግልግል ዳኞች ጋር በመሆንና በሰብሳቢነት በመምራት ለማንኛውም መብትም ሆነ ተግባር ቅድመ ሁኔታ ያወጣል፡፡

ማሳሰቢያ፡-
ይህ ፅሑፍ ስለቦንድ ዋስትና የቀረበ ማብራሪያ እንጂ በሕግ ፊት የሚፀና ውል አይደለም፡፡


   

Home  About Us Financial Indicator Life Insurance Non-Life Insurance Main Branch Forms Contact Us