About Us Financial Service Publication Branches News Forms Contact Us Articles FAQ
 

Side Menu



Proposal Forms
----------------------------
Motor Insurance
Fire Insurance
Personal Accident Insurance 
Workmens Compesation 
Burglarly and House Breaking
Contractors All Risk
Contractors Plant & Machinery
Deterioration of Stock
Electronic Equipment Insurance
Erection All Risk
Inland Carriers Liability
Machinary Loss of Profit
Machinary Insurance
Public Liability
Professional Indemenity
Product Liability 
Fidelity Guaranty
Money Insurance

Claim Notification Forms 
-----------------------------
Motor Insurance
Marine Insurance
Accedent and Disease

 
የንግድ ተሽከርካሪ የመድን ዋስትና ውል

መድን ገቢው የዚህ ውል አካል በሆኑት የውል መጠየቂያ እና የውል ማረጋገጫ ቅፅ መሠረት ዋስትና ለመግዛት ለኢትዮጵያ መድን ድርጅት ከዚህ በኋላ ድርጅት እየተባለ ለሚጠራው ጥያቄ በማቅረቡና ተገቢውን አረቦን በመክፈሉ ወይም ለመክፈል በመስማማቱ ይህ ዋስትና ለሚሰጠው ሽፋን ተጠቃሚ ይሆናል፡፡

ይህ ፖሊሲ በውሉ ውስጥ የተካተቱት ገደቦች፣ የሚሟሉ ሁኔታዎች፣ ብያኔዎች ከዚህ በኋላ በጥቅሉ የፖሊሲው ውሎች የሚባሉት እንደተጠበቁ ሆነው በውሉ ወቅት ለሚፈጠሩ ክስተቶች ማስረጃ ይሆናል፡፡

ክፍል አንድ
የተሽከርካሪ ዋስትና

1.የመድን ዋስትና በተገባለት ተሽከርካሪ ላይ ጉዳት ወይም ውድመት መድረስ፣

ድርጅቱ የመድን ዋስትና በተገባለት ተሽከርካሪና ተጓዳኝ /የመለዋወጫ/ መሣሪያዎች ላይ በሚከተሉት ሁኔታዎች ለሚደርስ ጉዳት ወይም ጥፋት የካሣ ክፍያ ይፈፅማል፤


ሀ.በድንገተኛ ግጭት ወይም መገልበጥ ወይም በመካኡ??ል ብልሽት ወይም በእርጅና ምክንያት ለደረሰ ግጭት ወይም መገልበጥ፣ ይሁንና የመድን ዋስትና የተሰጠው ተሽከርካሪ አብሮ ካልተጎዳ በስተቀር በጐማዎች ላይ የሚደርስን ጉዳት ወይም ውድመት አይሸፈንም፤

ለ.በእሳት፣ ከውጭ በደረሰ ፍንዳታ፣ በውስጣዊ አካል መቀጣጠል፣ በመብረቅ፣ በሌብነት ወይም በሌብነት ሙከራ፤

ሐ.ባለንብረቱን ለመጉዳት ሆን ብሎ ተሽከርካሪውን በማውደም/በመጉዳት፣

መ.በመጓጓዝ ላይ እያለ ማጓጓዙ በማጓጓዝ ሂደት የማይቀረውን የመጫንና የማውረድ ሂደትንም ይጨምራል በመንገድ ላይ፣ በባቡር፣ ወንዝ/ ማንኛውንም ውኃ በማሻገር ላይ፣ በሊፍት ወይም በአሳንሰር በመጓጓዝ ላይ እያለ፣

ሠ.የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ የአውሎ ንፋስ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ፣ የመሬት መንቀጥቀጥና የመሳሰሉትን ከሰው ልጅ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ የተፈጥሮ ክስተቶችን ሳይጨምር በተሽከርካሪው ላይ በወደቀ አካል ለደረሰ ጉዳት ወይም ጥፋት፤


2.የኃላፊነት መጠን

በውል ሠንጠረዡ ውስጥ የተገለፀ ማንኛውም ተሽከርካሪ ጉዳት ወይም ጥፋት ቢደርስበት ድርጅቱ በራሱ ምርጫ ተሽከርካሪውን ወይም ተለዋጭ ዕቃዎቹን ማደስ፣ መተካት ወይም የጉዳቱን ወይም የጥፋቱን መጠን በጥሬ ገንዘብ መክፈል ይችላል፡፡ ሆኖም የድርጅቱ ኃላፊነት አደጋው በደረሰበት ወቅት የተጎዱ ወይም የጠፉ ተለዋጭ ዕቃዎችን ትክክለኛ ዋጋና ዕቃዎቹን በተሽከርካሪው ላይ ለመግጠም ከሚጠየቀው ተቀባይነት ካለው የእጅ ዋጋ አይበልጥም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የተሽከርካሪው ዋጋ መለዋወጫ ዕቃዎችን ጨምሮ በማንኛውም ሁኔታ መድን ገቢው በሠንጠረዡ ላይ ከገለጹት ግምት ወይም የገበያ ዋጋ መብለጥ የሌለበት ሲሆን ድርጅቱ የሚከፍለው አነስተኛ ሆኖ ያገኘውን ይሆናል፡፡

3.ከአደጋ በኋላ ስለሚከናወን የጥበቃና የማጓጓዝ ሥራ

በውሉ ውስጥ የመድን ዋስትና ሽፋን እንደሚሰጠው በተጠቀሰ ድንገተኛ አደጋ ምክንያት ጉዳት ወይም ውድመት የደረሰበት ተሽከርካሪ በአደጋው ምክንያት መንቀሳቀስ ባይችል ድርጅቱ ለጥበቃና በቅርብ ወደሚገኝና ብቃት ወዳለው ጋራዥ ለማጓጓዝ የሚያስፈልገውን ወጪ ይሸፍናል፡፡ ሆኖም ይህ ወጪ ለተሽከርካሪው ጥገና ከሚያስፈልገው ወጪ ከ2®% አይበልጥም፡፡

4.በዱቤ የተገዛ ወይም በዕዳ ማስከበሪያነት የተያዘ ተሽከርካሪ

ዋስትና የተገባለት ተሽከርካሪ በዱቤ የተገዛ ወይም ለእዳ ማስከበሪያ በዋስትና የተያዘ ከሆነ ማንኛውም ክፍያ በውል ሰነዱ ውስጥ በባለቤትነት ለተጠቀሰ ወገን በጥሬ ገንዘብ ይፈፀማል፡፡ የክፍያው መፈፀም ድርጅቱን በደረሰው ጉዳት ወይም ውድመት ምክንያት ይኖርበት ከነበረው ኃላፊነት ሙሉ በሙሉ ነፃ ያደርገዋል፡፡


5.የማስጠገን ስልጣን

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሁኔታዎች እስከተሟሉ ድረስ መድን ገቢው በአደጋ ምክንያት ጉዳት ለደረሰበት ተሽከርካሪ ጥገና እንዲደረግለት የማዘዝ ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡


ሀ.የጥገናው ወጪ ግምት በሠንጠረዡ ውስጥ ከተጠቀሰው የሥልጣን ገደብ ያልበለጠ ከሆነ፣

ለ.ዝርዝር የጥገና ወጪው ግምት ወዲያውኑ ለድርጅቱ ከቀረበ፣

መ.መድን ገቢው ጥገናው አስፈላጊና ሂሳቡም አግባብነት ያለው ስለመሆኑ ድርጅቱ እንዲያውቀው ካደረገ፡፡

6. በገበያ ላይ ስለማይገኙ የመለዋወጫ ዕቃዎች

ዋስትና ተገብቶለት ጉዳት የደረሰበት የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃ ወይም አካል ጊዜ ያለፈበትና ከአምራቹ ድርጅት የማይገኝ ከሆነ አግባብነት ያለውን የማስጠገኛ ዋጋና አምራቹ ድርጅት ለመለዋወጫ ዕቃዎች ለመጨረሻ ጊዜ ከሰጠው ዋጋ ያልበለጠ የገንዘብ መጠን ይከፈላል፡፡

የክፍል አንድ ማግለያዎች

ድርጅቱ ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ሁኔታዎች ክፍያ የመፈፀም ኃላፊነት የለበትም፡-

1.በሠንጠረዡ ላይ የተጠቀሰውን የአደጋ መነሻ ክፍያ፣
2.በሠንጠረዡ ላይ የተጠቀሰው ተሽከርካሪ በደረሰበት ጥፋት ወይም ጉዳት ምክንያት ለሚከሰት የጥቅም እጦት፣
3.በሠንጠረዡ ላይ የተጠቀሰው ተሽከርካሪ ወይም የተሽከርካሪ አካል በሥራ ወይም በአገልግሎት ብዛት ለደረሰበት ጉዳት ወይም ዋጋ መቀነስ፣
4.ማንኛውም በውል ሠንጠረዡ ላይ የተጠቀሰ ተሽከርካሪ ለደረሰበት የመካኡ??ል፣ ኤሌክትሪካል፣ ኤልክተሮኡ??ስ ወይም ኮም፡??ተር ብልሽት፣
5.ፍሬን በመያዝ፣ በመበሳት፣ በመቆረጥ ወይም በፍንዳታ ምክንያት በጐማዎች ላይ ለሚደርስ ጉዳት፣
6.በተሽከርካሪው ላይ በተገጠመው የማንኛውም የመገናኛ መሣሪያ ላይ ለሚደርስ ማንኛውም አይነት ጥፋት ወይም ጉዳት፣
7.በውሉ መሠረት በቀረበ የካሣ ጥያቄም ሆነ ወይም በሌላ ለተሽከርካሪው በተደረገ ጥገና የተነሳ በተሽከርካሪው ላይ ለደረሰ የገበያ ዋጋ መቀነስ፤
8.በአምራቹ ድርጅት ከተገጠሙትና በግልፅ ተጠቅሰው ዋስትና ከተሰጣቸው በስተቀር ለማንኛውም ራዲዮ፣ ሬኮርደር ማጫወቻ፣ ቴኘሪከርደር፣ ሸራና ገመድ ላይ ለደረሰ ጥፋት ወይም ጉዳት፤

ክፍል ሁለት የሦስተኛ ወገን ኃላፊነት

1.በሠንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው የኃላፊነት መጠን መሠረት መድን ገቢው የመድን ዋስትና የተሰጠውን ተሽከርካሪ በሚገለገልበት ወቅት ወይም የመድን ዋስትና የተሰጠውን ተሽከርካሪ በመጫን ወይም በማራገፍ ሂደት ላይ ለደረሰ አደጋ፣ እንዲሁም የካሣ ጠያቂውን ወጪ ጨምሮ መድን ገቢው ሕጋዊ ኃላፊነት ለሚኖርበትና ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ሁኔታዎች ድርጅቱ ተገቢውን ካሣ ይከፍላል፤

ሀ.በሰው ላይ ለደረሰ የአካል ጉዳት ወይም ሞት እና
ለ.በንብረት ላይ ለደረሰ ውድመት፤ ማካካሻ ይከፍላል፡፡

2.የመድን ዋስትና የተሰጠውን ተሽከርካሪ ለማሽከርከር ሥልጣን የተሰጠው ማንኛውም ሹፌር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች እስካሟላ ድረስ የተቀመጠው ገደብ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ድርጅቱ ካሣ ይከፍልለታል፡፡


ሀ.ራሱ ዋስትና እንደተሰጠው በመቁጠር የዚህ ውል አንቀጾች ተግባራዊ የሚሆኑበትን ገደቦች ያከብራል፣ ያሟላል፡፡ እንዲሁም፣
ለ.በሌላ የድርጅቱ የመድን ዋስትና ማካካሻ የሚያገኝ ካልሆነ፣

3.ድርጅቱ በጽሑፍ ያረጋገጠውን ማንኛውንም ወጪ ይከፍላል፣
4.ድርጅቱ በራሱ ምርጫ

ሀ.በዚህ ክፍል ውስጥ ለተጠቀሰ ለማንኛውም የካሣ ክፍያ ለሚያስጠይቅ የሞት አደጋ ማንኛውንም የአሟሟት ምርመራና ጥያቄ ሊያከናውን የሚችል ወኪል ማዘጋጀት ይችላል፡፡
ለ.በዚህ ክፍል ውስጥ ለተጠቀሰውና የካሣ ክፍያ ለሚያስጠይቅ ማንኛውም ድርጊት ወይም ወንጀል ነው ለተባለ ድርጊት በማንኛውም የፍርድ ቤት ሂደት ላይ ትብብር ሊያደርግ ይችላል፤

የክፍል ሁለት ማግለያዎች
ድርጅቱ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሁኔታዎች ኃላፊነት አይኖርበትም፡-

1.የመድን ገቢው ሠራተኛ የሆነ ማንኛውም ሰው በሥራው ላይ እያለ ለሚደርስበት የአካል ጉዳትና ሞት፣

2.በዚህ ውል አማካኝነት የካሣ ክፍያ የሚጠይቅ ማንኛውም ሰው የራሱ ለሆነ፣ በአደራ በያዘው ወይም በራሱ ቁጥጥር ሥር ለሚገኝ በማንኛውም ንብረት ላይ ማንኛውንም ተሽከርካሪ ይጨምራል ለሚደርስ ጥፋት ወይም ጉዳት፣

3.ማንኛውም የካሣ ጥያቄ ሊያስቀርብ የሚችል ክስተት በተፈጠረበት ወቅት የመድን ዋስትና በተሰጠው ተሽከርካሪ በመጓጓዝ ወይም ወደ ተሽከርካሪው ላይ በመውጣት /በመሣፈር/ ወይም በመውረድ ላይ እያለ ለደረሰ ማንኛውም የአካል ጉዳት ወይም ሞት፤

4.በማንኛውም ድልድይ፣ የምድር ሚዛን፣ የባቡር ሐዲድ የተሸከመ ረጅም ድልድይ፣ ወይም ማንኛውም መንገድ ወይም ማንኛውም ተሽከርካሪ በሚያልፍበት መንገድ ሥር ያለ ነገር፣ በንዝረት ወይም የመድን ዋስትና በተሰጠው ተሽከርካሪም ሆነ በተሽከርካሪው በተጫኑ እቃዎች ክብደት

5.በሠንጠረዡ ላይ በተጠቀሰውና የመድን ዋስትና የተሰጠው ተሽከርካሪ በፈጠረው የእሳት ብልጭታ ወይም አመድ ምክንያት ለደረሰ የሞት፣ የአካል ጉዳት ወይም የንብረት ውድመት፣

6.ለማሽከርከር ከተፈቀደ መንገድ ውጭ የመድን ዋስትና የተሰጠው ተሽከርካሪ ጭነት እንዲጭን ጭነት በማቅረብ ወይም ጭነቱ ከተራገፈ በኋላ ጭነቱን በማራገፍ ሂደት ላይ የመድን ዋስትና ከተሰጠው ተሽከርካሪ ሹፌር ወይም ረዳት ሹፌር በስተቀር በሌላ በማንኛውም ሰው ላይ ለሚደርስ የሞት፣ የአካል ጉዳት ወይም የንብረት ውድመት፤

ጠቅላላ ሁኔታዎች

1.የካሣ ጥያቄ ባለመቅረቡ የሚገኝ ቅናሽ
እድሳት ከመደረጉ በፊት ባለው የዋስትና ዘመን ውስጥ በዚህ ውል መሠረት ምንም አይነት የካሣ ጥያቄ ካልቀረበ ወይም ካላጋጠመ፣ ደንበኛው የካሣ ጥያቄ ባለማቅረባቸው በውል እድሳት ወቅት በድርጅቱ የቅናሽ ስኬል መሠረት ተገቢው የአረቦን ቅናሽ ይደረግላቸዋል፡፡

2. ሽፋን ስለማቋረጥ
በውል ከተሰጠው ሽፋን ውጪ በሆነ ጉዳት ወይም ጥፋት ምክንያት የመድን ዋስትና የተሰጠው ተሽከርካሪ ሥራ ስለማቋረጡ ለድርጅቱ በጽሑፍ ማስታወሻ ከተሰጠው፣ ማስታወሻው ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ሽፋኑ እንዲቆም የሚደረግ ሲሆን ሽፋኑ ቢያንስ ለ12 አሥራ ሁለት ተከታታይ ሣምንታት ከተቋረጠ ድርጅቱ በዚያው ልክ የውሉን ሽፋን ያራዝማል፡፡

3.የባለቤትነት ለውጥ
ዋስትና በተሰጠው ተሽከርካሪ ላይ የባለቤትነት ለውጥ ከተደረገ ለተለዋጩ ባለቤት የሚሰጠው ሽፋን እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

ሀ.ይህን የሚከለክል ማንኛውም አንቀፅ ቢኖርም እንኳ ዋስትናው ተሽከርካሪውን እንዲጠቀምበት ለተሰጠው ወገንም ያገለግላል፣
ለ.ጥቅሙ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ ተጠቃሚውና ድርጅቱ ውሉን ሊያቋርጡ ይችላሉ፡፡

4.ለአደጋ የመጋለጥ ሁኔታ ስለመለወጥ

መድን ገቢው ማንኛውንም ለአደጋ የመጋለጥ ሁኔታን ለውጥ ለድርጅቱ ያሳውቃል፡፡ ሆኖም መድን ገቢው ለአደጋ የመጋለጥ ሁኔታውን ለውጥ ካላሳወቀና ድርጅቱ በውሉ ላይ ተጨማሪ ሽፋን ተሰጥቶት እንዲካተት ካላደረገ በስተቀር በለውጡ ምክንያት ለደረሰ ጥፋት፣ ጉዳት ወይም ኃላፊነት የሚቀርብ ጥያቄ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

4.ዕድሳትና ጥገና

ከሦስተኛ ወገን ከሚቀርብ የኃላፊነት ጥያቄ በስተቀር ዋስትና የተሰጠው ተሽከርካሪ በተሽከርካሪ ንግድ ድርጅት ውስጥ ለዕድሳት ወይም ለጥገና በሚቆምበት ወቅትም ሽፋኑ ይቀጥላል፡፡


ሽፋን የሚሰጥበት ሁኔታ

1.የተሰጠው የመድን ሽፋን ..አጠቃላይ.. ከሆነ የዚህ ውል ክፍሎች/አንቀጾች በሙሉ ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡

2.የተሰጠው የመድን ሽፋን "ለሦሥተኛ ወገን፣ ለእሳትና ስርቆት" ከሆነ ክፍል አንድ የሚያገለግለው በቀጥታ በእሳት፣ በራስ መቀጣጠል፣ በመብረቅ፣ በውጭ ፍንዳታ፣ በስርቆት ወይም በስርቆት ሙከራ ለሚደርስ ጥፋት ወይም ጉዳት ብቻ ይሆናል፡፡

3.የተሰጠው የመድን ሽፋን ..ለሦስተኛ ወገን.. ብቻ ከሆነ የዚህ ውል ክፍል አንድ ይሰረዛል፡፡

*አጠቃላይ ማግለያዎች/በውሉ
የማይሸፈኑ

1.ድርጅቱ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሁኔታዎች መንስዔነት ለደረሰ አደጋ፣ጥፋት፣ ጉዳት ወይም ኃላፊነት ክፍያ የመፈፀም ኃላፊነት አይኖርበትም፡፡

ሀ.ከኢትዮጵያ የድንበር ክልል ውጭ፣

ለ.ማንኛውም በውል ሠንጠረዡ ውስጥ የተጠቀሰ ተሽከርካሪ በእሽቅድምድም፣ በእሽቅድምድም ሥፍራ አሽቀዳዳሚነት በፍጥነት ፍተሻ፣ በአስተማማኝነት ሙከራ ወይም ዋስትና የተሰጠው ተሽከርካሪ በሠንጠረዡ ውስጥ ከተገለፀው ውጭ ሌላ አገልግሎት የሚሰጥ ከሆነ፣
ሐ.የመድን ዋስትና የተሰጠውን ተሽከርካሪ የሚያሰክር መጠጥ ወይም አደንዛዥ ዕጽ ከወሰዱ በፃላ በማሽከርከር፣ ለደረሰ ማንኛውም አደጋ፣ ጥፋት፣ ጉዳት ወይም ኃላነፊት፤

2.ከማንኛውም ኮንትራት ወይም ስምምነት ለመነጨ ኃላፊነት፣
3.አሽከርካሪው ተሽከርካሪውን ለመንዳት የሚያስችል መንጃ ፈቃድ የሌለው ወይም መሰል ፈቃድ እንዳያገኝ ወይም እንዳይዝ የተከለከለ ከሆነ፣
4.በጎርፍ፣ በማዕበል፣ በእሳተ ገሞራ ፍንዳታ፣ በመሬት መንቀጥቀጥ ወይም በሌላ የተፈጥሮ መናወጥ ምክንያት በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ለማንኛውም ጥፋት ወይም ኃላፊነት መንስኤ ለሆነ ወይም አስተዋጽኦ ላደረገ፣
5.በእርስ በርስ ጦርነት፣ በሥልጣን ንጥቂያ፣ በረብሻ፣ በሥራ ማቆም አድማ፣ በብጥብጥ፣ በወታደራዊ ረብሻ ወይም በሕዝብ መነሳሳት ብጥብጥ፣ በአብዮት፣ በወታደራዊ ወይም አላግባብ ሥልጣን ንጥቂያ፣ እንዲሁም በከበባ ሁኔታ፣ በታጠቀ ወይም ባልታጠቀ የዝርፊያ ወይም የሽፍታ ድርጊት፣ የቅሚያ ድርጊት ወይም ማርሻል ሕግ እንዲታወጅ ወይም እንዲቆይ ምክንያት ለሆነ ድርጊት፣

6.በዚህ ውል ውስጥ ሽፋን ያልተሰጠውን ማንኛውንም ተጐታች ወይም ብልሽት ያጋጠመውን ተሽከርካሪ ሲጐትት የመድን ውል ዋስትና በተሰጠው ተሽከርካሪ ላይ ጥፋት ወይም ጉዳት ቢደርስ፣

7.መድን ገቢው እያወቀው ፍቃድ ሰጭው ባለሥልጣን በባለቤትነት ደብተሩ ላይ ከገለፀው የጭነት ልክ በላይ በመጫን ወይም በማስጨነቅ ወይም ከመቀመጫው ልክ በላይ የተሳፋሪዎች ቁጥር በመብዛቱ በውል ሠንጠረዡ ላይ የተገለፀው ተሽከርካሪ ለሚደርስበት ማንኛውም ጥፋት፣ ጉዳት ወይም ኃላፊነት፣

8.በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ መንስኤ ለሆነ ወይም አስተዋጽኦ ላደረገ በማንኛውም ንብረት ላይ ለደረሰ ጥፋት፣ ውድመት፣ ጉዳት ወይም በምንም አይነት ለደረሰ ማንኛውም ጥፋት ወይም ወጭ ወይም ማንኛውም የጥቅም እጦት ወይም ማንኛውም ሕጋዊ ኃላፊነት፣


ሀ.አዮናይዜሽን ጨረር ወይም ከማንኛውም ¾ኡ??ክሊየር ነዳጅ ብክለት ወይም ራዲዮ አክቲቭ ብክለት ወይም uኡ??ክሊየር ነዳጅ መቀጣጠል፣ ከማንኛውም ኡ??ክሊየር ዝቃጭ፣

ለ.ከማንኛውም የኡ??ክሊየር ፈንጅ ወይም ኡ??ክሊየር አካል የመነጨ ራዲዮ አክቲቪቲ፣ መርዛማ ፈንጅ ወይም ሌላ አደገኛ ፀባይ፣

9.በውል ሠንጠረዡ ውስጥ ከተጠቀሰው ተሽከርካሪ ጋር የተያያዘ ወይም የተሽከርካሪው አካል የሆነ ማሞቂያ ወይም የአየር ግፊት መሣሪያ በመፈንዳቱ ለሚከሰት ሞት ወይም አካል ጉዳት ወይም የንብረት ውድመት ወይም ዋስትና በተሰጠው ተሽከርካሪ ላይ ለሚደርስ ጉዳት፤


ጠቅላላ የሚሟሉ ሁኔታዎች

1.የመድን ገቢው ተግባር
መድን ገቢው ወይም የካሣ ጥያቄ የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው በዚህ ውል ውስጥ በተቀመጡ ማግለያ አንቀጾችና በሚሟሉ ሁኔታዎች ውስጥ የሚተገበሩና የተከለከሉ ሁኔታዎችን ማክበርና ማሟላት እንዲሁም በውል መጠየቂያው ወይም በአደጋ ማሳወቂያ ቅጽ ላይ የተሰጡት ቃሎችና መልሶች እውነት መሆን ድርጅቱ ማንኛውንም ኃላፊነት ወስዶ በውሉ መሠረት ክፍያ ከመፈፀሙ በፊት ሊሟሉ የሚገባቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡

2.ስለተሽከርካሪ ደህንነት /ጥበቃ/
መድን ገቢው፣ የእሱ ሠራተኛ ወይም ማንኛውም የተፈቀደለት ሹፌር ወይም ዋስትና ለተሰጠው ተሽከርካሪ ኃላፊ የሆነ ማንኛውም ሰው፣ ተሽከርካሪውን ከጥፋት ወይም ከጉዳት መጠበቅና እንዲሁም ዋስትና የተሰጠው ተሽከርካሪ ተግባሩን ለማከናወን ብቁ እንዲሆን ተገቢውን እርምጃ ሁሉ ይወስዳሉ፡፡ ድርጅቱ በማንኛውም ጊዜ ተሽከርካሪውን ወይም ማንኛውንም አካል ወይም የመድን ገቢውን ማንኛውንም ሹፌር ወይም ሠራተኛ በማንኛውም ጊዜ ለመመርመር ነፃና ሙሉ መብት አለው፡፡ በአደጋ ወይም በብልሽት ወቅት ዋስትና የተሰጠው ተሽከርካሪ ተጨማሪ ጥፋት ወይም ጉዳት እንዳይደርስበት ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል፡፡ ተሽከርካሪው ተገቢው ጥገና ሳይደረግለት በመነዳቱ ለሚደርስበት ማንኛውም ተጨማሪ ጉዳት ወይም ሌላ አደጋ ድርጅቱ ሽፋን አይሰጥም፡፡

3.ማጭበርበር
አንድ የካሣ ጥያቄ በማንኛውም መንገድ የተጭበረበረ ከሆነ፤ እንዲሁም ዋስትና የተሰጠው ተሽከርካሪ ዋጋ የተጋነነ ከሆነ ወይም በውሉ መሠረት ጥቅም ለማግኘት መድን ገቢው ወይም በእሱ ምትክ ማንኛውም ሰው በተጭበረበረ መንገድ ከተጠቀመ ወይም መድን ገቢው ሆን ብሎ ወይም ከሌላ ወገን ጋር በመመሳጠር ዋስትና በተሰጠው ተሽከርካሪ ላይ ጥፋት ወይም ጉዳት ካደረሰ ውሉ የሚያስገኛቸው ጥቅሞች በሙሉ ይሠረዛሉ፡፡

4.አደጋን ስለማሳወቅ
ማንኛውም አደጋ ጥፋት ወይም ጉዳት እንደተከሰተ ወዲያውኑ ለድርጅቱ በጽሑፍ ማሳወቅ ያስፈልጋል፡፡ በማንኛውም የካሣ ጥያቄ ወቅት ማንኛውንም ደብዳቤ፣ የካሣ ጥያቄ፣ ትዕዛዝ፣ መጥሪያ ወይም ሂደት መድን ገቢው እንደደረሰው ወዲያውኑ ለድርጅቱ ማስተላለፍ ይገባዋል፡፡ በዚህ ውል አማካኝነት ካሣ የሚያስጠይቅ የክስ ጉዳይ በሂደት ላይ መሆኑን መድን ገቢው እንዳወቀ ለድርጅቱ በጽሑፍ ወዲያውኑ ያሳውቃል፡፡ በዚህ ውል መሠረት ካሣ ሊያስጠይቅ የሚችል ስርቆት ወይም ሌላ የወንጀል ሥራ ከተከናወነ መድን ገቢው ለፖሊስ ወዲያውኑ ያሳውቃል፡፡ አጥፊውም እንዲቀጣ ለድርጅቱ ትብብር ያደርጋል፡፡

5.ስለ ካሣ ሂደት/የመዳረግ መብት
መድን ገቢው ወይም የካሣ ጥያቄ የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው ከድርጅቱ የጽሑፍ ማረጋገጫ ከማግኘቱ በፊት ክፍያዎችን ማመን፣ ማዘጋጀት፣ቃል መግባት ወይም መፈፀም አይችልም፡፡ ድርጅቱ ከፈለገ በራሱ ስም ማንኛውንም የካሣ ጥያቄ መከታተል፣ በፍትሐብሄር ጉዳዮች ወይም በድርድሮች መከራከር እና ክፍያ መፈፀም ወይም በራሱ ስም በማንኛውም የካሣ ጥያቄ ወይም ጉዳት ወይም በሌላ ሦሥተኛ ወገን ላይ ለራሱ ጥቅም ሲል ክስ መመስረት ይችላል፡፡ በተጨማሪም ማንኛውንም የክስ ሂደት መከታተልና ማንኛውንም የካሣ ክፍያ የመፈፀም ሙሉ ሥልጣን ያለው ሲሆን እንደ ድርጅቱ ጥያቄ ማንኛውንም መረጃና እገዛ መድን ገቢው ይሰጣል፡፡

6.ሌላ የመድን ዋስትና ስለመኖር
በዚህ ውል መሠረት ማንኛውም የካሣ ጥያቄ ሲቀርብ ሌላ ዋስትና ሰጪ ድርጅት ይህንኑ ጥፋት፣ ጉዳት ወይም ኃላፊነት ሸፍኖ ከተገኘ፣ ድርጅቱ ለማንኛውም ጥፋት፣ ጉዳት ማካካሻዎችና የካሣ ወጪዎች በስሌት የሚደርስበትን ከመሸፈን በስተቀር ከዚያ በላይ የመክፈል ወይም የማዋጣት ኃላፊነት አይኖርበትም፡፡

7.ውል ስለመሰረዝ
በሚታወቀው አድራሻው መሠረት ለመድን ገቢው በተመዘገበ ደብዳቤ አማካኝነት ድርጅቱ ውሉን እንደሚሰርዝ የአሥራ አምስት ቀናት ማስጠንቀቂያ መስጠት ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ውሉ ለሰራበት ወቅት መቶኛውን በማስቀረት ልዩነቱን ድርጅቱ ለመድን ገቢው ይከፍላል፡፡ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ በመስጠት መድን ገቢውም ውሉን በማንኛውም ጊዜ መሠረዝ ይችላል፡፡ በዚህ መሠረት በውል ዘመኑ ውስጥ የካሣ ክፍያ እስካልቀረበ ድረስ ውሉ ለሠራበት ወቅት በድርጅቱ የአጭር ጊዜ ሂሳብ ማስያ መሠረት አረቦኑን ቀንሶ ልዩነቱን ለመድን ገቢው ይከፍላል፡፡

8.ስለ ግልግል
ኃላፊነት መኖሩ ከታመነ በኋላ በኋላ በፖሊሲው መሠረት ሊከፈል በሚገባው የካሣ መጠን ላይ ልዩነት ከተፈጠረ፣ አለመግባባቱ በሁለቱም ወገኖች በፅሑፍ በሚሾም አንድ አስታራቂ ውሣኔ እንዲሰጥበት ይደረጋል፡፡ በዚህ ላይ ልዩነት ከተፈጠረ ወይም በአንድ ላይ ስምምነት መድረስ ካልተቻለ አንደኛው ወገን ለሌላኛው ወገን ባሳወቀው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ የየራሱን አንድ አንድ አስታራቂ መርጦ በፅሑፍ ያሳውቃል፡፡ ሁለቱም ወገኖች ሰብሳቢ የሚሆነውን ሰው ለመምረጥ ስምምነት ላይ መድረስ ካልቻሉ ከሁለቱ ወገን የተሾሙት አስታራቂዎች አንድ ላይ ሆነው ሰብሳቢ የሚሆነውን ሰው በፅሑፍ ይመርጣሉ፡፡ ሰብሳቢውም ከአስታራቂዎቹ ጋር በመቀመጥ ሽምግልናውን ይመራል፡፡ በኮርፖሬሽኑ ላይ ማንኛውንም ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ በቅድሚያ በሸምጋዮቹ የተሰጠ ውሣኔ ሊኖር ይገባል፡፡

9.ስለ መዋጮ
በዚህ ውል ውስጥ የተገለፀውና የመድን ዋስትና የተሰጠው ተሽከርካሪ ማንኛውም አካሉ ከጠፋ ወይም ከተጐዳ፣ እና በአዲስ ዕቃ ከተተካ ከአደጋ በፊት ለነበረው የተሽከርካሪ አካል እርጅና መድን ገቢው ተገቢውን መዋጮ የመክፈል ኃላፊነት አለበት፡፡

10.መተካት ሙሉ ውድመት
ውድመት ደርሶ ጥገና የሚካሄድ ከሆነ ወይም ተሽከርካሪው በጥገና በማይስተካከልበት ሁኔታ በመውደሙ ምክንያት የሙሉ ውድመት ክፍያ የሚከፈል ሆኖ ሲገኝ መድን ገቢው ምትክ የተደረገላቸውን አሮጌ የመለዋወጫ ዕቃዎች ወይም ሙሉ ውድመት የደረሰበትን ተሽከርካሪ ከሕጋዊ ሰነዶች፣ ከባለቤትነት መብቶችና ከሌሎች ሰነዶች ጋር በማድረግ ለድርጅቱ ያስረክባል፡፡ ድርጅቱ እነዚህን የመለዋወጫ ዕቃዎች ወይም ሙሉ ውድመት የደረሰባቸውን ተሽከርካሪዎች የራሱ የማድረግ፣ የመሸጥ እና የመለወጥ ሙሉ መብት አለው፡፡

11.አደጋ ከደረሰበት ቦታ ተሽከርካሪን ስለማንሣት
ድርጅቱ አደጋ ስለመድረሱ የፅሑፍ መረጃ እንደደረሰው ውድመት የደረሰበትን ተሽከርካሪ ከተጨማሪ ጉዳቶች ለመከላከል ከአደጋው ቦታ ያነሳል፡፡ ድርጅቱ ይህንን በማድረጉ ኃላፊነትን እንደተቀበለ ተደርጎ መታሰብ የለበትም፡፡ በኢንሹራንስ ፖሊሲው መሠረት ተጨማሪ ምርመራዎች ከተካሄዱ በኋላ የካሣ ክፍያ ጥያቄው ውድቅ ሊደረግ ይችላል፡፡ የካሣ ጥያቄው ውድቅ ከተደረገ ድርጅቱ ለጥበቃ እና ተሽከርካሪውን ለማንሣት ያወጣቸውን ወጪዎች መድን ገቢው ይተካለታል፡፡

ማሳሰቢያ፡-
ይህ ጽሑፍ ስለ የንግድ ተሽከርካሪ የመድን ዋስትና የቀረበ ማብራሪያ እንጂ በሕግ ፊት የሚፀና ውል አይደለም፡፡

   

Home  About Us Financial Indicator Life Insurance Non-Life Insurance Main Branch Forms Contact Us