የጋራ ቤት ተጠቃሚች ከዚህ በታች በተጠቀሱት የስጋት ዓይነቶች በቤቱ ላይ ጉዳት ቢደርስ ከፍተኛ ኪሳራ ሊያጋጥማቸው ይችላል፡፡ ይህ ኪሳራ በዚህ መድን ይካሳል፡፡
1. የዋስትናው ተጠቃሚች
ሀ. በማሕበር ተደራጅተው የጋራ ቤት የሚሠሩ ለ. ከመንግሥት የጋራ ቤት የሚገዙ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
2. ዋስትናው የሚሰጣቸው ጠቀሜታች የጋራ ቤት መድን ዋስትና ሶስት ክፍሎች አሉት፡ እነሱም
ክፍል 1 የሕንፃ መድን
ይህ ክፍል በሚከተሉት የአደጋ ሥጋቶች የተነሳ በሕንፃው ላይ ለሚደርሰው ጉዳት ሽፋን ይሰጣል፡፡
ሀ. በእሣት በመብረቅና በፍንዳታ
ለ. በተለያዩ አውሎነፋሶች፣ በጎርፍ፣ በመሬት መንቀጥቀጥ፣ በባሕር ወይም በውቅያኖስ ሞገድ፣ በውሃ ቧንቧ መፈንዳት፣ በተንኮል፣ በረብሻ፣ በዛፍ መውደቅ፣ በቴሌቪዥን አንቴናችና መሰል ተሰቃዮች መውደቅ፣ በእንስሳት ወይም በመኪና ግጭት በአውሮኘላን ወይም የአውሮኘላን ክፋይ ወድቆ በመከስከስ፣ በስርቆት
ሐ. ድንገተኛ የመስታወትና የመፀዳጃ ዕቃች መሰበር
መ. ድንገተኛ ለሕንፃው አገልግሎት የሚያቀርቡና በመድን ገቢው ኃላፊነት ሥር ያሉ በመሬት ውስጥ የተቀበሩ እንደ ቧንቧና መሰል መስመሮች ጉዳት
ማግለያች በሚከተሉት አኳኋን በሕንፃው ላይ ጉዳት ቢደርስ ይህ ዋስትና ሽፋን አይሰጥም፣
1. በመበስበስ፣ ህንፃው በተገነባበት መሬት መስመጥ ወይም ወጣገባ መሆን ወይም መንሸራተት፣
2. ከሕንፃው ጋር ጉዳት ሲደርስ አብሮ ካልሆነ በቀር በአጥሮችና በበሮች ላይ የሚደርስ ጉዳት፣
3. የጋራ መኖሪያ ቤቱ በተከታታይ ለ 3ዐ ቀናት በነዋሪች ካልተያዘ
4. በሕዝባዊ አመፅ
5. በለማዳ እንስሳት አማካይነት ለሚደርስ ጉዳት
6. በሳተላይት ቴሌቪዢን መሣሪያች፣ የውጭ የራዲዮና ቴሌቪዥን አንቴና፣ በአንቴናው ላይ የሚገጠሙ ዕቃችና ሌሎች ውጭ የሚተከሉ አንደ በፀሐይ ውኃ ለማሞቅ የሚያገለግሉ ዕቃች ወ.ዘ.ተ ላይ ለሚደርስ ጉዳት፣
7. በሰው ሰራሽ የመሬት አቀማመጥ፣ በዛፎችና መሰል ዕፅዋት፣ በቅርፃቅርጽ እና በመዋኛ ገንዳ ሽፋኖች ላይ ለሚደርስ ጉዳት፣
8. በራዲዮ አክቲቭ ብክለትና ተዛማጅ ክስተቶች፣ በጦርነትና መሠል ክስተቶች፣ በሽብርተኝነት፣ በከፍተኛ ፍጥነት ከሚጓዙ አውሮኘላኖችና ሌሎች በአየር ላይ ተንሳፋፊ መሣሪያች ከሚመነጭ ከፍተኛ ድምፅ በሚፈጠር የግፊት ሞገድ ምክንያት የሚደርስ ጉዳት
ክፍል 2 የንብረት መድን
የጋራ ቤት ተጠቃሚች የጋራ ንብረት ላይ በክፍል 1 በፊደል ተራ ሀ እና ለ ሥር በተጠቀሱት ሥጋቶች ጉዳት ሲደርስ ውል ገቢው በዚህ መድን ሊካስ ይችላል፡፡ የጋራ ንብረት ማለት የጋራ መጠቀሚያ ቦታች ላይ ለምሳሌ እንደ የጋራ ቢሮ ውስጥ ያሉ ቁሳቁሶችን ምንጣፎችን ወ.ዘ.ተ እና በመድን ገቢው ኃላፊነት ሥር ያሉ ንብረቶችን ማለት ነው፡፡
ማግለያች
በሚከተለው አኳኋን በጋራ ንብረት ላይ ለሚደርስ ጉዳት ይህ ዋስትና ሽፋን አይሰጥም፣
1. ለተሽከርካሪች፣ ለአትክልት ሥፍራ ማስዋብያ ከሚያገለግሉት በስተቀር ተንቀሳቃሽ ቤቶች ተጎታች አውሮኘላኖች ሌሎች ተንሳፋፊ መሳሪያች፣ ጀልባች እና በእነሱ ላይ የሚገጠሙ ቁሳቁሶች
2. ከቤት ውጭ የሚገኙ ንብረቶች፣ ለማዳ እንስሳት፣
3. ለግለሰብ አልባሳት፣ ገንዘብ፣ የተለያዩ የመገበያያ ሠነዶች
4. የሳተላይት ቴሌቪዥን መሣሪያች፣ የራዲዮ ቴሌቪዥን አንቴና፣ በአንቴናው ላይ የሚገጠሙ ዕቃችና ሌሎች ከቤት ውጭ የሚተከሉ እንደ በፀሐይ ውሃ ለማሞቅ የሚያገለግሉ ዕቃች ወ.ዘ.ተ እንዲሁም በሰው ሰራሽ የመሬት አቀማመጥ፣ በዛፎችና መሠል እፅዋት፣ በቅርፃቅርፅ እና በመዋኛ ገንዳ ሽፋኖች ላይ ለሚደርስ ጉዳት፣
5. ሕንፃው በተገነባበት ወይም በሕንፃው ይዞታ መሬት መስመጥ፣ ማበጥ ወይም መንሸራተት ለሚደርስ ጉዳት፣
6. በሕዝባዊ አመፅ ለሚደርስ ጉዳት፣
7. በሕንፃው ነዋሪና ቤተሰቡ ለሚደርስ ጉዳት፣
8. ሕንፃው ለተከታከይ 3ዐ ቀናት በነዋሪች ሳይያዝ በመቅረት ለሚደርስ ጉዳት፣
9. ያለ ኃይልና ሠብሮ መግባት ወይም መውጣት ለተፈፀመ ስርቆት፣
10. በለማዳ እንስሳት አማካይነት ለሚደርስ ጉዳት፣
11. በራዲዮ አክቲቭ ብክለትና ተዛማጅ ክስተቶች፣ በጦርነትና መሠል ክስተቶች፣ በሽብርተኝነት፣ በከፍተኛ ፍጥነት ከሚጓዙ አውሮኘላኖችና ሌሎች በአየር ላይ ተንሳፋፊ መሣሪያች ከሚመነጭ ከፍተኛ ድምፅ በሚፈጠር የግፊት ሞገድ ምክንያት የሚደርስ ጉዳት
ክፍል 3 የሶስተኛ ወገን ኃላፊነት
በዚህ ክፍል የጋራ ቤት ተጠቃሚች ከጋራ ቤቱ ጋር በተያያዘ በሶስተኛ ወገን ላይ ድንገተኛ የአካል ጉዳት ቢደርስ እንዲሁም በሶስተኛ ወገን ንብረት ላይ ለሚደርስ ጉዳት ሃላፊነት ሽፋን ይሰጣል፡፡
ማግለያች
ይህ ዋስትና በሚከተሉት ስጋቶች ምክንያት ለሚደርስ ጉዳት ሸፋን አይሰጥም፣
1. በመድን ገቢው ንብረት በሆነ ተሽከርካሪ፣ በተንቀሳቃሽ ቤት'በአውሮኘላን" ሌሎች በአየር እና ውኃ ላይ ተንሳፋፊ መሳሪያች ምክንያት ለሚደርስ ጉዳት፣
2. በመድን ገቢው ሠራተኛ ላይ ለሚደርስ ጉዳት፣
3. ማንኛውም ከውል የመነጨ ሀላፊነት፣
4. በመበከል የሚደርስ ጉዳት፣
5. በአስቤስቶስ ጎጂ ተፈጥሮ የሚደርስ ጉዳት፣
6. በራዲዮ አክቲቭ ብክለትና ተዛማጅ ክስተቶች፣ በጦርነትና መሠል ክስተቶች፣ በሽብርተኝነት፣ በከፍተኛ ፍጥነት ከሚጓዙ አውሮኘላኖችና ሌሎች በአየር ላይ ተንሳፋፊ መሣሪያች ከሚመነጭ ከፍተኛ ድምፅ በሚፈጠር የግፊት ሞገድ ምክንያት የሚደርስ ጉዳት
1. የሚሟሉ ሁኔታች
1. መድን ገቢው መድን ለተገባለት ንብረት ደህንነት ተገቢውን ጥንቃቄና ክትትል እንክብካቤ ማድረግ ይኖርበታል፣
2. መድን ሰጪው መድን የተገባለትን ንብረት የማየትና የመጐብኘት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
3. በዚህ ውል መሠረት የካሣ ጥያቄ የሚያስነሳ ወይም ሊያስነሳ የሚችል ማንኛውም ሁኔታ ቢከሰት መድን ገቢው፣
ሀ. ንብረቱ ሙሉ በሙሉ በአደጋው እንዳይወድም ጉዳቱን ለማቆም ወይም ለመቀነስ አፋጣኝ እርምጃ ይወስዳል፡፡
ለ. በንብረቱ ላይ ለደረሰ ጉዳት ወይም ውድመት ኃላፊነት ያለበት አካል ካለ ኃላፊነቱን እንዲወስዱና ሰርቬይ እንዲያደርጉ ዕድል ለመስጠት እንዲያመች በአፋጣኝ ያሳውቃል፡፡
ሐ. ውድመት ወይም ጉዳት በደረሰበት ጊዜ የአደጋውን ቀን በመጥቀስ ለመድን ሰጪው ወዲያውኑ ያሳውቃል፡፡
4. በዚህ ውል መሠረት ማንኛውም የካሣ ጥያቄ በሚነሳበት ጊዜ ያንኑ ተመሣሣይ ጥፋት ወይም ጉዳት የሚሽፍን ሌላ የመድን ዋስትና ቢኖር በዚህ ዋስትና የካሳ ክፍያ የሚፈፀመው ይህ የመድን ዋስትና እንደሌለ ተቆጥሮ የጉዳቱ መጠን ሌላው የመድን ዋስትና ሊከፍል ከሚገባው በላይ ከሆነ ብቻ ነው፡፡
5. አለአግባብ የካሣ ክፍያ ለማግኘት ሲባል በመድን ገቢው ወይም በሱ ምትክ ማንኛውም ሰው የማጭበርበር መንገድ ቢጠቀም የዚህ ውል ጥቅም ውድቅ ይሆናል፡፡
6. ድርጅቱ በመጨረሻ ጊዜ በሚታወቅ አድራሻ የ15 ቀን የፅሑፍ ማስታወቂያ በተመዘገበ ደብዳቤ ለመድን ገቢው በመላክ ውሉን ሊሰርዘው ይችላል፡፡ እናም አረቦኑ ውሉ ፀንቶ የቆየበትን ጊዜ በማሰብ ተቀንሶ ለመድን ገቢው ይመለስለታል፡፡ ውሉ በማንኛውም ጊዜ በመድን ገቢው የፅሑፍ ማስታወቂያ በመስጠት መሠረዝ ይችላል፡፡ በውሉ የጊዜ ገደብ ውስጥ የካሣ ጥያቄ ካልቀረበ ውሉ ፀንቶ ለቆየበት ጊዜ በድርጅቱ የአጭር ጊዜ የአረቦን ስሌት መሠረት አረቦኑን ቀንሶ ልዩነቱን ለመድን ገቢው ተመላሽ ያደርግለታል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ይህ ፅሑፍ ስለ የጋራ ቤት መድን ኃላፊነት የመድን ዋስትና የቀረበ ማብራሪያ እንጂ በሕግ ፊት የሚፀና ውል አይደለም፡፡ |