ቢኖሩ ለራራስዎ መጦሪያ ቢሞቱ ለቤተሰብዎ መርጃ የሚጠቅም ዋስትና ‹‹ኢንዳውመንት›› መድን ነው፡፡ ይህ መድን ለተወሰነ የውል ዘመንና ለተወሰነ ገንዘብ ልክ የሚገባ ዋስትና ነው፡፡
• በወጣትነት ዘመን ገቢ በሚገኝበት ጊዜ ከገቢ በጥቂቱ በማጠራቀም ከተወሰነ ዘመን በኋላ በአንድ ጊዜ ለመውሰድ ወይም ያለ ምንም ተጨማሪ ክፍያ እስከ ሕይወት ዘመን ፍፃሜ ድረስ የማያቋርጥ መጦሪያ ያስገኛል፡፡ • ውሉ ተገዝቶ ከውሉ ፍፃሜ ቀን በፊት በሞት ቢለዩ ጠቅላላ የዋስትናውን ገንዘብ በስም ተጠቃሽ ወይም ለሕጋዊ ወራራሾች ተከፋይ እንዲሆን ያደርጋል፡፡
• ከሁለት ዓመት ላላነሰ ጊዜ አረቦኑ ከተከፈለ በየጊዜው ለሚያጋጥም ችግር ማቃለያ የሚውል ውሉ ካፈራራው ገንዘብ ላይ ተመጣጣኝ ብድር ያስገኛል፡፡ በዚህ መልኩ የተወሰደውን ብድር የውሉ ባለቤት ለመመለስ ወይም ለማስቀረት የራራሳቸውን ምርጫ መውሰድ ይችላሉ፡፡ ስለሆነም ‹‹ኢንዳውመንት›› ዋስትና ዓይነተኛ የገንዘብ ማጠራቀሚያ ዘዴ ነው፡፡
ኢንዳውመንት ዋስትና በቡድንም የሚሰጥ የዋስትና ዓይነት ሲሆን ከግል ኢንዳውመንት የሚለየው በዋናነት ለሁሉም የቡድን አባላት የሚያገለግል አንድ ዋና ዋስትና (master policy) ይሰጣል፡፡ ሌላው የቡድን ዋስትና ገንዘብ ማፍራት (cash value) የሚጀምረው ዋስትናው ከተገዛ ከሦስት ዓመታት በኋላ መሆኑ ነው፡፡
|