About Us Financial Service Publication Branches News Forms Contact Us Articles FAQ
 

Side Menu



Proposal Forms
-----------------------
Proposal With Medical Certificate
Proposal Without  Medical Certificate
Proposal for Medical Insurance 

Claim Forms 
------------------------
Medical Claim Notification
Accident and Disease Notification
Medical Attendance Certificate
Death Confirmation Form

 
ኢንዳውመንት አኒዩቲ

ኢንዳውመንት አኒዩቲ የሕይወት ዋስትና እንዲኖራቸው የሚሹ ደንበኛ የመጦሪያ ዕድሜያቸውን ከ55 ዓመት፣ ከ6ዐ ዓመት ወይም ከ65ኛው ዓመት ጀምሮ እንዲሆን እንደምርጫቸው በቅድሚያ በመለየትና የዋስትና መጠኑን በመወሰን ከኢትዮጵያ መድን ድርጅት ጋር ውል ይዋዋላሉ፡፡ የኢንዳውመንት አኒዩቲ ተጠቃሚ ለመሆን ቢያንስ የጡረታ ዕድሜ አሥር ዓመት ሲቀር ዋስትናውን መግዛት ያስፈልጋል፡፡

የውሉ ባለቤት ከመጦሪያ ዕድሜአቸው በፊት ከዚህ ዓለም በሞት ቢለዩ የዋስትና መጠኑን ወይም ዋስትናው ያፈራውን ጥሬ ገንዘብ (cash value) ከሁለቱ ብልጫ ያለው ክፍያ ለወራሾች ይከፈላል፡፡ 

የውሉ ባለቤት በተመረጠው የመጦሪያ ዕድሜ ላይ በሕይወት ከደረሱ የክፍያ ሥርዓቱ በሚከተሉት አማራጮች የሚስተናገድ ይሆናል፡፡

ለምሣሌ የውሉ ባለቤት ከ6ዐኛው ዓመታቸው ጀምሮ ለመጦር ቢፈልጉና የዋስትናው መጠን ብር 40‚000 አርባ ሺህ ብር ቢሆን፣

አማራጭ 1

የውሉ ባለቤት በየወሩ የጡረታ ክፍያ መውሰድ ምርጫቸው ከሆነ በየወሩ ብር 4ዐዐ አራት መቶ ብር የጡረታ አበል እየተከፈላቸው ቢያንስ ለ12ዐ ወራት አሥር ዓመት ይጦራሉ፡፡ ይህ ክፍያ በህይወት እስከአሉ ድረስ የሚቀጥል ሲሆን ከመጦሪያ ዕድሜአቸው ጀምሮ ከ12ዐ ወራት ላነሰ ጊዜ በሕይወት ከቆዩ ግን የጡረታ አበል ያልተቀበሉባቸው ወራት ክፍያ ለወራሾች ተከፋይ ይሆናል፡፡

አማራጭ 2

የውሉ ባለቤት የጡረታ ዕድሜአቸው ሲደርስ የተወሰነ ጥቅል ክፍያ በአንድ ጊዜ መውሰድ ከፈለጉ ብር 68‚040 ስልሣ ስምንት ሺህ አርባ ብር የጡረታ አበል ይከፈላቸዋል፡፡ ከዚያ በኋላ ተጨማሪ ክፍያ ለውሉ ባለቤትም ሆነ ለወራሾች አይኖርም፡፡

አማራጭ 3

የውሉ ባለቤት የጡረታ ዕድሜአቸው ሲደርስ የተወሰነ ጥቅል ክፍያ በአንድ ጊዜ በመውሰድ ከዚያ በኋላ ቀሪውን በማንኛውም ጊዜ ከዚህ ዓለም በሞት ቢለዩ ለወራሾች የሞት ካሣ እንዲከፈል ከመረጡ፡-
 
2. የጡረታ ዕድሜአቸው ሲደርስ ብር 44‚440 አርባ አራት ሺህ አራት መቶ አርባ ብር ለውሉ ባለቤት ይከፈላል፡፡
3. ከጡረታ ዕድሜአቸው በኋላ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ ለወራሾቻቸው ብር 40‚000 አርባ ሺህ ብር ካሣ ይከፈላል፡፡


አማራጭ 4

የውሉ ባለቤት የጡረታ ዕድሜአቸው ከደረሰ በኋላ ምንም ዓይነት የጡረታ አበል በህይወት እያሉ የመቀበል ምርጫ ሳያደርጉ ከጡረታ ዕድሜአቸው በኋላ በማንኛውም ጊዜ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ ለወራሾቻቸው የሞት ካሣ እንዲከፈል ከመረጡ ብር 115‚360 አንድ መቶ አሥራ አምስት ሺህ ሦስት መቶ ስልሣ ብር ለወራሾች ተከፋይ ይሆናል፡፡

ከፍ ብሎ ከተጠቀሱት አማራጮች መካከል የውሉ ባለቤት አንደኛውን አማራጭ ብቻ ውሉን ሲዋዋሉ በቅድሚያ ያሳውቃሉ፡፡

 

   

Home  About Us Financial Indicator Life Insurance Non-Life Insurance Main Branch Forms Contact Us