About Us Financial Service Publication Branches News Forms Contact Us Articles FAQ
 

Side Menu



Proposal Forms
----------------------------
Motor Insurance
Fire Insurance
Personal Accident Insurance 
Workmens Compesation 
Burglarly and House Breaking
Contractors All Risk
Contractors Plant & Machinery
Deterioration of Stock
Electronic Equipment Insurance
Erection All Risk
Inland Carriers Liability
Machinary Loss of Profit
Machinary Insurance
Public Liability
Professional Indemenity
Product Liability 
Fidelity Guaranty
Money Insurance

Claim Notification Forms 
-----------------------------
Motor Insurance
Marine Insurance
Accedent and Disease

 
የእሳት ቃጠሎና የመብረቅ ዋስትና

መግቢያ

እሳት ለሰው ልጅ ኑሮ አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች አንዱ ቢሆንም በጥንቃቄ ጉድለት በሰው ልጅ ሕይወት፣ ሀብትና ንብረት ላይ የሚያደርሰው ጥፋት ከፍተኛ ነው፡፡ ይልቁንም ከሚሰጠው ጥቅም ጎን ለጎን የሚያደርሰው ጉዳትም ጨመረ ለማለት የሚቻልበት ደረጃ ላይ የደረስን ይመስላል፡፡

ከሐምሌ 1 ቀን 1999 ዓ.ም. እስከ መጋቢት 3ዐ ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ባሉት 9 ወራት በአዲስ አበባ ብቻ በእሳት አደጋ መከላከያና ማጥፊያ ብርጌድ የተመዘገቡ 375 የተለያዩ የቃጠሎ አደጋዎች ደርሰዋል፡፡ የደረሱት የቃጠሎ አደጋዎች መተኪያ የሌለውን የ7 ሰዎች ሕይወት ቀጥፈዋል፡፡ በ32 ሰዎች ላይም ቀላልና ከባድ የመቁሰል አደጋ አድርሰዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ግምቱ ብር 32,842,489 የሚሆን ንብረት ወድሟል፡፡

ከላይ ከተጠቀሱት 357 የቃጠሎ አደጋዎች ውስጥ 219 የቤት 22 የመኪና፣ 4ቱ የፋብሪካ 112ቱ ደግሞ በልዩ ልዩ ንብረቶች ላይ የደረሱ የቃጠሎ አደጋዎች ናቸው፡፡

ስለዚህ ይህን ድንገተኛ አደጋ መቋቋሚያው ዋነኛ መፍትሄ ከጥንቃቄ ባሻገር የእሳት ቃጠሎና የመብረቅ ዋስትና ከኢትዮጵያ መድን ድርጅት መግዛት ነው፡፡

የእሳት ቃጠሎና የመብረት ዋስትናንም ሆነ ሌሎች ድርጅታችን የሚሸጣቸውን የመድን ዓይነቶች በመግዛት ባልታሰበ ወቅትና ሁኔታ በሚመጣ አደጋ በብዙ ድካምና ውጣ ውረድ ያገኙት ንብረት ሲጠፋ ቀኑ እንዳይጨልም ዙሪያው ገደል እንዳይሆን ማድረግ ይቻላል፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ስለእሳት ቃጠሎና የመብረቅ ዋስትና የሚያብራራ አጭር መግለጫ እነሆ ይላል፡፡

እሳት ምንድነው?

እሳት ሦስት ነገሮች አንድ ላይ ተገኝተው መስተጋብር ሲፈጥሩ የሚገኝ ውጤት ነው፡፡ እነዚህ የእሳት ሦስት ጎኖች (triangle) የሚባሉትና ለእሳት መፈጠር ምክንያት የሚሆኑት ነገሮች፡-

ሀ. ነዳጅ
ለ. ሙቀትና
ሐ. ኦክስጅን ናቸው፡፡

እሳት በነዳጅ፣ በሙቀትና በኦክስጅን አንድ ላይ መሆን የሚፈጠር ነው ስንል ከነዚህ ነገሮች አንዱ ቢጎድል እሳት አይፈጠርም ማለታችን ነው፡፡ እሳትን ማጥፋት ማለት እሳት እንዲፈጠር ከሚያደርጉት ከነዚህ ሦስት ነገሮች አንዱን ማስወገድ ወይም ሁለቱን መለየት ማለት ነው፡፡

የዋስትናው ምንነትና የሚሰጠው ሽፋን

የእሳት ቃጠሎና የመብረቅ ዋስትና በእሳት ወይም በመብረቅ ምክንያት በቀጥታ ለሚደርስ የንብረት ጥፋት ወይም ውድመት ለመድን ገቢው ካሣ የሚያስገኝ ዋስትና ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ዋስትናው በቤት ውስጥ ግልጋሎት ላይ በሚውል ቡታ ጋዝና ማሞቂያ ፍንዳታ የተነሣ የሚደርስ ጉዳትንም ይሸፍናል፡፡

ከእሳት ቃጠሎና ከመብረቅ ዋስትና አንፃር እሳት ተፈጠረ የሚባለው የሚከተሉት ሦስት ዋና ዋና ሁኔታዎች ሲሟሉ ነው፡፡


ሀ. በትክክል ወይም በእርግጥ የተፈጠረ ቃጠሎ መኖር፣

ለ. አንድ በእሳት መቃጠል የሌለበት ግን የተቃጠለ ነገር መኖር፣
ሐ. እሳቱ በአደጋ ወይም በአጋጣሚ የተፈጠረ ማለትም ሆን ተብሎ ለተፈጠረ የአሳት አደጋ ዋስትናው ሽፋን አይሰጥም፡፡ ነገር ግን በቸልተኝነት ለተፈጠረ አደጋ ሽፋን ይሰጣል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ጉዳቶች በዋስትናው ይሸፈናሉ፡፡

¨በቃጠሎው ምክንያት በሚፈጠረው ጭስ ለሚጎዱ ንብረቶች፣
¨እሳቱን ለማጥፋት በሚደረግ ጥረት አገልግሎት ላይ በዋለ ውኃ ወይም ሌላ የእሳት ማጥፊያ ምክንያትነት በንብረት ላይ ለደረሰ ጥፋት፣
¨እሳቱ እንዳይስፋፋ ለመቆጣጠር ሆን ተብሎ እንዲወድሙ ለተደረጉ ንብረቶች፣
¨ውል ገቢው እሳቱን ለመቆጣጠር ወይም ንብረት ለማዳን በሚያደርገው ሙከራ የተነሣ ከሚከሰት ጉዳት ይህም ማለት በእሳት ከተያያዘው ቤት ውስጥ በወጣ ንብረት ላይ በዝናብ የተነሣ ወይም ንብረቱ በሚወጣበት ጊዜ በተለያየ ምክንያት የሚደርሰውን ጉዳት ይሸፍናል፡፡

ነገር ግን ውል ገቢው ወዲያውኑ ለንብረቶቹ መደረግ የሚገባውን ጥንቃቄ ሁሉ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

ለእንደዚህ ዓይነት ጉዳቶች ዋስትናው ሽፋን የሚሰጠው ጉዳቶቹ የተከሰቱት ውል ተቀባዩ የሚደርሰውን ጥፋት ለመቀነስ ጥረት በሚያደርግበት ወቅት በመሆኑና እሳቱ ለደረሰው ጉዳት ቀጥተኛ መንስዔ በመሆኑ ነው፡፡

ነገር ግን ሽፋን ሰጪው የመድን ድርጅት


ሀ. እሳቱ የተነሣው በተገለለ የአደጋ መንስዔ መሆኑን ማረጋገጥ ከቻለ

ለ. የእሳት አደጋው መነሾ ውል ተቀባዩ ሆን ብሎ እንዲፈጠር ያደረገው መሆኑን ማረጋገጥ ወይም ተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ ከቻለ ውል ገቢው የካሣ ክፍያ አያገኝም፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በራሱ ውስጣዊ የመብላላት ወይም ሙቀት የመፍጠር ሁኔታ የተነሣ ለሚከሰት የእሳት አደጋ ዋስትናው ክፍያ አይፈፅምም፡፡ የሚከተለው ምሣሌ ይህን የበለጠ ግልፅ ያደርገዋል፡፡

ምሣሌ
የሣር ክምር በራሱ ሙቀት ቃጠሎ መፍጠር ይችላል፡፡ በሣሩ ክምር ላይ የሚደርስን የእሳት አደጋ ዋስትናው አይሸፍንም፡፡ ነገር ግን እሳቱ ተዛምቶ ሌላ የእሳት አደጋ ከፈጠረ አደጋው ሽፋን ይኖረዋል፡፡ የመጀመያው አደጋ የማይሸፈነው በተገለለ የአደጋ መንስዔነት የተፈጠረ በመሆኑና የተገለለው የአደጋ መንስዔ የጉዳቱ ቀጥተኛ ምክንያት ስለሆነ ለውል ተቀባዩ ካሣ አይከፈለውም፡፡

ዋስትና የሚገባለት ንብረት

የእሳት ቃጠሎና የመብረቅ ዋስትና ሊገባላቸው የሚችሉት የንብረት ዓይነቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

¨የመኖሪያ ቤቶችና ሕንፃዎች ቢሮዎች፣ሆስ፡??ሎች፣መጋዘኖች፣ ፋብሪካዎች ወዘተ፣
¨ከላይ በተጠቀሱት ቤቶች ወይም ሕንፃዎች ውስጥ ወይም ግድግዳዎች ላይ ለሚገኙ የሥራ ማከናወኛ መሣሪያዎች፣ ቁሳቁሶችና መገልገያ ዕቃዎች፣
¨በመጋዘን የተከማቸ የአምራች ወይም የቸርቻሪ ዕቃ፣


በተጨማሪ የአረቦን ክፍያ የሚካተቱ አደጋዎች

በተጨማሪ የአረቦን ክፍያ የእሳት ቃጠሎና የመብረቅ ዋስትና የሚከተሉትን የአደጋ መንስዔዎች እንዲያጠቃልል ማድረግ ይቻላል፡፡


ሀ. በኬሚካል የተነሣ ለሚደርሱ የአደጋ ዓይነቶች፡-
በኬሚካሎች የተነሣ ለሚደርስ ፍንዳታ፣ ውስጥ ለውስጥ በመብላላት ወይም በሙቀት ለሚከሰት እሳት በተጨማሪ አረቦን ዋስትና ሊገባላቸው ይችላል፡፡ ቦይለሮች ወይም ማሞቂያዎች ላይ የሚደርስ የፍንዳታ አደጋ የበለጠ አመቺ የሚሆነው በኢንጂነሪንግ ዋስትና ውስጥ ቢካተት በመሆኑ በእሳትና በመብረቅ ለሚደርስ አደጋ በተዘጋጀው የመድን ዋስትና ውስጥ አይሸፈንም፡፡ ሆኖም በቀለም ፋብሪካዎች ውስጥ በሚገኙ ተቀጣጣይነትና የመትነን ባህሪይ ባላቸው ኬሚካሎች የተነሣ ለሚደርስ የፍንዳታ አደጋ፣ በዘይት መጭመቂያዎች፣ በጫማ ፋብሪካዎችና የእህል ጎተራዎች (silos) እና በመሳሰሉት ላይ የሚደርሱ አደጋዎች ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡

ለ. ማህበራዊ አደጋዎች
በረብሻ፣ በህዝብ በሚነሱ ብጥብጦችና ሆን ተብለው በውል ገቢው ንብረት ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች፣ በተጨማሪ አረቦን በዚህ ዋስትና ሽፋን ያገኛሉ፡፡

ነገር ግን በዚህ በማህበራዊ አደጋዎች ውስጥ የሚከተሉት አይካተቱም፡፡ እነሱም፡-

1.በውርስ፣ ወይም በመንግሥት ትዕዛዝ የሚደርስ ጉዳት፣
2.ሥራ በማቋረጥ ምክንያት ለሚመጣ ጉዳት፣
3.በስርቆት ለሚደርስ ጉዳት፣
4.ሥራ ላይ ባልሆኑ ማለትም በባዶ ሕንፃዎች ላይ የሚደርስ ጉዳት ናቸው፡፡


ሐ. በተፈጥሮ የሚከሰቱ አደጋዎች፡-
በጎርፍ መጥለቅለቅ፣ በኃይለኛ ዝናብ (storm)' እና በመሬት መንቀጥቀጥና በመሬት መንሸራተት የሚከሰቱትን አደጋዎች ያካትታል፡፡ ነገር ግን ለጎርፍ አደጋ የቅርብም ሆነ የሩቅ መንስዔው ኃይለኛ ዝናብ መሆን ይኖርበታል፡፡ በመሆኑም የጎርፍ አደጋ ሽፋን የሚሰጠው ኃይለኛ ዝናብ ከሚያስከትለው አደጋ ጋር ተጣምሮ ነው፡፡ በእነዚህ የአደጋ መንስዔዎች ለሚደርስ ጉዳት ባለንብረቱ እስከተወሰነ የክፍያ መጠን ድረስ (Excess) እንዲከፍል ይደረጋል፡፡ ይህም የሚሆነው አነስተኛ የጥገና ወጪዎች በዋስትናው እንዳይሸፈኑ ለማድረግ ነው፡፡
መ. ልዩ ልዩ አደጋዎች፡-
ከእነዚህ በተጨማሪ አረቦን ከሚሸፈኑ አደጋዎች ውስጥ አንዱ ከውኃ ጋር በተያያዘ ማለትም ከውኃ ማጠራቀሚያ ወይም ቧንቧ የፈነዳ ውኃ የሚያስከትለው ጉዳት ወይም ለንግድ ሥራ ሲባል በሚደረግ የማቀዝቀዣ ሂደት ወይም እጥረት የተነሣ የሚደርስ ጉዳት ነው፡፡ ይሁንና ለባዶ ሕንፃ ወይም አገልግሎት ለማይሰጥ ሕንፃ ይህ ሽፋን አይሰጥም፡፡

ሌላው ተሽከርካሪዎች የድርጅቱን ግቢ ለቀው ሲወጡ ወይም ወደ ግቢው ሲገቡ በግድግዳዎች፣ በበሮችና በአጥሮች ላይ የሚያደርሱአቸው አደጋዎች ሲሆኑ እነዚህም በተጨማሪ አረቦን ይሸፈናሉ፡፡ ሆኖም በአሽከርካሪው ችሎታ ማነስ ምክንያት ለሚደርሱ አደጋዎች ሽፋን አይሰጥም፡፡ የራሱ የውል ገቢው ተሽከርካሪዎች ለሚያደርሱት ተመሳሳይ አደጋ ሽፋን የሚሰጥ ቢሆንም ለእያንዳንዱ አደጋ እስከ ተወሰነ የክፍያ መጠን ድረስ ውል ገቢው እንዲሸፍን ይደረጋል፡፡

ሌላው በልዩ ልዩ አደጋዎች ውስጥ የሚካተተው ዋስትና በተገባለት ንብረት ላይ አይሮኘላን ወይም የአይሮኘላን ከፊል አካል ወድቆ በመከስከሱ የተነሣ ለሚደርስ ጥፋት በተጨማሪ አረቦን የሚሰጥ ክፍያ ነው፡፡ ለደረሰው ጥፋት የአይሮኘላኑን ባለቤት መድን ሰጪው የመጠየቅ መብት አለው፡፡ ነገር ግን ጉዳት የደረሰው በአየር ግፊት (pressure wave) ወይም አይሮኘላኖች በሚፈጥሩት ሶኡ?? ባንግስ (sonic bangs) ምክንያት ከሆነ ይህ ዋስትና አይሰጥም፡፡

በውሉ የማይካተቱ የሽፋን ዓይነቶች

መደበኛው የእሣት ቃጠሎና የመብረቅ ዋስትና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚከተሉት አደጋዎች ሽፋን አይሰጥም፡፡

1.በሚከተሉት ክስተቶች ሰበብ ለሚደርሱት ጉዳዮች፣

ሀ. በትክክል ተለይቶና በዋስትናው ላይ ተጠቅሶ ውል እስካልተገባለት ድረስ በብጥብጥ ወይም በረብሻ ምክንያት ለሚደርሱ ጉዳቶች እና
ለ. በጦርነት፣ በወረራ፣ በውጭ ጠላት ጥቃት፣ በጥል፣ በእርስ በርስ ጦርነት፣ በአመፅ፣ በአብዮት፣ በሕዝባዊ እንቅስቃሴ፣ በወታደራዊ ወይም ለሥልጣን ሽኩቻ በሚፈጠር ረብሻ፣ በአሸባሪነት በሚቃጣ ርምጃና ሰበብ ምክንያት ለሚደርሱ ጉዳቶች በሙሉ ሽፋን አይሰጥም፡፡

2.በሚከተሉት ክስተቶች ማለትም፡-

ሀ. በአዮናይዜሽን ጨረር ንክኪ፣ በራዲዮ አክቲቭ ብክለት፣ በኡ??ክለር ነዳጅ ወይም ከኡ??ክለር በሚመነጭ ቆሻሻ ወዘተ
ለ. በሬዲዮ አክቲቭ መርዛማ ፈንጂዎች ወይም ሌሎች ጎጂነት ያላቸው ቁሳቁሶች ሰበብ ለሚደርሱት የንብረት ጥፋት፣ ውድመት ወይም ጉዳት ሊያስከትሉ ለሚችሉት ወጪዎች ሽፋን አይሰጥም፡፡
3.በአየር መበከልና በመመረዝ ሳቢያ ለሚደርሱ ጥፋቶች፣ ውድመቶችና ጉዳቶች፣ ነገር ግን ዋስትና የተገባለት ንብረት በሚከተሉት ሁኔታዎች ጉዳት ከደረሰበት ዋስትናው ሽፋን ይሰጣል፡፡

ሀ. ዋስትና በተገባለት አደጋ ምክንያት በተከሰተ የአየር ብክለትና መመረዝ ሳቢያ የሚፈጠሩ ጉዳቶችና፣

ለ. በውሉ ላይ በአየር ብክለትና መመረዝ ምክንያት ሊደርሱ ይችላሉ በሚል ሥጋት ቀደም ሲል ዋስትና በተሰጣቸው የአደጋ መንስዔዎች
4.ውል ገቢው ወይም ተወካዩ በተለየ ሁኔታ ሽፋን ለገዛላቸው ንብረቶች፣
5.በጥቅም እጦት ምክንያት ለሚደርስ ጉዳት ነገር ግን በኪራይ መቋረጥ የተነሣ ለሚደርስ የገቢ መቋረጥ በውሉ ላይ የተካተተ ከሆነ ሽፋን ይኖረዋል፡፡

ሊታወሱ የሚገባቸው ነጥቦች

1.አደጋ ከመድረሱ በፊት ያለው የአንድ ንብረት ግምት መጀመሪያ ዋስትና ከተገባለት ግምት በታች ሆኖ ከተገኘ ለጉዳቱ የሚከፈለው ክፍያ በዚያው መጠን ይቀንሳል፡፡
2.ዋስትና ስለሚገባለት ንብረት ውል ገቢው የተጭበረበረ ወይም የተምታታ መረጃ ቢሰጥ ወይም ውል ገቢው መግለፅ የሚገባውን ይፋ ከማድረግ ቢቆጠብ የመድን ውሉን መድን ሰጪው እንዲቋረጥ ማድረግ ይችላል፡፡
3.በውሉ ወቅት የተደረጉ ማናቸውም ገደቦች ወይም ግዳጆች ከዋስትናው ሰነድ ጋር አባሪ ከተደረጉበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ውሉ መጨረሻ ድረስ ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡
4.ውል ገቢው አደጋ እንዳይደርስ መደረግ የሚገባቸውን የቅድሚያ ጥንቃቄዎች ሁሉ ያደርጋል፡፡
5.ውል ገቢው ወይም ማንኛውም ተወካይ በተጭበረበረ መንገድ ወይም ሆን ተብሎ ለደረሰ ጉዳት የካሣ ክፍያ ለማግኘት ቢሞክሩ በዚህ ውል ሊያገኙ የሚችሉትን ማንኛውንም ጥቅም ያጣሉ፡፡
6.የመድን ውል ሰጭው በራሱ ምርጫ ጉዳቱ ለደረሰበት ንብረት ግምት በጥሬ ገንዘብ ከመክፈል ይልቅ ማደስ ወይም መተካት ይችላል፡፡ ”Åሁኔታ¨< ወይም በተገቢው መንገድ እስከተፈፀመ ድረስ ውል ሰጭው የሚታደሰውን ንብረት ልክ እንደነበረ የማደስ ግዴታ የለበትም፡፡ ማለትም ውል ሰጭው ዋስትና ከተሰጠው ገንዘብ መጠን በላይ ወጭ ለማድረግ አይገደድም፡፡
7.ዋስትና የተገባለት ንብረት አደጋ ደርሶበት የካሣ ክፍያ ጥያቄ ሲቀርብ መድን ሰጪው የሚከተሉት መብቶች ይኖሩታል፡፡
¨አደጋ ከደረሰበት ህንፃ ወይም ግቢ ወዲያውኑ የመግባትና ህንፃውን የመቆጣጠር፣
¨በህንፃው ውስጥ ያሉትን ንብረቶች የመያዝና አስፈላጊውን እንክብካቤ የማድረግ፣
¨ነገር ግን ይህንን ማድረጉ የካሣ ክፍያውን ጥያቄ እንደተቀበለ ተደርጎ ሊተረጎም አይችልም፡፡
8.ለአንድ ንብረት ሁለት ዋስትና የተገባ ከሆነ በአደጋው ምክንያት ለደረሰው ጥፋት፣ በሁለቱ ውል ሰጪዎች ተከፋይ የሚሆነው የጉዳት ካሣ ክፍያ ድርሻ በስሌት ይወሰናል፡፡
9.የካሣ ክፍያ ከተፈፀመ በኋላም ሆነ ከመፈፀሙ በፊት በዚህ ዋስትና መሠረት ውል ሰጪው ለአደጋው ተጠያቂ ነው ብሎ ያመነበትን ሦስተኛ ወገን ለአደጋው ካሣ እንዲከፍል ለማድረግ ወይም ሌሎች የድርጅቱን መብቶች ለማስከበር በሚያደርገው ጥረት ውል ገቢው ያለውን ሕጋዊ ኃላፊነት ለውል ሰጪው የማስተላለፍ፣ የመተባበርና የሚፈለግበትን ሁሉ ለመሥራት ፈቃደኛ መሆን ይጠበቅበታል፡፡
10.በዚህ የመድን ዋስትና አማካኝነት ለሚፈጠር ማንኛውም አለመግባባት ሁለቱ ወገኖች ለሚሰይሙት የግልግል ዳኛ ቀርቦ ጉዳዩ መታየት ይኖርበታል፡፡

የካሣ ክፍያ አፈፃፀምና ደንበኞች ማሟላት ስለሚገባቸው ጉዳዮች

ውል ገቢዎች አደጋ ሲደርስባቸው፡-

ሀ. አደጋ ስለመድረሱ በፍጥነት ለውል ሰጪው ማሳወቅ፣

ለ. አደጋው እንደደረሰ በአቅራቢያው ላለ የፖሊስ ኃይል ማሳወቅ፣
ሐ. ቃጠሎው ተጨማሪ ጥፋት እንዳያስከትል ውል ገቢው የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ እንዲሁም ሌሎች የቃጠሎውን ግስጋሴ ለመገደብ ለሚያደርጉት ጥረት ፈቃደኛ መሆን አለበት፡፡
መ. በራሣቸው ወጪም
¨በእሳት አደጋው የወደመውን ንብረት ዓይነትና የጉዳቱን መጠን በፅሑፍ ያቀርባሉ፡፡
¨ንብረቱ በሌላ የመድን ዋስትና የተሸፈነ ከሆነ ይህንኑ መግለፅ፣
¨ማንኛውንም ለካሣ ክፍያ አፈፃፀም ሂደት የሚጠቅሙ ማረጋገጫዎችና ዘገባዎችን መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ውል ሰጪው አደጋ መድረሱን እንዳሳወቀ ዋስትና ሰጪው የሚከተሉትን ሂደቶች ያከናውናል፡፡

1.ከአደጋው በፊት ውል መገባቱንና ለተጠቀሰው ንብረት ሽፋን መኖሩን ያረጋግጣል፡፡
2.አደጋውን ከቦታው ድረስ ተገኝቶ ያያል፡፡ ከውል ገቢውም ጋር በጉዳዩ ላይ ይነጋገራል፡፡ ጉዳዩ በእሳት አደጋ ባለሙያ መታየት የሚገባው መሆኑን ካመነበት አደጋውን የሚመረምር ባለሙያ ይልካል፡፡ ባለሙያው ስለደረሰው አደጋ ውል ገቢውን፣ ፖሊሶችን፣ የእሳት አደጋ ብርጌዶችንና ሌሎች እማኞችን ያነጋግራል፡፡ ከዚያም ስለግኝቶቹ ሪፖርት ያቀርባል፡፡
3.ለጥገና የሚያስፈልገውን ጠቅላላ ወጪ ያሰላል፡፡
4.የአደጋውን ቅሪት (salvage) ይሰበስባል፡፡ ውል ገቢው ቅሪቱን የሚፈልገው ከሆነ በዋጋ በመስማማት ሊሰጠው ይችላል፡፡


ማሳሰቢያ፡- ይህ ፅሑፍ ስለየእሳት ቃጠሎና የመብረቅ አደጋ ዋስትና የቀረበ ማብራሪያ እንጂ በሕግ ፊት የሚፀና ውል አይደለም፡፡

   

Home  About Us Financial Indicator Life Insurance Non-Life Insurance Main Branch Forms Contact Us