About Us Financial Service Publication Branches News Forms Contact Us Articles FAQ
 

Side Menu



Proposal Forms
----------------------------
Motor Insurance
Fire Insurance
Personal Accident Insurance 
Workmens Compesation 
Burglarly and House Breaking
Contractors All Risk
Contractors Plant & Machinery
Deterioration of Stock
Electronic Equipment Insurance
Erection All Risk
Inland Carriers Liability
Machinary Loss of Profit
Machinary Insurance
Public Liability
Professional Indemenity
Product Liability 
Fidelity Guaranty
Money Insurance

Claim Notification Forms 
-----------------------------
Motor Insurance
Marine Insurance
Accedent and Disease

 
የአበባ መድን

1.መግቢያ

በአሁኑ ወቅት በሀገራችን የአበባ አምራቾች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣበት ወቅት ነው፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ መድን ድርጅት የአበባ አምራቾችን ጥረት ለመደገፍ ያስችል ዘንድ ትክክለኛ የመድን ዋስትና በመቅረፅ ለገበያ አቅርቧል፡፡ የዚህ መድን ዋስትና ዓላማ በመጠለያ መዋቅሩና በውስጡ የተዘሩ አበባዎች ላይ በተፈጥሮም ሆነ በማሕበራዊ አደጋዎች መንስኤነት ለሚደርሱ ጉዳቶች ሽፋን መስጠት ነው፡፡

2.የዚህ ዋስትና ተጠቃሚ ሊሆኑ የሚችሉት

ሀ/በግል
ለ/በሽርክና
ሐ/በድርጅት የአበባ ምርት ሥራ ላይ የተሰማሩ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

3.ዋስትናው የሚሰጣቸው ጠቀሜታዎች

የአበባ ምርት ዋስትና አምስት ክፍሎች አሉት፡-

ክፍል 1 የመጠለያ መዋቅር

በመጠለያ መዋቅሩ ላይ በእሳት፣ በመብረቅ፣ በከፍተኛ ዝናብና አውሎ ንፋስ እንዲሁም በጎርፍ፣ ጉዳት ቢደርስባቸው ጉዳቱ በዚህ ክፍል ይሸፈናል፡፡ ከእነዚህ ስጋቶች በተጨማሪ መድን ገቢው ለሌሎች ስጋቶች ሽፋን መግዛት ከፈለገ ከመድን ሰጪው ጋር ተነጋግሮ ስምምነት ላይ መደረስ ይኖርበታል፡፡

ክፍል 2 የመዋቅሩ የኘላስቲክ ልባስ

ከላይ በክፍል 1 በተጠቀሱት የአደጋ ስጋቶች ምክንያት የኘላስቲክ ልባስ ላይ ለሚደርሰ ጉዳት ወይም ጥፋት ይህ ክፍል ሽፋን ይሰጣል፡፡

ለመዋቅሩ የኘላስቲክ ልባስ መድን ለመግዛት አስቀድሞ በክፍል አንድ ላይ ለተጠቀሰው ንብረት መድን መግዛት ያስፈልጋል፡፡

ክፍል 3 በመጠለያ ውስጥ የተዘሩ አበባዎች

በመጠለያ ውስጥ የተዘሩ አበባዎች ላይ በክፍል 1 ስር በተጠቀሱት የአደጋ ሥጋቶች ምክንያት ለሚደርስ ጉዳት ወይም ጥፋት ይህ ዋስትና ሽፋን ይሠጣል፡፡


በመጠለያ ውስጥ ለተዘሩት አበባዎች የመድን ዋስትና ለማግኘት አስቀድሞ ለመጠለያ መዋቅርና ለመዋቅሩ የኘላስቲክ ልባስ መድን መግዛት ያስፈልጋል፡፡


ክፍል 4 ማቀዝቀዣ ማሽነሪና ተዛማጅ መሳሪያዎች

ይህ ክፍል አበባ ከተመረተ በኋላ በኋላ ለገበያ ከመቅረቡ በፊት ወይም ወደሚላክበት አገር ከመሄዱ በፊት ሳይበላሽ እንዲቆይ የሚያደርጉ ማቀዝቀዣ መሳሪያዎች ሽፋን የሚያገኙበት ነው፡፡

በዚህ ክፍል ውስጥ የሚገኙ ንብረቶች በውሉ ውስጥ ከተጠቀሱት ማግለያዎች በስተቀር በሌላ በማንኛውም ድንገተኛና ያልተጠበቁ ሥጋቶች ጉዳት ቢደርስባቸው ጉዳቱ ወይም ጥፋቱ በዚህ ክፍል ይሸፈናል፡፡


ክፍል 5 በማቀዝቀዣ ክፍል የተቀመጡ አበባዎች

ይህ ክፍል በማቀዝቀዣ ክፍል የተከማቸ አበባ ሽፋን የሚያገኝበት ነው፡፡ የአደጋ ስጋቶች በክፍል 4 ላይ የተጠቀሱት ሲሆኑ በእነዚህ አደጋ ስጋቶች በማቀዝቀዣ ማሽነሪና ተዛማጅ መሳሪያዎች ላይ ጉዳት ደርሶ የማቀዝቀዝ ኃይሉ ቢቀንስ ወይም ቢቋረጥ በውስጡ ያለው አበባ ላይ ጉዳት ይደርሳል፡፡ ይህ ጉዳት በአበባ መድን ዋስትና ላይ በተጠቀሰው መሠረት ሽፋን ይሰጠዋል፡፡


በዚህ ክፍል ለተጠቀሰው ንብረት መድን ለመግዛት አስቀድሞ ለማቀዝቀዣ ማሽነሪና ተዛማጅ መሳሪያዎች ዋስትና ሊገባለት ያስፈልጋል፡፡

2.አጠቃላይ ሁኔታዎች

መድን ገቢው መድን ለተገባለት ንብረት ደህንነት ተገቢውን ጥንቃቄና ክትትል እንክብካቤ ማድረግ ይኖርበታል፣

መድን ሰጪው መድን የተገባለትን ንብረት የማየትና የመጐብኘት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በዚህ ውል መሠረት የካሣ ጥያቄ የሚያስነሳ ወይም ሊያስነሳ የሚችል ማንኛውም ሁኔታ ቢከሰት መድን ገቢው፣


ሀ.ንብረቱ ሙሉ በሙሉ በአደጋው እንዳይወድም ጉዳቱን ለማቆም ወይም ለመቀነስ አፋጣኝ እርምጃ ይወስዳል፡፡

ለ.በንብረቱ ላይ ለደረሰ ጉዳት ወይም ውድመት ኃላፊነት ያለበት አካል ካለ ኃላፊነቱን እንዲወስዱና ሰርቬይ እንዲያደርጉ ዕድል ለመስጠት እንዲያመች በአፋጣኝ ያሳውቃል፡፡

ሐ.ውድመት ወይም ጉዳት በደረሰበት ጊዜ የአደጋውን ቀን በመጥቀስ ለመድን ሰጪው በ48 ሰዓት ያሳውቃል፡፡

በዚህ ውል መሠረት ማንኛውም የካሣ ጥያቄ በሚነሳበት ጊዜ ያንኑ ተመሣሣይ ጥፋት፣ ጉዳት የሚሽፍን ሌላ የመድን ዋስትና ቢኖር ድርጅቱ ከማንኛውም የጥፋት፣ የጉዳት፣ የካሣው ወይም የወጪው ድርሻ በላይ የመክፈል ወይም አስተዋፅኦ የማድረግ ኃላፊነት የለበትም፡፡

አለአግባብ የካሣ ክፍያ ለማግኘት ሲባል በመድን ገቢው ወይም በሱ ምትክ ማንኛውም ሰው የማጭበርበር መንገድ ቢጠቀም የዚህ ውል ጥቅም ውድቅ ይሆናል፡፡

ድርጅቱ በመጨረሻ ጊዜ በሚታወቅበት አድራሻ የ3ዐ ቀን የፅሑፍ ማስታወቂያ በተመዘገበ ደብዳቤ ለመድን ገቢው በመላክ ውሉን ለማቋረጥ ይችላል፡፡ ውል ገቢው የከፈለው አረቦን ውሉ ፀንቶ የቆየበትን ጊዜ በማሰብ ተቀንሶ ለመድን ገቢው ይመለስለታል፡፡ ውል ገቢው በማንኛውም ጊዜ የፅሑፍ ማስታወቂያ በመስጠት ውሉን መሠረዝ ይችላል፡፡ በውሉ የጊዜ ገደብ ውስጥ የካሣ ጥያቄ ካልቀረበ ውሉ ፀንቶ ለቆየበት ጊዜ በድርጅቱ የአጭር ጊዜ የአረቦን ስሌት መሠረት አረቦኑ ተቀንሶ ልዩነቱ ለመድን ገቢው ተመላሽ ይደረግለታል፡፡

ማሳሰቢያ፡
ይህ ፅሑፍ ስለ አበባ መድን የቀረበ ማብራሪያ እንጂ በሕግ ፊት የሚፀና ውል አይደለም፡፡

   

Home  About Us Financial Indicator Life Insurance Non-Life Insurance Main Branch Forms Contact Us