About Us Financial Service Publication Branches News Forms Contact Us Articles FAQ
 

Side Menu



Proposal Forms
-----------------------
Proposal With Medical Certificate
Proposal Without  Medical Certificate
Proposal for Medical Insurance 

Claim Forms 
------------------------
Medical Claim Notification
Accident and Disease Notification
Medical Attendance Certificate
Death Confirmation Form

 
የቀብር ማስፈፀሚያ ወጪ ሽፋን

ይህ ተጨማሪ ውል የቋሚው የሕይወት መድን ውል ከዚህ በኋላ  ውል እየተባለ የሚጠራ አካል ነው፡፡ ድርጅቱ የውሉ ባለቤት ከዚህ ዓለም በሞት በሚለይበት ጊዜ የሽፋኑን መጠን ለተጠቃሚዎቹ ይከፍላል፡፡ ተጠቃሚዎቹ በውል መጠየቂያ ሠንጠረዡ ላይ የተገለፁና የተጠቀሱት ናቸው፡፡

የሚሟሉ ሁኔታዎች

የግል አባላት መድንን ስለማቋረጥ

በግል መድን የገቡ አባል ውሉን ካቋረጡ በዚህ ውል ለአባሉ የሚሰጠው ሽፋን ወዲያውኑ ይቋረጣል፡፡

የካሣ ጥያቄ ስለማቅረብ በቡድን

ሞትን ማሳወቅና ጠቀሜታን ማስተላለፍ የሚከናወነው በባለውሉ ነው፡፡ የውሉ ባለቤት ሞት መከሰቱን ባሳወቀ በ48 ሰዓት ውስጥ የካሣ ክፍያው ይፈፀማል፡፡ የውሉ ባለቤት የሟቹን ሞትና ቀብር የሚያረጋግጥ ደብዳቤ እና የመታወቂያ ወረቀት ካርድ ወይም የልደት ሰርተፊኬት ለድርጅቱ ያቀርባል፡፡ ጠቀሜታው በተጠቃሚዎቹ ስም ለውሉ ባለቤት ይከፈላል፡፡

የውሉ ባለቤት የካሣ ክፍያው ከተፈፀመ ከ6ዐ ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ዋናውን የሞት ሰርተፊኬት ለድርጅቱ ያቀርባል፡፡

ከህልፈት ሕይወት ጋር ተያያዥነት ስለአላቸው ሌሎች ክፍያዎች

ድርጅቱ በዚህ ውል መሠረት ማንኛውንም ጠቀሜታ በመክፈሉ ተጠያቂ የሚሆንበትን ቀረጥና ግብር ከሚከፍለው ጠቀሜታ ላይ ይቀንሳል፡፡

ገንዘብና ዳኝነት

ማንኛውም በአረቦን ወይም በጠቀሜታ መልክ የሚከፈል ገንዘብ የሚከፈለው በኢትዮጵያ ገንዘብ ነው፡፡ ይህ ውል በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

የፍርድ አፈፃፀም

የአባሉ ሞት የተከሰተው በሞት ፍርድ ምክንያት ከሆነ ውሉ ይሰረዝና ለድርጅቱ የተከፈለው ማንኛውም ክፍያ በሙሉ ተመላሽ አይደረግም፡፡

የጦርነት የአደጋ ሥጋቶች

ማንኛውንም በዚህ ውል ውስጥ የተካተተ ነገርን የሚቃረን ነገርን ለመቋቋም ሲባል ካልሆነ በስተቀር ሞት የተከሰተው በቀጥታ በጦርነት፣ በወረራ፣ በውጭ ጠላት ጥቃት፣ በግጭት ወይም በጦርነት መሰል ድርጊቶች ጦርነት ቢታወጅም ባይታወጅም፣ በእርስ በርስ ጦርነት፣ በሕዝባዊ አመፅ መነሳሳት፣ በአብዮት፣ በሥልጣን ንጥቂያ ከሆነ፣ ውሉ የሚያስገኘው ምንም ዓይነት ጠቀሜታ አይከፈልም፡፡

 

የካሣ ክፍያ

በካሣ ክፍያ ወቅት ተፈፃሚ የሚሆን ምንም ዓይነት ..የመቆያ ጊዜ.. አይኖርም፡፡

ማሳሰቢያ፡

ይህ ፅሑፍ ስለ ተጨማሪ የሕይወት መድን ዋስትናዎች የቀረበ ማብራሪያ እንጂ በሕግ ፊት የሚፀና ውል አይደለም፡፡

   

Home  About Us Financial Indicator Life Insurance Non-Life Insurance Main Branch Forms Contact Us