አጠቃላይ
አጠቃላይ የአደጋ መድን ከመሠረታዊ የሕይወት መድን ጋር የሚሰጥ ነው፡፡
የውሉ ባለቤት ወይም በውል መጠየቂያ ሠንጠረዡ ላይ ስሙ የተጠቀሰው የሕይወት መድን ገቢ የመጀመሪውያን አረቦን በመክፈሉና ለጠቅላላ መድን ሽፋን ማንኛውንም ቀጣይ አረቦን ለኢትዮጵያ መድን ድርጅት ከዚህ በኋላ ድርጅቱ ተብሎ ለሚጠራው ለመክፈል በመስማማቱ ውሉ የሚያስገኘው ጠቀሜታ ባለቤት ይሆናል፡፡
የውሉ ባለቤት የሕይወት መድን ገቢው እና ድርጅቱ በውሉ ባለቤት በውል መጠየቂያ ቅፅ በቀረበው ማመልከቻ ወይም ማንኛውም በፅሑፍ የቀረበ ማስረጃ ለሚሰጠው የመድን ሽፋን መሠረት እንዲሆን ተስማምተዋል፡፡ እንዲሁም ይህ አጠቃላይ የአደጋ መድን የውሉ አካል ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
ከዚህ በላይ የተሰጠውን መግለጫ ከግንዛቤ በማስገባት የሕይወት መድን ዋስትናው ባለቤት እድሜው 6ዐ ዓመት ከመሆኑ በፊትና ይህ አጠቃላይ የአደጋ ዋስትና ውል በፀናበት ጊዜ በመድን ገቢው ላይ የሞት፣ የአካል ጉዳት ከደረሰ በዚህ አጠቃላይ የአደጋ ዋስትና ላይ በሰፈሩት አንቀፆችና ቅድመ ሁኔታዎች መሠረት አጠቃላይ የአደጋ ዋስትናው የሚያስገኘው” ጠቀሜታ ድርጅቱ በሠንጠረዡ ላይ በተመለከተው መሠረት ይፈፅማል፡፡ ሆኖም ይህ ጉዳት በቀጥታ እና ከሌሎች ጉዳቶች ጋር ባልተያያዘ በውጫዊ፣ ኃይለኛ ወይም በድንገተኛ ምክንያቶች የተፈጠረ መሆን ያለበት ሲሆን ለዚህም በውል ገቢው ሰውነት ላይ የሚታይ የቁስል ወይም የመበለዝ ምልክት መኖር አለበት፡፡
- ብያኔ
1.1 በዚህ ውል እንደተገለፀው የአካል ጉዳት ማለት ከአደጋ የተነሣ የተፈጠረ እንዲሁም አጠቃላይና ቋሚ የአካል ጉዳት በመከሰቱ በወቅቱም ሆነ ከዚያ በኋላ ባለዋስትናው በብቃት የሚሰራው ወይም ገቢ የሚያስገኝለት ወይም ትርፍ የሚያገኝበት ተግባር፣ ሥራ ወይም ሙያ ማከናወን አይችልም ማለት ነው፡፡
ይህ አደጋ በተፈጠረ በዘጠና ቀናት ውስጥ ከሌሎች ምክንያቶች ውጭ በድንገት ጉዳት ቢደርስና የብርሃን ማጣት ወይም የእጅ፣ የእግር መቆረጥ ቢከተል እንደ አካል ጉዳተኝነት ይቆጠራል፡፡ 1.2 እጅ/እግር ማጣት ማለት በቀጥታ በእጅ አንጓ መገጣጠሚያ ወይም በእግር ቁርጭምጪት እና ከዚያ በላይ የተፈጠረ የአካል ማጣት ሲሆን፤ የብርሃን ማጣት ማለት ሊድን ወይም ሊተካ በማይችል ደረጃ ማየት አለመቻል ማለት ነው፤ የአውራ ጣት ወይም ጣት ማጣት ማለት በቀጥታ በጣቶች ላይ ወይም በጣቶች መገናኛ ላይ የሚደርስ የጣት መቆረጥ ማለት ነው፡፡ ይህም የሁሉም ጣቶች በኦኘራሲዮን መቆረጥ ነው
- ፍፁም ቅን ልቦና
በመድን ዋስትና መሙያ ቅፅ ላይ የተሞሉት መረጃዎች ሀሰት ከሆኑ ወይም ይህ ጠቅላላ የአደጋ መድን ውል የተገኘው ጠቃሚ መረጃን በመደበቅ ወይንም እውነታን አሳስቶ በመግለፅ ከሆነ፤ ወይም የሕይወት መድን ገዢው መጥፎ ባህሪ ካለውና ጥቅም ለማግኘት ሲል ከዋሸ፤ የመድን ውሉና ጠቅላላ የአደጋ መድኑ ውድቅ ይደረግና የተከፈለው ዋስትና አረቦን ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- ጠቅላላ ውል
ይህ ጠቅላላ የአደጋ መድን ከማመልከቻው ጋር የውል፣ መጠየቂያውና በውስጡ የተካተቱት መረጃዎች እንዲሁም ደብዳቤዎች ከጠቅላላው የአደጋ መድን ጋር የተያያዙ ስምምነቶች፤ በመድን ሰጪው እና በመድን ገቢው መካከል የተደረገው የውል ስምምነት አካል ይሆናሉ፡፡ በሌላ አኳኋን ካልተገለፀ በስተቀር ስምምነቶች፣ ሁኔታዎች እና የውሉ ሰንጠረዥ እዚህ ላይ ከሰፈረው ጠቅላላ የአደጋ መድን ጋር ተዛማጅነት እስካላቸው ድረስ ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡
- ከፍተኛ የአደጋ ሥጋት ወደአለው የሥራ ሙያ መቀየር
መድን ገቢው በመድን መጠየቂያ ቅፅ ላይ ከተካተተው መረጃ ውጪ ወይም በማንኛውም ሰነድ ላይ ከሰፈረው የሥራ ዓይነት ውጪ አደገኛ የሆነን ሥራ መሥራት ከጀመረ ይህ ጠቅላላ የአደጋ መድን የሚሰጠው ሽፋን ይቋረጣል፡፡ ነገር ግን ይህንኑ መድን ገቢው ካሳወቀና ድርጅቱ መቀበሉን በፅሑፍ ከአረጋገጠ እና አስፈላጊው ተጨማሪ አረቦን ከተከፈለ ውሉ እንደፀና ይቆያል፡፡
- ጉዳትን ማስታወቅና ማረጋገጥ
|
ሀ. |
የሕይወት መድን የተገባለትን ሰው ለመለየት የሚያስችሉ ዝርዝር ሁኔታዎችንና የካሣ ክፍያ የተጠየቀበት ጉዳት የተከሰተበትን ሁኔታ፣ ባህሪ እና መጠኑን በሙሉ ያካተተ የፅሑፍ ማስታወቂያ ጉዳቱን ያስከተለው አደጋ በደረሰ በሰላሣ ቀናት ውስጥ ለድርጅቱ መቅረብ አለበት፡፡ በአደጋ ምክንያት ሞት በሚከሰትበት ጊዜ ወዲያውኑ ለድርጅቱ መገለፅ ይኖርበታል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ወይም ማስታወቅ በሚቻልበት ጊዜ ውስጥ ተገቢ ማስታወቂያ ሳይቀርብ ቢቀር ማንኛውም የካሣ ክፍያ ጥያቄ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ |
|
ለ. |
ድርጅቱ ኃላፊ የሚሆንበት የካሣ ጥያቄ ከቀረበ በኋላ ባሉት ዘጠና ቀናት ውስጥ የጉዳቱ ማረጋገጫ ለድርጅቱ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ |
|
ሐ. |
የካሣ ክፍያ ጥያቄው በይደር ላይ እያለ ድርጅቱ አስፈላጊ ሆኖ ባገኘው ጊዜ የካሣ ክፍያ ጥያቄ ያቀረበውን መድን ገቢ በተመለከተ የማጣራት መብት ይኖረዋል፡፡ በሕግ ካልተከለከለ በስተቀር ሞት በተከሰተ ጊዜ ድርጅቱ የሟቹን አስከሬን የማስመርመር መብት አለው፡፡ |
- የካሣ ክፍያ አፈፃፀም
- በዚህ ጠቅላላ የአደጋ መድን ለደረሰው ጉዳት የሚከፈለው ማካካሻ በሙሉ ማረጋገጫው እንደደረሰ ወዲያውኑ ይፈፀማል፡፡ ለመድን ገቢው ሞት የሚሰጠው ካሣ ከዚህ ጠቅላላ የአደጋ መድን ጋር ተያይዞ በሚገኘው የመድን ውል መሠረት ተጠቃሚ ለሆኑት አካላት ተከፋይ ይሆናል፡፡ የሕይወት መድን ገቢው በሕይወት ከተረፉ በዚህ ጠቅላላ የአደጋ መድን የሚገኙ ማንኛቸውም ሌሎች ማካካሻዎች ለባለውሉ ተከፋይ ይሆናሉ፡፡
- በዋስትናው ባለቤት በሚቀርብ ጥያቄና ድርጅቱ በሚያደርገው ማጣሪያ መሠረት የመክፈል ኃላፊነት ለሚኖርበት የአካል ጉድለት ክፍያውን በየአራት ሣምንቱ ይፈፅማል፡፡ ለደረሰው የአካል ጉድለት መከፈል የነበረበት ነገር ግን ሳይከፈል የቀረ ገንዘብ ካለ በውሉ ባለቤት ይህንኑ የሚያረጋግጥ መረጃ እንደቀረበ ክፍያው ወዲያውኑ ይፈፀማል፡፡
- የሕይወት መድን ገቢው የሥራ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ሳይገባ ከላይ ያልተጠቀሱ ቋሚ የአካል ጉድለቶች በዝርዝር ከተቀመጡት የአካል መጉደል ጋር እየተነፃፀሩና እንደ ከባድነታቸው እየታየ ማካካሻ ይከፈልባቸዋል፡፡
- በውል ሠንጠረዡ ውስጥ ተለይቶ ያልተጠቀሰ የእጅና የእግር ወይም የሰውነት ክፍል በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት አለመቻል በውል ሠንጠረዥ ውስጥ እንደተጠቀሰው እጅና እግር ወይም የሰውነት ክፍል ከፊል ወይም ሙሉ ጉዳት እንደደረሰበት ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
- አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ጉዳቶች በአንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ አደጋዎች ምክንያት ቢከሰቱ የሚከፈለው ካሣ ከጠቅላላው የአደጋ መድን ወይም በፅሑፍ ከተጠቀሰው የሽፋን መጠን ያልበለጠ ሆኖ የሁሉም ድምር ይሆናል፡፡
- ሕጋዊ ሂደቶች
በዚህ ጠቅላላ የአደጋ መድን መስፈርት መሠረት የጉዳቱ ማረጋገጫ ከቀረበ በኋላU ቢሆን የውል ጊዜ ከማብቃቱ ከስድሳ ቀናት በፊት ምንም ዓይነት ሕጋዊ እርምጃ አይወሰድም፡፡ በሌላ በኩል ሕጋዊ እርምጃው ከውሉ ማብቂያ ጊዜ ጀምሮ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ከጉዳት ማረጋገጫው ጋር ካልቀረበ በስተቀር የካሣ ክፍያውን ሙሉ በሙሉ መጠየቅ አይቻልም፡፡
- የውል ዕድሳት
ይህ ጠቅላላ የአደጋ መድን በውል እድሳቱ ወቅት በሥራ ላይ ባለው የድርጅቱ የአረቦን ተመን መሠረት አረቦኑን በቅድሚያ በመክፈል በድርጅቱ ስምምነት በየጊዜው ይታደሳል፡፡ ከመጀመሪያው የአረቦን ክፍያ በስተቀር ለእድሳት የአረቦን ክፍያ የሰላሣ አንድ ቀን የእፎይታ ጊዜ ይሰጣል፡፡ በዚህ የእፎይታ ጊዜ ውስጥ ይህ ጠቅላላ አደጋ መድን እንደፀና ይቆያል፡፡ የእፎይታ ጊዜው በሚያበቃበት ወቅት በዚህ ጠቅላላ የአደጋ መድን መከፈል ያለበት አረቦን ሳይከፈል ቢቀር ሽፋኑ ይቋረጣል፤ ከዚህ በኋላ ተፈፃሚ የሚሆን ምንም ዓይነት የመቆያ ጊዜም አይኖርም፡፡
- ውል ስለማቋረጥ
|
ሀ. |
በጠቅላላ የአደጋ መድን ሥር የተሰጠ መድን በሚከተሉት ሁኔታዎች ሊቋረጥ ይችላል፡፡ |
|
ጠቅላላ የአደጋ መድኑ ወይም አብሮት የተያያዘው የመድን ውል አረቦን መከፈል በሚኖርበት ጊዜ ወይም በእፎይታ ጊዜው ውስጥ ሳይከፈል ሲቀር፣ |
|
የተጠቀሰው የመድን ውል ሁለት ዓመት አልፎት ለመድን ገቢው ሊመለስ የሚችል ገንዘብ ካስገኘ ወይም ወደ ተከፈለ መድን ከተለወጠ ወይም የተወሰነ ጠቀሜታ ከተገኘበት በኋላ ወይም፣ |
|
የተጠቀሰው ውል የእድሳት ወቅት የመድን ገቢው 6ዐኛ ዓመት ልደት በተቃረበበት ወቅት ከሆነ፣ |
|
|
ይህ ጠቅላላ የአደጋ መድን ውል በመድን ገቢው ወይም በድርጅቱ አማካይነት እንዲቋረጥ ሲደረግ ውሉ ከመቋረጡ በፊት በቀረበ ማንኛውም የካሣ ክፍያ ጥያቄ ምክንያትነት አይሆንም፡፡
|
|
ለ. |
ይህ ጠቅላላ የአደጋ መድን በሚቋረጥበት በማንኛውም ጊዜ ለዚሁ ሲባል ይከፈል የነበረው የአረቦን ክፍያ ይቋረጥና መድን ገቢው ያልተጠቀመበት አረቦን ካለ ያንን ከመመለስ ባሻገር ድርጅቱ ሌላ ኃላፊነት አይኖርበትም፡፡
ይህ ጠቅላላ የአደጋ መድን እንደገና እንዲፀና ካልተደረገ በስተቀር ውሉ ከተቋረጠ በኋላ ቀሪ ሂሣብን በተመለከተ መድን ገቢው የከፈለው ወይም ድርጅቱ የተቀበለው አረቦን በድርጅቱ ላይ ኃላፊነት ሊያስከትል አይችልም፡፡ |
- ውል እንደገና እንዲፀና ማድረግ
ለጠቅላላ የአደጋ መድን ስምምነት የተደረገበት አረቦን ክፍያ ሳይከፈል ቢቀርና ጠቅላላ የአደጋ መድን ውሉ አብሮ የተሰጠበት የዋናው ውል አረቦን ተከፍሎ ውሉ የፀና ከሆነ ጠቅላላ የአደጋ መድን ውሉ በድርጅቱ ስምምነት እንደገና እንዲፀና ሊደረግ ይችላል፡፡ ውሉ እንዲሸፍን የሚደረገው ጠቅላላ የአደጋ መድን የሚሸፍነው ውሉ እንደገና እንዲፀና ከተደረገ በኋላ በአደጋ ምክንያት የደርስ ጉዳትን ነው፡
- ሽፋን የማይሰጣቸው አደጋ ስጋቶች
በጠቅላላ የአደጋ መድን የሚሰጠው መድን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ምክንያቶች በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ፣ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የደረሰን ማንኛውንም ጉዳት ወይም የአካል ጉድለት አይሸፍንም፡፡
|
ሀ. |
በአእምሮ ሕመምም ሆነ በጤነኛ መንፈስ በማንኛውም ሁኔታ በራስ ላይ ጉዳት ለማድረስ፣ በሚደረግ ሙከራ፣ |
|
ለ. |
በታወጀ ወይም ባልታወጀ ጦርነት፣ በአመፅ፣ በብጥብጥ፣ በእርስ በርስ ጦርነት፣ በአብዮት ወይም በማንኛውም ጦርነት መሰል ድርጊት፣ |
|
ሐ. |
የታወጀ ወይም ያልታወጀ ጦርነት በሚካሄድበት ወቅት በሚኖር የወታደር፣ የባህር ኃይል ወይም የአየር ኃይል አገልግሎት ወይም የመንግሥትን ትዕዛዝ ለማስጠበቅ ወይም በጦርነት መሰል ድርጊት፣ |
|
መ. |
በሕጋዊ አካል በሚፈፀም እስር፣ |
|
ሠ. |
ጥቃት በማድረስ ወይም ግድያ በመፈፀም ወይም ማንኛውንም ሌላ ሕግ በመጣስ ወይም ለመጣስ በሚደረግ ሙከራ ወይም አልታሰርም በማለት፣ |
|
ረ. |
በልብ ሕመም ወይም በጨረር በመወጋት፣ |
|
ሰ. |
በሁከት ላይ በመሳተፍ፣ |
|
ሸ. |
በመኪና ውድድር በመሳተፍ፣ |
|
ቀ. |
በእርግዝና ወይም በወሊድ፣ |
|
በ. |
የሕይወት መድን ገቢው በአልኮል ወይም በዕፅ ታውኮ ለደረሰበት አደጋ፣ |
|
ተ. |
በሥር መዞር ምክንያት የሚመጣ የባክቴሪያ ኢንፍክሽን በአደጋ ምክንያት በደረሰ መቆረጥ ወይም መጎዳት የተፈጠረ ኢንፍክሽን ካልሆነ በስተቀር |
|
ቸ. |
ማንኛውም በሽታ ወይም ሕመም |
|
ነ. |
በውዴታም ሆነ በግዴታ የተወሰደ መርዝ፣ ጋዝ ወይም የተበከለ ጭስ |
|
ኀ. |
በተመዘገበ በታወቀ የመንገደኛ ጉዞ ወይም መስመር በሚሰራ የንግድ አውሮኘላን ሲጓዝ ካልሆነ በስተቀር በማንኛውም አየር ላይ ለመጓጓዝ ሲገባ፣ ሲሰራ ወይም አገልግሎት ሲሰጥ፣ ሲወጣ ወይም ሲወረድ ለደረሰ ጉዳት |
የጠቀሜታ ሠንጠረዥ
ክፍል 1
|
|
የጉዳቱ መጠን |
የክፍያ መጠን የሽፋን መጠኑ በመቶኛ |
|
1.1 |
የሕይወት ማለፍ |
100 |
|
1.2 |
ሁለቱንም እጆች ማጣት |
100 |
|
1.3 |
ሁለቱንም እግሮች ማጣት |
100 |
|
1.4 |
የሁለቱንም ዓይኖች ብርሃን ማጣት |
100 |
|
1.5 |
አንድ እጅና የአንድ ዓይን ብርሃን ማጣት |
100 |
|
1.6 |
አንድ እጅና አንድ እግርን ማጣት |
100 |
|
1.7 |
አንድ እግርና የአንድ ዓይን ብርሃን ማጣት |
100 |
|
1.8 |
ሙሉ የአካል ሽባነት |
100 |
|
1.9 |
ሙሉ በሙሉ አእምሮን መሳት |
100 |
|
1.10 |
ሙሉ እና ቋሚ የአካል ጉድለት የሚያስከትል ሌላ ማንኛውም ጉዳት |
100 |
ክፍል 2
|
2.1 |
የአንድ ዓይን ብርሃን ማጣት |
50 |
|
2.2 |
ከትከሻ ላይ የአንድ እጅ መቆረጥ |
60 |
|
2.3 |
በክርን እና በትከሻ መካከል የአንድ እጅ መቆረጥ |
55 |
|
2.4 |
ከክርን ላይ የአንድ እጅ መቆረጥ |
50 |
|
2.5 |
በእጅ አንጓና በክርን መካከል የአንድ እጅ መቆረጥ |
50 |
|
2.6 |
በእጅ አንጓ ወይም በሰዓት ማሰሪያ ላይ የአንድ እጅ መቆረጥ |
50 |
|
2.7 |
ትከሻ ወይም ክርን ሙሉ ለሙሉ መሥራት አለመቻል |
30 |
|
2.8 |
የእጅ አንጓ ሰዓት ማሰሪያ ሙሉ ለሙሉ መሥራት አለመቻል |
25 |
|
2.9 |
የአንድ እጅን አምስቱንም ጣቶች ማጣት |
50 |
|
2.10 |
አራት ጣቶችንና አንድ እጅን ማጣት |
40 |
|
2.11 |
የአውራ ጣት ሁለት አንጓዎችን ማጣት |
20 |
|
2.12 |
የአውራ ጣት አንድ አንጓን ማጣት |
10 |
|
2.13 |
የአመልካች ጣት ሦስት አንጓዎችን ማጣት |
15 |
|
2.14 |
የአመልካች ጣት ሁለት አንጓዎችን ማጣት |
10 |
|
2.15 |
የአመልካች ጣት አንድ አንጓን ማጣት |
5 |
|
2.16 |
የመሃል ጣት ሦስት አንጓዎችን ማጣት |
10 |
|
2.17 |
የመሃል ጣት ሁለት አንጓዎችን ማጣት |
5 |
|
2.18 |
የመሃል ጣት አንድ አንጓን ማጣት |
3 |
|
2.19 |
የቀለበት ጣት ሦስት አንጓዎችን ማጣት |
6 |
|
2.20 |
የቀለበት ጣት ሁለት አንጓዎችን ማጣት |
5 |
|
2.21 |
የቀለበት ጣት አንድ አንጓን ማጣት |
3 |
|
2.22 |
የትንሿን ጣት ሦስት አንጓዎችን ማጣት |
5 |
|
2.23 |
የትንን ጣት ሁለት አንጓዎች ማጣት |
4 |
|
2.24 |
የትንሿን ጣት አንድ አንጓ ማጣት |
3 |
|
2.25 |
የመዳፍ አጥንት የመጀመሪያ ወይም ሁለተኛ መሰበር ተጨማሪ ) |
3 |
|
2.26 |
የመዳፍ አጥንት ሦስተኛ፣ አራተኛ ወይም አምስተኛ መሰበር ተጨማሪ |
3 |
|
2.27 |
የእግር እጭን ላይ መሰበር |
70 |
|
2.28 |
በጭንና በጉልበት መካከል የእግር መቆረጥ |
50 |
|
2.29 |
ከጉልበት በታች የእግር መቆረጥ |
40 |
|
2.30 |
የአንድ እግር ጣቶችን በሙሉ ማጣት |
16 |
|
2.31 |
የእግር አውራ ጣትን ሁለት አንጓዎች ማጣት |
7.5 |
|
2.32 |
የእግር አውራ ጣትን አንድ አንጓ ማጣት |
3 |
|
2.33 |
ከአውራ ጣት በስተቀር ሌሎቹን የእግር ጣቶች በማጣት ለእያንዳንዳቸው |
2 |
|
2.34 |
የጭን ወይም የጉልበት ወይም የቁርጭምጭሚት ከሥራ ውጪ መሆን |
20 |
|
2.35 |
የእግር ማጠር ቢያንስ በትንሹ 5 ሣ.ሜ ሲያጥር |
15 |
|
2.36 |
የአንድ ዓይን ብርሃን ሙሉ በሙሉ መጥፋት |
50 |
|
2.37 |
ሁለቱም ጆሮዎች መስማት ሲሳናቸው |
80 |
|
2.38 |
አንድ ጆሮ መስማት ሲሳነው |
20 |
ክፍል 3
3.1 የሕይወት መድን ገቢው ጊዜያዊ ሙሉ የአካል ጉድለት ቢደርስበትና ይህም
|
ሀ. |
አደጋው በደረሰ በአስራ ሦስት ሣምንታት ውስጥ ቢከሰት፣ |
|
ለ. |
የአካል ጉድለቱ የሕይወት መድን ገቢውን ማንኛውንም መደበኛ ሥራውን ከመሥራት ቀጣይነት ላለው ጊዜ ቢያግደው እና |
|
ሐ. |
ቢያንስ ለአራት ሣምንታት የሚቆይ ከሆነ |
ክፍያው በሚከተሉት ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ይሆናል፡፡
ድርጅቱ ጠቅላላ ዋስትና ከተገባለት የሽፋን መጠን ተገቢውን ክፍያ በስሌት ይፈፅማል፡፡
|
-
ክፍያው አደጋው ከደረሰበት ጊዜ አንስቶ ለአምሣ ሁለት ሣምንታት ይፈፀማል፡፡
-
የአካል ጉድለቱ ቀጣይነት ከሌለው በስተቀር ከአራት ሣምንት በታች ለሆነ ጊዜ ክፍያ አይፈፀምም፡፡ |
|
|
3.2 የሕይወት መድን ገቢው ጊዜያዊ ከፊል የአካል ጉድለት ቢደርስበትና ይህም
|
ሀ. |
አደጋው ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ቢከሰት ወይም በተራ ቁጥር 3.1 ሥር የተጠቀሰውን ጊዜያዊ ሙሉ የአካል ጉድለት ተከትሎ ወዲያውኑ ከተከሰተ፣ |
|
ለ. |
የአካል ጉድለቱ ሙሉ በሙሉ ሣይሆን አንዱን ወይም ከዚያ በላይ የሆነውን የመደበኛ ሥራውን ክፍል ከመሥራት ካገደው፣
|
|
ሐ. |
አካል ጎድለቱ አደጋው ከደረሰበት ቀን ከሆነና ቢያንስ ለአራት ሣምንታት ከቆየበት ፣
|
ድርጅቱ ጠቅላላ ዋስትና ከተገባለት የሽፋን መጠን ተገቢውን ክፍያ በማስላት ይከፍላል፡፡ የክፍያው አፈፃፀም ግን በተራ ቁጥር 3.1 በተዘረዘሩት ሁኔታዎች መሠረት ይሆናል፡፡ 3.4 በዚህ ክፍል በተራ ቁጥር 3.1 እና 3.2 የተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የሣምንታት ብዛት በጠቅላላው ከአምሣ ሁለት ሣምንታት መብለጥ የለበትም፡፡ በተራ ቁጥር 3.1 እና 3.2 ሥር የሚፈፀመው አጠቃላዩ የክፍያ መጠን በማንኛውም መንገድ ከጠቅላላ የሽፋን መጠን የበለጠ አይሆንም፡፡
ክፍል 4
የሕይወት መድን ገቢው የምርመራ፣ የመድኃኒት፣ የአልጋና በአደጋው ምክንያት ያወጣቸው ሌሎች ወጪዎች ቢኖሩ ድርጅቱ ለአንድ ሰው በአንድ የመድን ሽፋን ወቅት ከተወሰነው ገንዘብ ያልበለጠ ክፍያ ለተጠቀሱት ወጪዎች ይከፍላል፡፡ |