ይህ ዓይነቱ መድን በየዓመቱ የሚታደስ ሲሆን፣ ውሉ ካልታደሰ ለውል ገቢው የሚመለስ ገንዘብ አይኖርም፡፡
ለምሣሌ አንድ ሰው የብር 10‚000 አሥር ሺህ ብር የቡድን ተርም የሕይወት ዋስትና የአደጋ መድን ጨምረው በመግዛት የውል ባለቤት ከሆኑበት ጊዜ ጀምሮ ውሉ የሚከተሉትን ጥቅሞች ለራሳቸው ወይም ለሕጋዊ ወራሾች ሊያስገኝ ይችላል፡፡
• ሞት ሲያጋጥም ለወራሾች ብር 10‚000 ይሰጣል፡፡ • በተጨማሪም የአደጋ ዋስትና ካላቸው በአደጋ ምክንያት ቢሞቱ ለወራሾቹ ብር 20‚000 ይሰጣል፡፡ • ሁለት እጆች ቢቆረጡ ብር 10‚000 • ሁለት እግሮች ቢቆረጡ ብር 10‚000 • የሁለት የዓይኖች ብርሀን ቢጠፋ ብር 10‚000 • አንድ እጅና አንድ እግር ቢቆረጡ ብር 10‚000 • አንድ እጅ ቢቆረጥና የአንድ ዓይን ብርሀን ቢጠፋ ብር 10‚000 • በጠቅላላው የሁለት አካል ወይም ከዚያም በላይ ጉዳት ቢደርስ ብር 10‚000 • በአደጋ ምክንያት ለሚደርስ የአካል ጉድለት ይኸውም የአውራ ጣትና የአመልካች ጣት ቢቆረጥ ብር 2‚500 • አንድ እጅ ቢቆረጥ ብር 5‚000 • አንድ እግር ቢቆረጥ ብር 5‚000 • አንድ ዓይን ብርሀን ቢጠፋ ብር 3‚333
ይህ ዝርዝር በምሳሌነት ለተጠቀሰው ለብር 10‚000 የዋስትና መጠን እንጂ እንደ ደንበኛው ፍላጎት ከፍና ዝቅ ሊል ይችላል፡፡
|