- የውሉ መሠረት የሆኑ ሁኔታዎች
ይህ ውል፤ የውል መጠየቂያ ሠንጠረዡ እና ከዚህ ጋር ተያይዞ ያለ ማንኛውም ማስታወሻ እንደ አንድ ሰነድ ይቆጠራሉ፡፡ እንዲሁም ማንኛውም ቦታ የተለየ ትርጉም የተሰጠው ማንኛውም ቃል ወይም አገላለፅ እስከመጨረሻው ይህንኑ ትርጉም ይይዛል፡፡
ድርጅቱና መድን ገቢው እንደሚከተለው ተስማምተዋል፡፡
የውል መጠየቂያ
- የውል መጠየቂያው ሠንጠረዥ የውሉ አካልና የውሉ መሠረት ሆኖ ያገለግላል፣
- መድን ገቢው ተገቢውን አረቦን ይከፍላል፣
- በዚህ ውል መሠረት ድርጅቱ የመድን ሽፋን ይሰጣል፡፡
ድርጅቱ ኃላፊነት ከመውሰዱ በፊት መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች፡-
|
ሀ. |
በውሉ ውስጥ መድን ገቢው ሊያከናውናቸው ወይም ሊፈፅማቸው የሚገቡ ሁኔታዎች ሁሉ መፈፀም አለባቸው፡፡
|
|
ለ. |
በውል መጠየቂያው ላይ የተገለፁት ጉዳዮች በሙሉ እውነት መሆን አለባቸው፡፡ |
በውል ዘመኑ ውስጥ መድን ገቢው ህመም ቢያገኘው ወይም ድንገተኛ የአካል ጉዳት ቢደርስበት ለባለዋስትናው የሚደረጉት አጠቃላይ ገደቦች እንደተጠበቁ ሆነው በውል ዘመኑ ውስጥ መድን ገቢው ቢታመም ወይም በአደጋ ምክንያት የአካል ጉዳት ቢያጋጥመው በመድን ገቢው ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑት ገደቦች እንደተጠበቁ ሆነው በ12 ወራት ውስጥ ላወጣው ወጪ ድርጅቱ ማካካሻ ይከፍላል፡፡
ድርጅቱ የሚሸፍናቸው የሕክምና ወጪዎች ከፍተኛ መጠን በሚከተሉት ሁኔታዎች ይወሰናል፡-
|
ሀ. |
በአንድ የተወሰነ ምክንያት መነሻነት ወይም ውጤት መንስዔነት የመጣ አንድ የካሣ ክፍያ ጥያቄ ወይም ተከታታይ የካሣ ክፍያ ጥያቄዎች በአንድ የውል ዘመን ቢሆንም ባይሆንም ጉዳዩ ለሚመለከተው መድን ገቢ ከሚፈፀምለት አጠቃላይ የካሣ ክፍያ ጣራ አይበልጥም፡፡
|
|
ለ. |
በሽታው ወይም ህመሙ ወይም የአካል ጉዳቱ በግልፅ በታየበት በማንኛውም የውል ዘመን የሚቀርብ የካሣ ክፍያ ጥያቄ ሁሉ ጉዳዩ ለሚመለከተው መድን ገቢ ከሚከፈለው አጠቃላይ የካሣ ክፍያ መጠን አይበልጥም፡፡ | 2. አማራጭ ሽፋኖች በውሉ ላይ ከተመለከቱ ብቻ ሽፋን የሚሰጣቸው
ሀ. የቡድን ድንገተኛ አደጋ ወጪዎች
ለመድን ገቢው ሕይወት የሚያሰጋ የጤና ችግር መድን ገቢውን በማጋጠሙና የጤንነቱን ሁኔታ ለማሻሻል አስቸኳይ ህክምና በማስፈለጉ ምክንያት ድንገተኛ ወጪ ቢወጣ ደንበኛው ተጨማሪ አረቦን እንደሚከፍል ታሳቢ በማድረግ ድርጅቱ ወጪውን ይሸፍናል፡፡
ድርጅቱ ይህንን ወጪ የሚተካው ለመድን ገቢው በመደበኛው ሽፋን ሊያገኛቸው የሚገቡ ጠቀሜታዎች ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቁ ብቻ እና ሕክምናው ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ምክንያቶች የግድ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡
- ሕክምናው ከፍተኛ ጥንቃቄና ክትትል የሚያስፈልገው መሆኑ ሲረጋገጥ፣
- ሕክምናው ሀገር ውስጥ ባለመኖሩ ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ መታከም የሚያስፈልግ መሆኑ ሲረጋገጥ፣
- ከላይ በተራ ቁጥር 1 እና 2 በተጠቀሱት ሁኔታዎች ምክንያት ለረዥም ጊዜ በሆስፒታል ቆይቶ መታከም አስፈላጊ ሲሆንና
እንዲሁም ከላይ በተራ ቁጥር 2 ለተቀመጠው ቅድመ ሁኔታ ድርጅቱ ክፍያ የሚፈፅመው በሀገር ውስጥ በቂ ሕክምና ለማግኘት የማይቻል ሲሆንና ድርጅቱ የራሱን የሕክምና ባለሙያዎችን ምክር የመጠየቅ መብቱ ተጠብቆና የአማካሪው ሃሣብ ሁሉንም ወገኖች የሚያስማማ ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡
የድርጅቱ የኃላፊነት ጣራ በውል ሠንጠረዡ ላይ ከተቀመጠው የዋስትና መጠን የበለጠ አይሆንም፤ በአማራጭ ሽፋኖች የተገለፀው የኃላፊነት ገደብ በቡድን የተሰጠ ከሆነ የካሣ ክፍያው መጠን ለጠቅላላ ለቡድኑ እንጂ ለእያንዳንዱ ግለሰብ የሚፈፀም አይደለም፡፡ እንዲሁም ይህ መጠን ቡድኑን በተመለከተ በዋስትናው ዘመን ድርጅቱ ተጠያቂ የሚሆንበት ከፍተኛ መጠን ነው፡፡ የሽፋን መጠኑም ካሣ በተከፈለ ቁጥር እየቀነሰ ይመጣል፡፡
ለ. የጥርስ ሕክምና ወጪዎች
ድርጅቱ ተጨማሪ አረቦን በማስከፈል ለህክምናና ከሕክምና ጋር በተያያዘ ለሚሰጥ የምክር አገልግሎት፣ ለጥርስ መነቀያና መሙያ እንዲሁም በድንገተኛ፣ ውጪያዊ በሆነና በሚታይ መልኩ በጥርስ ላይ ለደረሰ አደጋ የሚወጣውን ወጪ ድርጅቱ ይሸፍናል፡፡
ልዩ ማግለያዎች
ድርጅቱ በሚከተሉት ሁኔታዎች ለሚፈፀም ክፍያ ኃላፊ አይሆንም፡፡
|
ሀ. |
በመድን ገቢው ላይ የደረሰው የአካል ጉዳት በውጫዊና በሚታይ አደጋ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር፤ በሰው ሰራሽ ጥርስና የጥርስ ሽፋን ላይ ለደረሰ ጉዳት የሚወጣውን የመቀየሪያ ወይም የመታከሚያ ወጪ አይሸፍንም፡፡ |
|
ለ. |
ህክምናው በድንገተኛ፣ በውጪያዊና በሚታይ ምክንያት በመድን ገቢው ላይ ለደረሰ የአካል ጉዳት ወይም ከጥርስ መበስበስ ውጭ በሆነ ህመም በሽታ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ለኦርቶዶንቲክ ወይም ውበት ለመፍጠር ተብሎ የሚደረግ ህክምና ወጪ አይሸፈንም፡፡ |
ገደቦች
በውል ዘመኑ ውስጥ የሚፈፀመው የካሣ ክፍያ መጠን የሚወሰነው ሠንጠረዡ ላይ በተገለፀው የሽፋን መጠን ይሆናል፡፡
ሐ. የመነፅር ወጪዎች
ድርጅቱ የመድን ገቢውን የመነፅር ወጪ፤ በድንገተኛ፣ በውጫዊና በሚታይ ምክንያት ወይም አይንን ወይም ኦኘቲክ ነርቭን በሚጎዱ ህመሞች የተነሣ በመድን ገቢው ዓይኖች ላይ ለደረሰ ጉዳት የሚወጣን የሕክምና ወጪ በተጨማሪ አረቦን ክፍያ ይሸፍናል፡፡
ሆኖም በዚህ ክፍል በማንኛውም የውል ዘመን የሚደረገው አጠቃላይ ክፍያ በሠንጠረዡ ላይ ለመነፅር ወጪዎች ተብሎ ከተቀመጠው መብለጥ አይኖርበትም፡፡
ልዩ ማግለያዎች
ድርጅቱ በሚከተሉት ሁኔታዎች ለሚወጡ ወጪዎች ኃላፊነት አይኖርበትም፡፡
|
ሀ. |
መድን ገቢው ባጋጠመው ድንገተኛ አደጋ ምክንያት በሚደረግ ሕክምና መቀየር ወይም መጠገን የግድ አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ለመነፅር ጥገና ወይም መነፅር ለመተካት ሲባል የወጣ ወጪ፣ |
|
ለ. |
በዕይታ መዳከም የተነሣ ለሚደረግ የዓይን ምርመራ፣ ወይም የመነፅር ወይም የሌንሶች መስፋትና መጥበብ ፍተሻ የሚደረግ ወጪን አይሸፍንም፣ |
አጠቃላይ ማግለያዎች
1. ድርጅቱ ከሚከተሉት ሁኔታዎች ጋር በተያያዘ ለተከሰተ የአካል ጉዳት ወይም በሽታ ወይም ህመም ኃላፊነት አይኖርበትም፡፡
|
ሀ. |
መድን ገቢው በማንኛውም በማግለያው ላይ በተጠቀሱት ተግባሮች በመለማመድ ወይም በተገለሉ እንቅስቃሴዎችና ሥልጠና ላይ በመሳተፍ ሊሆን ይችላል ላይ በመሳተፉ፤ |
|
ለ. |
ችግሩ የተፈጠረው የውሉ ዘመን ካበቃ በኃላ ከሆነና በዚህ ወቅት የመድን ገቢው ዕድሜ 6ዐ ዓመት ከሆነ፤ |
|
ሐ. |
ችግሩ የተፈጠረው መድን ገቢው ከሙሉ ጊዜ ተቀጣሪነት በጡረታ ከተገለሉ በኋላ ከሆነ፤ ይህ ማግለያ የሙሉ ጊዜ ሠራተኞች በሆኑት በመድን ገቢው ባለቤትና ልጆች ላይ ተግባራዊ አይሆንም፤ |
|
መ. |
የሰውን ልጅ ህይወት ለማዳን በሚደረግ ሙከራ ካልሆነ በቀር መድን ገቢው ራሣቸውን በመግደላቸው ወይም ራሣቸውን ለመግደል ሙከራ በማድረጋቸው ወይም ሆን ብለው ራሣቸውን በማቁሰላቸው ወይም በራሣቸው ላይ ህመም በመፍጠራቸው ወይም በገዛ ፈቃዳቸው ራሣቸውን ለአላስፈላጊ የአደጋ መንስዔ በማጋለጣቸው ምክንያት የተፈጠረ ከሆነ፤
|
|
ሠ. |
በአዮናይዚንግ፣ ጨረር ወይም ከማንኛውም የራዲዮ አክቲቭ ብክለት፣ በዚህ ማግለያ መሠረት የኒኩሊየር መቀጣጠል ማንኛውንም በራሱ ሂደት የተፈጠረ መቀጣጠልን ያካትታል፡፡
|
|
ረ. |
በጦርነት ወረራ፣ በውጭ ጠላት እንቅስቃሴ ጦርነት ቢታወጅም ባይታወጅም በእርስ በርስ ጦርነት፣ አመፅ፣ አብዮት፣ ሁከት ወይም በወታደራዊ ወይም ባልተገባ ኃይል የተፈጠረ ሲሆን፤
|
|
ሰ. |
ጉዳቱ ዕድሜው ከ6 ወራት በታች በሆነ በማንኛውም አባል ላይ የደረሰ ሲሆን፣ |
2. በመድን ገቢው በራሱ በተደረገ አስተዋፅኦ ለደረሰ የአካል ጉዳት፣ ህመም ወይም በሽታ ወይም የህክምና ወጪዎች
|
ሀ. |
መድኃኒት በመጠቀም ማለትም መድኃኒቱ ከህክምና ባለሙያ በተሰጠ አግባብ ባለው የመድኃኒት ማዘዣ እና መመሪያ መሠረት የተወሰደ መሆኑንና በዕፅ ሱስ አለመሆኑን ካላረጋገጠ በስተቀር መድን ገቢው ማረጋገጥ ካልቻለና መድኃኒቱም የታዘዘው የአደገኛ ዕፅ ተጠቃሚነትን ለማከም ከሆነ፣ |
|
ለ. |
መድን ገቢው በአልኮል ሱሰኝነት ወይም በአባላዘር በሽታ ከተጠቃ፣
|
|
ሐ. |
መድን ገቢው የውሉ ዘመን ከመጀመሩ አስቀድሞ የአዕምሮ ወይም ከሰውነት ጉድለት ወይም አካለ ጎዶሎነት ካለበትና ይኸውም ለድርጅቱ ቀርቦ ድርጅቱ መቀበሉን በፅሑፍ ካላረጋገጠ፣
|
|
መ. |
መድን ገቢው በተለመደ ሕመም የሚሰቃይ ከሆነና ይኸው ለድርጅቱ ቀርቦ ተገልፆ በፅሑፍ ተቀባይነት ካላገኘ፣ |
3. በሚከተሉት ምክንያቶች ለሚደርስ የሕክምና ወጪ
|
ሀ. |
የአካል ጉዳት ቀጥተኛ ውጤት ካልሆነ በስተቀር ለጥርስ ህክምና ወጪ፤
|
|
ለ. |
ሌንስን ከማስተካከል ውጭ የተለየ የዓይን ህክምናን ከአካተተ፣
|
|
ሐ. |
መድን ገቢው ሕክምና ያገኙት በመደበኛ ሆስፒታል ወይም ሕጋዊ በሆነ መንገድ በተቋቋመ ድርጅት ውስጥ በመታከም ካልሆነ በስተቀር ለአእምሮ ሕመም ለሚሰጥ የሥነ ልቦና ሕክምና፣
|
|
መ. |
አሰቃቂ የሰውነት ጉዳትን ለማስተካከል ካልሆነ በቀር ውበትን ለመጠበቅ ወይም የኘላስቲክ ቀዶ ሕክምና ለማድረግ ለሚወጣ ወጪ፣ |
|
ሠ. |
በሀይድሮ ኔቸር (hydro nature) የጤና ተቋም ወይም ክሊኒክ ወይም ተመሳሳይ ተቋም ወይም በሕክምና ተቋምነት የተመዘገበ የግል ድርጅት ውስጥ የተሰጠ ህክምና ወይም ጥበቃ፣
|
|
ረ. |
በሆስፒታል ወይም በሕክምና ተቋም ውስጥ በሚከተሉት ሁኔታዎች በተደረገ ማንኛውም የመኖሪያነት ቆይታ፣ |
|
1. |
ሙሉ ለሙሉ ወይም በተወሰነ መልኩ በእራሱ ምክንያት የተደረገ ቆይታ፣
|
|
2. |
በመደበኛ የመኖሪያ ሥፍራ በመሆን ሕክምና ለመስጠት የሚቻልበት ሁኔታ እያለ፣ |
|
ሰ. |
ማስታመም |
|
1. |
በተመዘገበና ሙያው ባለው ነርስ ካልተሰጠ በቀር፣ |
|
2. |
እንክብካቤው ከተመዘገበና ሙያው ካለው ነርስ ውጪም ቢሆን ሊሰጥ ከቻለ፣ |
|
ሸ. |
በድንገተኛ አደጋ ካልሆነ በቀር አንድ ሰው አባል በሆነ በ28 ቀናት ውስጥ ለሚደረግ ህክምና፣ |
|
ቀ. |
በክሊኒክ ወይም በዶክተር ለታዘዘ መድኃኒት |
3.ከሌላ የመድን ሽፋን ወይም ከሌላ ምንጭ፣ ከሠራተኛ ጉዳት ካሣ ጠቀሜታዎች ወይም ከመንግሥት ኘሮግራም ወይም ከካሣ ክፍያ ወጪው የተሸፈነለት ወይም ሊሸፈንለት ከቻለ፤ ለሕክምናው ተጨማሪ ወይም ከእነዚህ ተቋማት ከሚገኘው ካሣ መጠን በላይ የሆነ ገንዘብ ከአላስፈለገ በስተቀር ወጪው አይሸፈንም፡፡
የሚሟሉ ሁኔታዎች
- የካሣ ክፍያ የሚያስነሳ ክስተት በተፈጠረ በ3ዐ ቀናት ውስጥ የፅሑፍ ማስታወቂያ ለድርጅቱ መቅረብ አለበት፣
- ድርጅቱ የሚፈልጋቸው ሰርተፊኬቶች፣ መረጃዎችና ማስረጃዎች በሙሉ ያለምንም ክፍያ ድርጅቱ በአዘጋጀው ቅፅ ላይ ተሞልተው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከማንኛውም የካሣ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ድርጅቱን በመወከልና በድርጅቱ ወጪ በተፈለገ ጊዜ ሁሉ መድን ገቢው ለጤና ምርመራ መቅረብ አለበት፡፡
- መድን ገቢው ወይም የመድን ገቢው የግል ተወካይ የካሣ ክፍያ መቀበላቸው ድርጅቱን ከኃላፊነት ነፃ ያደርገዋል፡፡ መድን ገቢው ወይም ወኪሉ ድርጅቱን የመክሰስ መብት ፈፅሞ አይኖራቸውም:: መድን ገቢው በሽፋኑ የመጠቀም መብት ያላቸው ከአንድ በላይ የሆኑ ወገኖች ካሉ በጠቅላላው የሚፈፀመው የካሣ ክፍያ መጠን በዚህ የመድን ሽፋን መሠረት ለመድን ገቢው የሚከፈለውን ያህል ብቻ ይሆናል፡፡
- ድርጅቱ በራሱ ወይም በመድን ገቢው ስም በዚህ የመድን ሽፋን መሠረት ከማንኛውም ሦስተኛ ወገን የሚገኝን የካሣ ክፍያ ተፈፃሚነት አረጋግጦ ጠቀሜታውን ለማግኘት በማንኛወም ጊዜ በራሱ ወጪ እንቅስቀሴ ለማድረግ ሥልጣን ይኖረዋል፡፡ ድርጅቱ ለዚህ የሚፈልገውን ማንኛውንም ድጋፍ መድን ገቢው ያደርግለታል፡፡
- በዚህ ውል መሠረት የሚፈፀም ክፍያ ወለድ አይኖረውም፡፡
- ድርጅቱ ከዚህ ውል ጋር በተያያዘ ወይም በዚህ ውል መሠረት ማንኛውንም የክፍያ ትዕዛዝ ወይም የወለድአገድ ማስታወቂያ እንዲቀበል አይገደድም፡፡
- መድን ገቢው የሚያከማውነውን ማንኛውንም ሥራ ተፅዕኖ በሚያሳድር መልኩ ለውጥ ወይም የእንቅስቃሴ ለውጥ ከተከሰተ አግባብ ባለው ጊዜ ውስጥ ለድርጅቱ በፅሑፍ ያሳውቃል፤ እንዲሁም በዚህ ምክንያት ድርጅቱ የሚጠይቀውን ማንኛውንም ተጨማሪ አረቦንም ይከፍላል፡፡
- የመጀመሪያው ወይም የውል ዕድሳት አረቦኑ መድን ገቢው ባቀረበው መረጃ ላይ በመመሰረት የተሰላ ከሆነ መድን ገቢው ትክክለኛና ዝርዝር መረጃዎችን መዝግቦ በመያዝ ድርጅቱ እነዚህን መረጃዎች እንዲመረምር ይፈቅድለታል፡፡ መድን ገቢው እነዚህን መረጃዎች የውል ጊዜው በአበቃ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለድርጅቱ አዘጋጅቶ ያቀርባል፡፡ በዚህ ላይ በመመስረትም አረቦኑ ወይም የእድሳት አረቦኑ ይስተካከላል፡፡
- ድርጅቱ ወይም መድን ገቢው በመጨረሻ በሚታወቅበት አድራሻ የ14 ቀናት ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን መሰረዝ ይችላሉ፡፡ ውል ለመሰረዝ ማስታወቂያ የሰጠው ድርጅቱ ከሆነ መድን ገቢው ሽፋን ያላገኘበት ጊዜ አረቦን ይመለስለታል፡፡ ውል ለመሰረዝ ማስታወቂያ የሰጠው መድን ገቢው ከሆነና በውል ዘመኑ ውስጥ ምንም ዓይነት የካሣ ክፍያ ጥያቄ ካላቀረበ በድርጅቱ የአጭር ጊዜ ስሌት መሠረት የአረቦን ተመላሽ ይደረግለታል፡፡
|