About Us Financial Service Publication Branches News Forms Contact Us Articles FAQ
 

Side Menu



Proposal Forms
-----------------------
Proposal With Medical Certificate
Proposal Without  Medical Certificate
Proposal for Medical Insurance 

Claim Forms 
------------------------
Medical Claim Notification
Accident and Disease Notification
Medical Attendance Certificate
Death Confirmation Form

 
ለገዳይ በሽታዎች ወጪዎች በተጨማሪ የሚሰጥ የሕይወት መድን

በመጀመሪያው የውል መጠየቂያ ሠንጠረዥ ላይ በተገለፀው መሠረት ለድርጅቱ አረቦን በመከፈሉና በሚከተሉት የሚሟሉ ሁኔታዎችና ገደቦች ላይ ተመስርቶ ድርጅቱ ለገዳይ በሽታዎች የሕክምና ወጪ ለመክፈል ተስማምቷል፡፡

 

  1. ጠቀሜታዎች

ለመድን ገቢው የሚሰጠው ጠቀሜታ የሽፋን መጠኑን መሠረት በማድረግ ሲሆን የሚፈፀመው ክፍያ ከፍተኛው የሽፋን መጠኑን 50% ይሆናል፡፡

    1. የተለዩ ሁኔታዎች


ሀ.

የልብ ድካም ሕመም

የደም ቧንቧ በመዘጋቱ ምክንያት የልብ ጡንቻዎች በከፊል ሥራ በማቆማቸው፤ በሽታው ለረዥም ጊዜ የቆየ የደረት ሕመም በማስከተሉና አዲስ ምርመራ ኤሌክትሮ ካርዲዮግራፍ (electrocardiograph) በሚደረግበት ወቅት ለውጥ ቢያመጣና ከልብ የሚመነጨው ኢንዛይም ከትክክለኛው መጠን በልጦ ቢገኝ፣

ለ.

የደም ቧንቧ በሽታ ቀዶ ጥገና

ለደም ቧንቧ በሽታ ሲባል ለተደረገ ቀዶ ሕክምና የደም ሥር ወይም የውስጥ ሕክምና፡፡ ውሉ ሌሎች ቀዶ ሕክምናዎችን አይሸፍንም፡፡

ሐ.

ካንሰር

ከመጠን በላይ ነጭ የደም ሴሎችን በማመንጨት የሚከሰት ስንፈትንና ..የሆድ ኪን.. ¾(hodgkin's) በሽታን ጨምሮ በሕክምና ለመቆጣጠር አዳጋች የሆነና ዕድገቱን ለመቆጣጠር የማይቻል የጭንቅላት ዕጢ መኖር፤ የተረጋገጠ የሴሎች መበከል ወይም በሴሎች ላይ በተደረገ ጥናት እርግጠኛ የሆነ የበሽታው መስፋፋት መኖር፤ ሽፋኑ የሚከተሉትን ሁኔታዎች አያካትትም፡፡
በማህፀን አፍ ላይ የበቀለን እጢ፣ ያላደገን ወይም ገና ማደግ በመጀመር ላይ ያለን የጭንቅላት እጢ፣ ማንኛውም የቆዳ ካንሰር (except malignant melanomas)፣ በደረጃ 1 ላይ የሚገኝ ¾Hodgkin's በሽታ እና ማንኛውም የኤድስ ምልክት የሆነን እጢ፣

መ.

የደም ዝውውር መቋረጥ

ሠ.

የኩላሊት ስንፈት

ሁለቱም ኩላሊቶች ሊድኑ በማይችሉበት የመጨረሻ ደረጃ ላይ በመሆናቸው ተከታታይ የሆነ ደምን የማጣራት ወይም ኩላሊትን የመቀየር ሥራ በመከናወኑ፣

ረ.

የእግር ሽባነት እና የነርቭ ሲስተም መቋረጥ

በጉዳት ወይም በበሽታ ምክንያት የሁለቱም እግሮች እና/ወይም የሁለቱም እጆች የጡንቻ ሥራ ማቆም ወይም መደንዘዝ፤ የአካል ጉድለቱ በተከታታይ ባሉት የ12 ወራት ጊዜ ውስጥ ከተከሰተና ተቀባይነት ባለው የነርቭ ሐኪም ማስረጃ ከተደገፈ፣

ሰ.

የወሳኝ አካል መለወጥ

ተቀባይነት ያለው የልብ፣ የጉበት፣ የሳንባ፣ የኩላሊት፣ የሐሞት ከረጢት፣ የአጥንት ወይም ሌሎች አካላት መለወጥ፣

 

    1. ማግለያዎች

በሽታው በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ በሚከተሉት ሁኔታዎች ምክንያት የተከሰተ ከሆነ ምንም ዓይነት የጠቀሜታ ክፍያ አይፈፀምም

ሀ.

ራስን የማጥፋት ሙከራ በማድረግ ወይም በራስ ላይ ጉዳት በማድረስ ወይም በማንኛውም መንገድ የሕይወት መድን ገቢው ሆን ብሎ በፈፀመው ድርጊት አማካይነት፣

ለ.

አልኮል፣ ዕፅ ወይም መርዝ በመጠቀም በመውሰድ ወይም በጤና ባለሙያ ከሕይወት መድን ገቢው ሌላ ካልታዘዘ በስተቀር በሚወሰድ መድኃኒት፣

ሐ.

ለሽባነት ፓላራይዝድ ተፈፃሚ የሚሆን

  1. የሕይወት መድን ገቢው በፈፀመው የተንኮል ድርጊትና ሕግ መጣስ ወይም

  2. በማንኛውም አደገኛ በሆነ ስፖርት በመሳተፍ ወይም ቋጥኝ ላይ በመውጣት፣ ውሃ ውስጥ በመስጠም፣ ሞተር በሌለው በራሪ ነገር በመንሳፈፍ እና በማንኛውም ዓይነት ፍጥነት ባለው ውድድር በመሳተፍ፡፡
  3. የአደጋው ሥጋት ሽፋን በተሰጠው በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ በሐኪም ለተረጋገጠ በሽታ በዚህ ክፍል ክፍያ አይፈፀምም፡፡ ይህ ማግለያ ዋና የሆነውን የሰውነት አካል መቀየርንና ሽባነትንም ያካትታል፡፡

       

    Home  About Us Financial Indicator Life Insurance Non-Life Insurance Main Branch Forms Contact Us