About Us Financial Service Publication Branches News Forms Contact Us Articles FAQ
 

Side Menu



Proposal Forms
----------------------------
Motor Insurance
Fire Insurance
Personal Accident Insurance 
Workmens Compesation 
Burglarly and House Breaking
Contractors All Risk
Contractors Plant & Machinery
Deterioration of Stock
Electronic Equipment Insurance
Erection All Risk
Inland Carriers Liability
Machinary Loss of Profit
Machinary Insurance
Public Liability
Professional Indemenity
Product Liability 
Fidelity Guaranty
Money Insurance

Claim Notification Forms 
-----------------------------
Motor Insurance
Marine Insurance
Accedent and Disease

 
የባህር ላይ ጉዞ የመድን ዋስትና

መግቢያ

የባህር ላይ ጉዞ የመድን ዋስትና ከዋና ዋናዎቹ የመድን ዋስትና ዓይነቶች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ በዚህ የመድን ዋስትና ሥር የተለያየ ሽፋን የሚሰጡ ልዩ ልዩ ውሎች ያሉ ሲሆን ሽፋን የሚሰጡትም:-

  • ለመርከብና ለማሽነሪዎች
  • ከቦታ ቦታ ለሚጓጓዝ ጭነት
  • ለኃላፊነት ግዴታዎች ነው፡፡

ይሁን እንጂ በዚህ የማብራሪያ ፅሑፍ ውስጥ የምንመለከተው የመርከብ ጭነቶችን ብቻ ሲሆን የመርከብ ጭነትም ሲባል በባህር፣ በአየርና በየብስ የሚተላለፉ ጭነቶችን የሚያካትት መሆኑን መገንዘብ ያሻል፡፡ ስለሆነም ይህ ብሮሸር በዋናነት የሚያብራራው በባህርና በአየር ስለሚጓጓዙ ጭነቶች ነው፡፡

ክፍል 1

የመርከብ ጭነት ዋስትና

የባህር ላይ ጉዞ የመድን ዋስትና የተለየ ባህሪ በዓለም ላይ የሚገኙ የመድን ዋስትና ሰጪዎች በሙሉ የመርከብ ጭነት ደንብ አንቀፅ ሀ፣ ለ እና ሐ የሚል ተመሳሳይ አባባል መጠቀማቸው ነው፡፡ የደንቡ አንቀፆች በዋናነት የሚለያዩት መድን ሰጪዎቹ በሚሰጡት የሽፋን መጠን ነው፡፡ የደንቡ አንቀፅ ሀ ስፋት ያለው ሽፋን ሲሰጥ አንቀፅ ለ እና ሐ የተወሰኑ የአደጋ ሥጋት መንስዔዎችን ያገላሉ፡፡ በውሉ ሽፋን የሚሰጣቸው የአደጋ ሥጋት መንስዔዎች ደንበኛው ሽፋን ለማግኘት በመረጠው አንቀፅፆች ላይ የተመሰረተ ይሆናል፡፡

1.ሽፋን የሚሰጣቸው አደጋ ስጋቶች

1.1በደንቡ አንቀፅ ሀ ሽፋን የሚሰጣቸው:-

ሀ.በማግለያ አንቀፆቹ ከተጠቀሱት በስተቀር ዋስትና በተገባለት ንብረት ላይ ጥፋት ወይም ጉዳት የሚያመጡ የአደጋ ስጋቶች በሙሉ፣
ለ.በማንኛውም ምክንያት የሚደርስን ጥፋት ወይም ጉዳት ለማስወገድ ሲባል የሚወጣውን ወጪ ጨምሮ የጠቅላላውን፣ የአማካዩንና የቅሪቱን ዋጋ፣
ሐ. ይህ ዋስትና በደንቡ አንቀፆች የሚሸፈኑትን ጨምሮ የሁለቱም ወገን ተጠያቂነት (Both to blame collision) በሚለው አንቀፅ ዋስትና ገቢው የሚኖርበትን የኃላፊነት ድርሻ እስከማካካስ ሊራዘም ይችላል፡፡ በዚህ አንቀፅ መሠረት ማንኛውም የካሣ ጥያቄ በመርከቧ ባለቤት ሲቀርብ የቀረበውን የካሣ ጥያቄ አስመልክቶ የሚከሰተውን ወጪ በመሸፈን ዋስትና ገቢውን ወክሎ ለመከላከል መብት ላለው ለኢትዮጵያ መድን ድርጅት ዋስትና ገቢው ያሳውቃል፡፡

1.2በመርከብ ጭነት አንቀፅ ለ ሽፋን የሚሰጣቸው የአደጋ ስጋቶች

ይህ አንቀፅ የሚከተሉትን እንዲሁም በአንቀፅ ሐ የሚሸፈኑትን የአደጋ ሥጋቶች ይሸፍናል፡፡
እነዚህም፡-

  • የመሬት መንቀጥቀጥ፣ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ወይም የመብረቅ አደጋ ፣
  • የባህር፣ የሐይቅ ወይም የወንዝ ውኃ የዕቃ ማጓጓዣ ኮንቴይነር ወደያዘችው መርከብ ወይም ጀልባ ወይም ወደ ዕቃው ማከማቻ በመግባቱ ለደረሰ ጉዳት፣
  • ለማንኛውም በመርከቧ ላይ እያለ ሙሉ በሙሉ ውድመት ለደረሰበት ንብረት ወይም ንብረቱ በመርከብ ወይም በጀልባ በሚጫንበትና በሚራገፍበት ወቅት ለደረሰ ውድመት ሽፋን ይሰጣል፡፡

1.3በመርከብ ጭነት ደንብ አንቀፅ ሐ የሚሸፈኑ የአደጋ ሥጋቶች

በመርከብ ጭነት ደንብ አንቀፅ ሐ መሠረት የተሰጠ የባህር ላይ ጉዞ የመድን ዋስትና ውል ዋስትና በተገባለት ንብረት ላይ በሚከተሉት ሁኔታዎች ጥፋት ወይም ጉዳት ቢደርስ ሽፋን ይሰጣል፡፡

  • በእሳት ወይም በፍንዳታ
  • በመርከቧ ወይም ጀልባዋ ከአለት ጋር በመጋጨት ወይም ጥልቅ ባልሆነ ባህር ውስጥ መሬት በመንካት መነቃነቅ ቢያቅታት፣ ብትሰምጥ ወይም ብትገለበጥ፤
  • የየብስ ማጓጓዣ ቢገለበጥ ወይም መንገዱን ለቆ ከመስመር ቢወጣ፣
  • መርከቧ፣ ጀልባዋ ወይም ሌላው ማጓጓዣ ከውኃ በስተቀር ከሌላ ውጫዊ አካል ጋር ቢጋጭ፣
  • አስቸጋሪ በሆነ ወደብ ላይ ለሚራገፍ ጭነት፣
  • ከአቅም በላይ የሆነ የአደጋ ስጋትን ለመቀነስ ሆን ተብሎ ወደ ባህር በተወረወረ ንብረት ምክንያት የሚደርስ እጦትን፣ ወደመርከቧ በገባ ውኃ ምክንያት ለተበላሸ ዕቃ ወይም መርከቧን ከጉዳት ለማዳን ሲባል ከመርከቧ ወደ ባህር ለተወረወረ ዕቃ

2ጠቅላላ የሚሟሉ ሁኔታዎች

2.1ሽፋን የሚሰጥበት የጊዜ ገደብ
1.ይህ ዋስትና ንብረቱን ማጓጓዝ ከሚጀምርበት መጋዘን ጊዜ ወይም በስም ከተጠቀሰ የማከማቻ ቦታ ዕቃዎቹ ከወጡበት ጊዜ ጀምሮ ከሚከተሉት ነጥቦቹ አንዱ እስኪሟላ ድረስ ተግባራዊ ይሆናል፡፡ በዚህም መሠረት ውሉ፡-

ንብረቱ ለተላከለት ሰው ወይም በውሉ ውስጥ ወደተጠቀሰ መጋዘን ወይም ማከማቻ ቦታ ሲደርስ፣
ውል ገቢው ሊጠቀምበት ከመረጠው መጋዘን ወይም ማከማቻ ውጪ ንብረቱ በመድረሱ በውሉ በተጠቀሰው መድረሻ ቦታ ወይም ከዚያ በፊት ዋስትና ገቢው ሊጠቀምበት በመረጠው በማንኛውም መጋዘን ወይም ማከማቻ ቦታ ንብረቱን ሲረከብ ወይም

  • ንብረቱ ከመደበኛ የመጓጓዝ ሂደት ውጪ ማከማቻ ውስጥ ከገባ ወይም
  • ንብረቱን የማደላደል ወይም የማከፋፈል ተግባር ሲከናወን፣
    ወይም
    ዋስትና የተገባለት ንብረት ከመርከብ ላይ ከተራገፈ በኋላ ውሉ እስከሚቋረጥበት ባሉት 60 ቀናት ድረስ፣ ከሁለቱ ቀድሞ በተፈፀመው ተግባር፣
    መርከቧ የጉዞዋ መጨረሻ ወደሆነው ወደብ በመድረሷ የጫነችውን ንብረት ወደ ሌላ ጫፍ ለማድረስ በሌላ መርከብ ማጓጓዝ ካስፈለገና ይህ ውል ከመቋረጡ በፊት ንብረቱ ወደሌላ መድረሻ ቦታ የሚጓጓዝ ከሆነ ውሉ ከቀጣዩ ጉዞ መነሻ ባሻገር አይራዘምም፡፡
    ከዋስትና ገቢው ቁጥጥር ውጭ በተለየ አጋጣሚ፣ በግዴታ በተፈፀመ የጭነት ማራገፍ፣ እንደገና በመጫን ወይም ጭነት በመለወጥ እንዲሁም የመርከቧ ባለቤት ወይም አከራይ ባለው መብት ምክንያት የጉዞ መዘግየት ቢፈጠር ይህ ዋስትና የፀና ሆኖ ይቆያል፡፡

    2.መርከቧ ከዋስትና ገቢው ቁጥጥር ውጭ በሆነ ምክንያት በውሉ ውስጥ ከተጠቀሰው የጉዞ መድረሻ ወደብ ወይም ቦታ ውጪ በመቆሟ የማጓጓዣው ኮንትራት ቢቋረጥ ወይም ውል ገቢው ንብረቱን ከመረከቡ በፊት ጉዞው ቢቋረጥ ስለሁኔታው ወዲያውኑ ለድርጅቱ እስካልተገለፀና ዋስትናው እንደፀና ቆይቶ ሽፋኑ እንዲቀጥል ጥያቄ እስካልቀረበ ድረስ ይህ ዋስትና ይቋረጣል፡፡

    ይሁንና ሽፋኑ እንዲራዘም ከተጠየቀና ድርጅቱ አስፈላጊውን የአረቦን ክፍያ ማስተካከያ ከተደረገ በኋላ

    በተጠቀሰው ወደብ ላይ ንብረቱ እስከሚሸጥና ገዢው እስከሚረከብ ድረስ ወይም የተለየ ስምምነት ካልተደረገ በስተቀር የውሉ ማብቂያ 6ዐ ቀናት እስከሚጠናቀቅ ወይም
    በተጠቀሰው 60 ቀን ወይም በማንኛውም ስምምነት በተደረገበት የውል ማራዘሚያ ጊዜ ውስጥ ንብረቱ በውሉ ውስጥ ወደ ተጠቀሰው የጉዞ መጨረሻ ወይም ወደ ማንኛውም መድረሻ ቦታ የሚላክ ከሆነ ሽፋኑ ሊቀጥል ይችላል፡፡

    3.ይህ የዋስትና ውል ስምምነት ከተፈፀመ በኋላ ዋስትና ገቢው ንብረቱ የሚራገፍበትን ቦታ ቢቀይር፣ ሁኔታውን ወዲያውኑ ለድርጅቱ ከገለፀ የአረቦንና የሚሟሉ ሁኔታዎች ማስተካከያ ተደርጐ ሽፋኑ ሊቀጥል ይችላል፡፡

    3.ማግለያዎች

    የሚከተሉት ማግለያዎች በሁሉም የደንቡ አንቀፆች ስለ ጭነት በሚገልፁት አንቀፆች ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡

    ሀ.ይህ ዋስትና በማንኛውም መንገድ

    • በዋስትና ገቢው በጎ ፈቃድ ላይ በተመሰረተ ምክንያት ለደረስ ጥፋት፣ ጉዳት ወይም ወጪ፤
    • ዋስትና በተገባለት ንብረት ላይ ሰርጎ በገባ ውኃ (leakage) በክብደት ወይም መጠን መቀነስ፣ በአገልግሎት ምክንያት ለሚፈጠር የማለቅና የመበጣጠስ ሁኔታ ለሚደርስ ጉዳት፣
    • ዋስትና የተገባለት ንብረት በበቂ ወይም በተገቢው ሁኔታ ባለመጠቅለሉ ወይም ለመጓጓዝ በሚያመች ሁኔታ ባለመዘጋጀቱ ምክንያት ለሚደርስ ጥፋት፣ ጉዳት ወይም ወጪ፣
    • ዋስትና በተገባለት ንብረት ውስጣዊ ባህሪ ምክንያት ለሚደርስ ጥፋት፣ ጉዳት ወይም ወጪ፣
    • ምንም እንኳን በመዘግየት የሚመጣ ጉዳት ዋስትና የሚሰጠው ቢሆንም መዘግየት ዋናው ምክንያት ለሆነበት ጥፋት፣ ጉዳት ወይም ወጪ፣
    • በመርከቧ ነጂ፣ በመርከቧ ባለቤት፣ ሥራ አስኪያጅ ወይም በሙሉ ኃላፊነት (Charterers) በተረከበ አካል ሊከፈል ባልቻለ ዕዳ ወይም በተገባው ቃል መሠረት ክፍያው ሊፈፀም ባለመቻሉ ምክንያት ለተፈጠረ ጥፋት፣ ጉዳት ወይም ወጪ፣
    • ማንኛውንም ለጦርነት የሚያገለግል መሣሪያን አውቶሚክ ወይም የኑክለር ኃይልን ለመለያየት/ለማዋሃድ ወይም ሌሎች መሰል የማብላላት ተግባር ወይም የራዲዮ አክቲቭ ኃይል ወይም ንጥረ ነገርን ከመጠቀም በመነጨ ለሚከሰት ጥፋት፣ ጉዳት ወይም ወጪ ሽፋን አይሰጥም፡፡


    ለ.ዋስትና የተገባለት ንብረት በተጫነበት ወቅት ዋስትና ገቢው ወይም የዋስትና ገቢው ሠራተኞች የመርከቧን ወይም የጀልባዋን ለባህር ጉዞ ብቁ አለመሆን ሚስጥር የማያውቁ ካልሆነ በስተቀር ይህ ዋስትና በምንም ሁኔታ መርከቧ ወይም ጀልባዋ ለባህር ላይ ጉዞ ብቁ ባለመሆኗ ምክንያት በጫነችው ንብረት ወይም ኮንቴይነር ላይ ለተፈጠረ ጥፋት፣ ጉዳት ወይም ወጪ ሽፋን አይሰጥም፡፡
    ሐ.ዋስትና ገቢው ወይም የእሱ ሠራተኞች የመርከቧን ለባሕር ላይ ጉዞ ብቁ አለመሆን ሚስጥር የማያወቁ ካልሆነ በስተቀር መርከቧ ዋስትና የተገባለትን ንብረት ለመጫን ላላት ብቃትና ለባህር ላይ ጉዞ ብቁ ስለመሆኗ የተሰጠው የተጠቀሰው ማረጋገጫ ተጥሶ ከተገኘ ድርጅቱ ውሉን ይሰርዛል፡፡
    መ.ይህ ዋስትና በማንኛውም ሁኔታ በሚከተሉት ምክንያቶች ለሚደርስ ጥፋት፣ ጉዳት ወይም ወጪ ሽፋን አይሰጥም፡፡
    • በጦርነት፣ በእርስ በርስ ጦርነት፣ በሽብር፣ በአመጽ፣ በሁከት ወይም በእርስበርስ ብጥብጥ ወይም በማንኛውም በጠብ ወዳድ ኃይሎች በተፈፀመ የጥላቻ ድርጊት፣
    • በምርኮ፣ በድንገተኛ በሽታ፣ በእስር፣ በማዘግየት ወይም በማንኛውም ተመሳሳይ ሙከራ፣
    • ሰዎች በጣሉት ቶር��ዶ ቦምብ ወይም የጦር መሣሪያ ለደረሰ ጉዳት ፡፡


        ሠ.ይህ ዋስትና በማንኛውም ሁኔታ በሚከተሉት ምክንያቶች ማለትም

        • የሥራ ማቆም አድማ ባደረጉ ሰዎች፣ ከሥራ በተሰናበቱ ሠራተኞች ወይም በሠራተኞች ረብሻ ውስጥ ተሳታፊ በሆኑ ሰዎች፣ በብጥብጥ ወይም በሕዝባዊ አመጽ ምክንያት ለደረሰ ጉዳት፣
        • በአድመኞች፣ ከሥራ በተሰናበቱ ሠራተኞች፣ በሠራተኞች ረብሻ፣ ብጥብጥ ወይም ሕዝባዊ አመፅ መነሻ ለሆነበት ጥፋት፣ ጉዳት ወይም ወጪ፣
        • በማንኛውም አሸባሪ ወይም በማንኛውም የፖለቲካ ዓላማ ባለው ሰው ለተፈፀመ ድርጊት ሽፋን አይሰጥም
          በሚከተለው ምክንያት ለደረሰ ጉዳት በደንቡ አንቀፅ ለ እና ሐ ሽፋን አይሰጠውም፡፡ ዋስትና በተገባለት ንብረት ላይ ሆን ተብሎ ወይም በስህተት በማንኛውም ሰው ወይም ሰዎች ለተፈፀመ ጉዳት ወይም ጥፋት

        4.የካሣ ክፍያ ሥርዓት

        1.በዚህ ዋስትና መሠረት ጥፋት ወይም ጉዳት በደረሰ ጊዜ የካሣ ክፍያ ለማግኘት ዋስትና ገቢው ዋስትና ለተገባለት ንብረት የመድን ዋስትና የመግዛት ሕጋዊ መብት ሊኖረው ይገባል፡፡

        2.የዋስትናው የኮንትራት ውል ከመፈረሙ በፊት የተከሰተ አደጋ ቢኖርና፤ ለቀረበ የካሣ ጥያቄ ዋስትና ገቢው አውቆት ድርጅቱ ሳያውቀው የቆየ ካልሆነ በስተቀር፤ ዋስትና ለተገባለት ንብረት በውል ዘመኑ ውስጥ ዋስትና ገቢው ሽፋን የማግኘት መብት አለው፡፡

        3.በዚህ ዋስትና ሽፋን በተሰጠው አደጋ መከሰት (Operation) ምክንያት ዋስትና የተገባለት ንብረት በውሉ ወደተጠቀሰው ወደብ ወይም ማራገፊያ ቦታ ከመድረሱ በፊት ጉዞው ቢቋረጥ ዋስትና የተገባለትን ንብረት ለማራገፍ፣ ለማከማቸትና ዋስትና ወደ ተገባለት መድረሻ ቦታ ለማመላለስ ዋስትና ገቢው ያወጣውን ተገቢ የሆነ ተጨማሪ ወጪ ድርጅቱ ይተካል፡፡

        4.ዋስትና ገቢው ዋስትና የተገባለትን ንብረት ለድርጅቱ በማስረከብ ሙሉ የጉዳት ካሣ ለመጠየቅ የሚችለው፣ በንብረቱ ላይ ሙሉ ጉዳት የመድረሱን ሁኔታ ለማስወገድ/ለማስቀረት የማይቻል ከሆነና የደረሰው ጉዳት ሙሉ ካሣ የማያስከፍል፤ ወይም ንብረቱን ለማስጠገን፣ ለማጓጓዝ በሚመች ሁኔታ ለመመለስና ንብረቱን በመጨረሻ ወደሚደርስበት ሥፍራ ለማጓጓዝ የሚጠይቀው ወጪ በውሉ ውስጥ እተጠቀሰው ቦታ ሲደርስ ለሙሉ የጉዳት ካሣ ከሚከፈለው ዋጋ በልጦ ከተገኘ ነው፡፡


        ሀ.በተጨማሪ ለሌሎች አነስተኛ ንብረቶች መድን ገቢው በውሉ ውስጥ በዝርዝር ከተጠቀሱት ዋስትና (Increased Value Insurance) የሚገባ ከሆነ ስምምነት የተደረገበት የጭነት ዋጋ በዚህ ውል ዋስትና የተሰጠውን መጠን እንዲጨምር ያደርገዋል፡፡ በመሆኑም ጉዳቱንና ኃላፊነቱን የሚሸፍነው የተጨማሪ ዋጋ ዋስትና በጠቅላላው ዋስትና የተገባለትን ንብረት መጠን እንዲጨምር ያደርገዋል፡፡

        በካሣ ክፍያ ወቅት ዋስትና ገቢው በዋናነት ዋስትና ከተገባላቸው ንብረቶች በተጨማሪ ለሌሎች ንብረቶች ስለተገባው የዋስትና መጠን የሚገልፅ ማስረጃ ለድርጅቱ ያቀርባል፡፡
        ለ.ዋስትናው የሌሎች አነስተኛ ንብረቶችን ዋስትና (Increased Value Insurance) የሚያካትት ከሆነ የሚከተለው አንቀጽ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

        ስምምነት የተደረገበት የጭነት ዋጋ መጀመሪያ በተገባው ዋስትና መሠረት ዋስትና ከተገባለት ጠቅላላ መጠን ጋር እኩል እንደሆነ ይቆጠራል፡፡ ዋስትና ገቢው በጭነቱ ላይ ተፈፃሚ የሚያደርጋቸውና ለጥፋቱ ወይም ለጉዳቱ ሽፋን የሚሆኑት የሌሎች አነስተኛ ንብረቶች ዋስትናዎች እና በዚህ ውል በዋናነት ለተቀመጠው ንብረት የተሰጠው ዋስትና ኃላፊነት ጠቅላላ ዋስትና የተገባለትን መጠን ድርሻ ይሆናል፡፡

        በካሣ ክፍያ ወቅት ዋስትና ገቢው ለንብረቱ በሌሎች ዋስትናዎች የተገባለትን መጠን የሚገልፁ ማስረጃዎችን ለድርጅቱ ያቀርባል፡፡

        5.ዋስትናው ስለሚያስገኛቸው ጥቅሞችና ጉዳትን ስለመቀነስ

        1.ይህ ዋስትና ለአጓጓዡ ወይም ለሌሎች ንብረቱን በመያዣነት ለያዙ ወገኖች ሽፋን አይሰጥም፡፡
        2.የጉዳት ካሣ ሊያስከፍል የሚችል ጉዳትን በተመለከተ
        ሀ.ጉዳቱን ለማዳን ወይም መጠኑን ለመቀነስ ሲባል ተገቢ እርምጃዎችን መውሰድና፣
        ለ.የአጓጓዦቹ ወይም የሌሎች የሶስተኛ ወገን መብቶች በሥርዓቱ የተጠበቁና ይህም በተግባር ላይ የዋለ መሆኑን ማረጋገጥ የዋስትና ገቢው፣ የሠራተኞቹና የወኪሎቹ ተግባራት ናቸው፡፡

        3.ዋስትና የተገባለትን ንብረት ለመጠበቅ፣ ለመከላከል ወይም ወደነበረበት ሁኔታ ለመመለስ በሚሉ ዓላማዎች በዋስትና ገቢው ወይም በድርጅቱ የተወሰዱ እርምጃዎች የሁለቱንም ወገኖች መብት የሚከለክሉ፣ የሚሰጡ ወይም የሚቀንሱ ተደርገው አይቆጠሩም፡፡

        6.መዘግየትን ማስወገድ

        ዋስትና ገቢው በማንኛቸውም በሱ ቁጥጥር ሥር ባሉ ሁኔታዎች ሁሉ ንብረቱ በተገቢው መንገድ እንዲጫን ማድረግ በዚህ ዋስትና መሠረት ሊሟላ የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡

        7.ሕግና ደንብ

        ይህ የመድን ዋስትና በኢትዮጵያ ሕግና ደንብ መሠረት የሚፈፀም ይሆናል፡፡

        ክፍል 2

        በአውሮኘላን ለሚጓጓዝ ጭነት የሚያገለግል አንቀፅ በፖስታ መላክን አይመለከትም

        የሚሰጠው ሽፋን፣ ማግለያዎቹ፣ የካሣ ክፍያው ሥርዓት፣ ዋስትናው የሚያስገኘው ጠቀሜታና ሌሎችም መሟላት የሚገባቸው ሁኔታዎች ከመርከብ ጭነት ዋስትና ጋር ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ልዩነታቸው የሚጓጓዘው ዕቃ በውሉ በተጠቀሰው ሥፍራ ከመድረሱ በፊት በሚፈጠር ሁኔታ የኮንትራቱን ውል መሰረዝን በሚመለከተው አንቀፅ ላይ ነው፡፡

        በአውሮኘላን በሚደረግ የጭነት ማጓጓዝ የመድን ዋስትና ከዋስትና ገቢው ቁጥጥር ውጭ በሆነ ምክንያት በውሉ ውስጥ በተጠቀሰው የጉዞ መድረሻ ቦታ ከመድረሱ በፊት ለማጓጓዝ የተገባው ኮንትራት ቢቋረጥ ወይም ውል ገቢው ንብረቱን ከመረከቡ በፊት ጉዞው ቢቋረጥ ስለሁኔታው ወዲያውኑ ለውል ሰጪው እስካልተገለፀና ዋስትናው እንደፀና ቆይቶ ሽፋኑ እንዲቀጥል ጥያቄ እስካልቀረበ ድረስ ይህ ዋስትና ይቋረጣል፡፡ ሆኖም ተጨማሪ አረቦን የሚያስከፍል ከሆነና ውል ሰጪው ከጠየቀ


        ሀ.ዋስትና የተገባለት ንብረት በተጠቀሰው ቦታ ላይ እስከሚሸጥና ገዢው ንብረቱን እስከሚረከብ ድረስ ወይም የተለየ ስምምነት ካልተደረገ በስተቀር የውሉ ማብቂያ 3ዐ ቀናት እስካልተላለፈ ድረስ፣ ወይም
        ለ. በተጠቀሰው 3ዐ ቀን ወይም በማንኛውም ስምምነት በተደረገበት የውል ማራዘሚያ ጊዜ ውስጥ ወይም በአውሮኘላን ለሚጓጓዘው ንብረት በሚያገለግለው አንቀፅ ውስጥ ስለሽፋኑ መቆያ የተጠቀሰው የጊዜ ገደብ እስካበቃ ድረስ ዋስትና የተገባለት ንብረት በውሉ ውስጥ ወደተጠቀሰው የጉዞ መጨረሻ ወይም ወደ ማንኛውም መድረሻ ቦታ የሚላክ ከሆነ ተጨማሪ የሽፋን ጊዜ ሊሰጥ ይችላል፡፡

        ሌሎች አንቀፆች

        በባህር ላይ ጉዞ ዋስትና በአንቀፅ ሀ፣ ለ፣ እና ሐ ላይ ከተገለፁት በተጨማሪ በአመፅ እና በጦርነት ለሚመጡ ጉዳቶች ሽፋን የሚሰጡ ሌሎች አንቀፆችም አሉ፡፡ እነዚህ የአደጋ ሥጋቶች በተጨማሪ የአረቦን ክፍያ የሚሸፈኑ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ የአመፅ ድንጋጌ እና የጦርነት ድንጋጌ በመባል ይታወቃሉ፡፡

        የአመፅ ድንጋጌ በየትኛውም ቦታ ሽፋን የሚሰጥ ሲሆን የጦርነት ድንጋጌ ግን በባህር ላይ ለ15 ቀናት ብቻ ሽፋን ይሰጣል፡፡ የአመፁ ድንጋጌ የሽፋን ጊዜ ከሌሎቹ አንቀፆች ማለትም ከአንቀፅ ሀ፣ ለ፣ እና ሐ የተለየ አይደለም፡፡

        ማሳሰቢያ፡-
        ይህ ፅሑፍ በመርከብ ስለሚጓጓዝ ንብረት የመድን ዋስትና ለማብራራት ቀረበ እንጂ በሕግ ፊት የሚፀና ውል አይደለም፡፡

           

        Home  About Us Financial Indicator Life Insurance Non-Life Insurance Main Branch Forms Contact Us