About Us Financial Service Publication Branches News Forms Contact Us Articles FAQ
 

Side Menu



Proposal Forms
----------------------------
Motor Insurance
Fire Insurance
Personal Accident Insurance 
Workmens Compesation 
Burglarly and House Breaking
Contractors All Risk
Contractors Plant & Machinery
Deterioration of Stock
Electronic Equipment Insurance
Erection All Risk
Inland Carriers Liability
Machinary Loss of Profit
Machinary Insurance
Public Liability
Professional Indemenity
Product Liability 
Fidelity Guaranty
Money Insurance

Claim Notification Forms 
-----------------------------
Motor Insurance
Marine Insurance
Accedent and Disease

 
የገንዘብ የመድን ዋስትና ውል

መድን ገቢው የዚህ ውል አካል በሆኑት የውል መጠየቂያና የውል ማረጋገጫ ቅጽ መሠረት የገንዘብ መድን ዋስትና ጥያቄ በማቅረቡና ተገቢውን አረቦን በመክፈሉ ወይም ለመክፈል በመስማማቱ ዋስትናው የሚሰጠው ሽፋን ተጠቃሚ ይሆናል፡፡

ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ማግለያ አንቀጾች (exclusions) ውጪ የውል ተቀባዩ ገንዘብ ወይም እሱ ኃላፊነት ለወሰደበት ገንዘብ በውል ዘመኑ ውስጥ በማንኛውም ጊዜ ለሚደርስ ማንኛውም ጥፋት ወይም ጉዳት ከኃላፊነት ጣሪያው ያልበለጠ ክፍያ ለመፈፀም ተስማምቷል፡፡

የገንዘብ የመድን ዋስትና የሽፋን ሁኔታ እንደሚከተለወው ይሆናል፡-

- ከቤት ከድርጅት ወደ ባንክ፣
- ከባንክ ወደ ቤት ድርጅት፣
- ሌሎች የገንዘብ እንቅስቃሴዎች፣
- በካዝና ላይ በሌቦች ወይም ዘራራፊዎች ለሚደርስ ጥፋት ወይም ጉዳት፡፡

ማግለያ አንቀጾች (Exclusions)

ድርጅቱ በሚከተሉት ሁኔታዎች ኃላፊነት አይወስድም፡-

ሀ) በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ለውጤቱ መንስኤ ለሆነ ጦርነት፣ ወረራራ፣ የውጭ ጠላት ድርጊት፣ ጦርነት መሰል ብጥብጦች ጦርነት ቢታወጅም ባይታወጅም የርስበርስ ጦርነት፣ ብጥብጥ፣ ሥራራ ማቆም የወታደር ወይም የሕዝብ መነሳሳት፣ ስልጣን ንጥቂያና ዝርፊያ ወ.ዘ.ተ

ለ) እምነት ባጐደለ የውል ተቀባይ ሠራራተኛ ወይም ተላላኪ ለደረሰ ጉዳት፣

ሐ 1. በስሕተት ወይም በግድፈት ለደረሰ ጉድለት፣

2. በዋጋ መቀነስ ምክንያት ለደረሰ ጉድለት፣

መ)  በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ በኑክሊየር መሣሪያ ጨረር ራራዲዮ አክቲቭ ብክለትና ከማንኛውም የኑክሊየር ነዳጅ ወይም ኑክሊየር ዝቃጭ ወይም ከኑክሊየር ነዳጅ መንደድ በተነሳ ለደረሰ ጉዳት ወይም መባባስ፣

ሠ ከኢትዮጵያ ውጭ ለደረሰ ጉዳት፣

ረ) በሌላ የመድን ውል ወይም ውሎች ዋስትና ለተሰጠ ጉዳት ወይም ጥፋት፣

ሸ) ጥበቃ ባልተደረገለት ተሽከርካሪ ለደረሰ ጥፋት፣

የሚሟሉ ሁኔታዎች (Conditions)

1. ይህ ውልና የውሉ ሰንጠረዥ (Schedule) አይነጣጠሉም፡፡ ለአንድ ቃል ወይም ገለፃ የተለየ ትርጉም በውሉ ወይም በውሉ ሠንጠረዥ ውስጥ ከተሰጠው ይሄው ትርጓሜ ለቃሉ ወይም ለገለፃው በተገኘበት ቦታ ሁሉ ተጠቃሽ ይሆናል፡፡

2. ውል ተቀባዩ ለገንዘቡ ደህንነት ተገቢውን ጥንቃቄ ያደርጋል፡፡

3. የካሣ ጥያቄ የሚያስነሳ ጉዳይ ቢከሰት ውል ተቀባዩ፡-

ሀ) ስለጉድለቱ ወዲያውኑ ለፖሊስ ያሳውቃል፡፡ በተጨማሪም የጠፋውን ንብረት ለማግኘትና አጥፊውም ተይዞ ቅጣቱን እንዲያገኝ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል፡፡

ለ)  መድን ገቢው ስለክስተቱ ወዲያውኑ ለድርጅቱ በጽሑፍ ያሳውቃል፡፡ እንዲሁም በ15 ቀናት ውስጥ ወይም ድርጅቱ በፈቀደው ተጨማሪ ቀናት ውስጥ ዝርዝር የካሣ ጥያቄ ያቀርባል፡፡ በተጨማሪም ገለፃዎችን፣ ቫውቸሮችን፣ የሂሣብ መዝገቦችን፣ የባለቤትነት ማረጋገጫና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ የካሣ ጥያቄውን የሚደግፉ መረጃዎችንና አስፈላጊም ከሆነ ስለካሣ ጥያቄው እውነተኛነት ሕጋዊ ማረጋገጫ ጭምር ያቀርባል፡፡ ጉዳት ለመድረሱ በ7 ቀናት ውስጥ ድርጅቱ እንዲያውቀው ካልተደረገ ድርጅቱ ኃላፊ አይሆንም፡፡

የቀረበው የካሣ ጥያቄ የማጭበርበር ወይም ሆን ብሎ በማጋነን ወይም የሀሰት ማስረጃ በደጋፊነት የቀረበበት ከሆነ ድርጅቱ ለቀረበው የካሣ ክፍያ ጥያቄ ኃላፊ አይሆንም፡፡

4. ድርጅቱ በራራሱ ወይም በመድን ገቢው ስም የጠፋውን ንብረት መልሶ ለማግኘት ወይም ጉድለቱ እንዲተካለት ለማድረግ ይችላል፡፡ ውል ተቀባዩም ለድርጅቱ መረጃ ማቅረብና ተገቢ ትብብር ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ የካሣ ክፍያ ከተፈፀመ በኋላ የሚገኝ ማንኛውም ንብረት የድርጅቱ ይሆናል፡፡ ሆኖም ከተከፈለው ካሣ መብለጥ የለበትም፡፡

5. የአረቦን ክፍያው የተሰላው መድን ገቢው ባቀረበው ግምት ላይ ተመርኩዞ ከሆነ መድን ገቢው ትክክለኛ መዝገብ መያዝና ድርጅቱ በፈለገ ጊዜ መዝገቦችን እንዲመረምር መፍቀድ ይኖርበታል፡፡ መድን ገቢው እያንዳንዱ የውል ዘመን ከማለቁ በፊት ባለው የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ድርጅቱ የጠየቀውን መረጃ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ የውል ዘመኑ የአረቦን ስሌት ሲስተካከል ልዩነቱ ለመድን ገቢው ይመለሳል ወይም ቀሪውን እንዲከፍል ይደረጋል፡፡

6. መድን ገቢው የዚህን ውል ግዴታዎችና አንቀጾች እንዲሁም በውሉ ውሰጥ የተካተቱትን ተጨማሪ ስምምነቶች (endorsement) ማሟላትና ማክበር ካሣ ለማግኘት ያለውን መብት ለማስከበር እንደ ቅድመ ሁኔታ ይቆጠራራል፡፡ መድን ገቢው በቅድመ ውል መጠየቂያው ቅጽ ላይ ወይም በውል እድሳት ወቅት የሰጠው ቃል ወይም ከካሣ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ያቀረበው ቃል የተሳሳተ ከሆነ ወይም ሆን ብሎ ከእውነተኛው ሂሳብ በላይ ከጠየቀ የመድን ውሉ ውድቅ ይሆናል፡፡ የተከፈለውም አረቦን ተመላሽ አይሆንም፡፡

7. ድርጅቱ መድን ገቢው ባስመዘገበው አድራራሻ የአሥራራ አምስት ቀን ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን ሊሰርዝ ይችላል፡፡ በዚህ ሁኔታ አረቦኑ ከላይ በአንቀጽ 5 በተሰጠው መሠረት ይስተካከላል፡፡

8. ከዚህ የመድን ውል በመነጨ ማንኛውም አለመግባባት ቢፈጠርና ድርጅቱ ከጠየቀ ጉዳዩ በሕጉ መሠረት በግልግል ዳኞች የሚታይ ይሆናል፡፡

9. ድርጅቱ ከዚህ ውል በመነጨ የመብት ዝውውርን በተመለከተ እስካላፀደቀው ድረስ እንዲቀበል አይገደድም፡፡

ማሳሰቢያ፡- ይህ ጽሑፍ ስለየገንዘብ የመድን ዋስትና የቀረበ ማብራራሪያ እንጂ በሕግ ፊት የሚፀና ፖሊሲ አይደለም፡፡

   

Home  About Us Financial Indicator Life Insurance Non-Life Insurance Main Branch Forms Contact Us