የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ከ30 በላይ ሕይወት ነክ ያልሆኑ የመድን ዋስትናዎችን ይሰጣል፡፡ ሕይወት ነክ ያልሆኑ ዋስትናዎች የሚያገለግሉት ለንብረትና ለህጋዊ ኃላፊነት ነው፡፡ ድርጅቱ ዋስትናዎቹን በየጊዜው በመፈተሸ የማሻሻል ሥራ (revise) ያከናውናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የወቅቱ የአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት የሚጠይቀውንና በደንበኞች ፍላጎት ላይ የተመሰረተ አዳዲስ የዋስትና ዓይነቶችን በመቅረፅ ገበያ ላይ ያውላል፡፡
ለአብነት ያህል በአሁኑ ጊዜ፣የአበባ፣ የጋራ መኖሪያ ቤት፣ የቡናና ሻይ፣በዝናብ እጥረት ለሚደርስ የምርት መቀነስ፣ ለግብርና ውጤቶች የመጋዘን ባለቤቶች የክምችት ኃላፊነት የሚያገለግሉ ዋስትናዎች ቀርፆ አቅርቧል፡፡ ድርጅቱ በዋናነት ከሚሰጣቸው የንብረትና የኃላፊነት ዋስትናዎች ውስጥ የማንኛውም አደጋ፣የአዬሸን (ለጭነቱና ለአይሮፕላኑ)፣ የባንኮች ሁሉን አቀፍ ዋስትና፣ ቤት ሰብሮ ለሚፈፀም ዝርፊያ፣ የቦንድ፣ የጋራ መኖሪያ ቤት፣ የትርፍ እጦት፣ የአዝርዕት፣ የኢንጂነሪንግ፣ የእምነት ማጉደል፣የእሳትና የመብረቅ፣ በትራንዚት ለሚተላለፉ ዕቃዎች፣ የአጓጓዦች ኃላፊነትጓ የእንስሳት፣ የማሪን፣ (ለጭነቱና ለመርከቡ)፣የገንዘብ፣ የተሸከርካሪ፣ የግል (የቡድን አደጋ፣ የመስታወት፣ የምርት ኃላፊነት፣ የሙያ፣ የሦስተኛ ወገን (ሕጋዊ) ኃላፊነት፣ የሠራተኛ ጉዳት ካሣ እና ሌሎች የመድን ዋስትናዎች ይገኙበታል፡፡ |