· በድርጅቱ የተዘጋጀውን የውል መጠየቂያ ቅጽ በጥያቄው መሠረት በጥንቃቄ መሙላት፣ · አንድ ጊዜ የእምነት ማጉደል ያደረሰ ሠራተኛ¼‰t®C ዳግም በውሉ ሊሸፈን /ሊሸፈኑ አይችልም፣ · ሌሎች መረጃዎች ወይም ሠነዶች እንደ አስፈላጊነቱ ሊጠየቁ ይችላሉ፣
በዕምነት ማጉደል መድን (Fidelity Guarantee Policy) ለሚደርሱ አደጋዎች መቅረብ ያለባቸው ዋና ዋና ማስረጃዎች
1 . የዕምነት መጉደሉ እንደደረሰ ወዲያውኑ ለሚመለከተው ቅርንጫፍ ማሳወቅ 2 . ዕምነት ያጐደለው ሠራተኛ መተማመኛ ካልፈረመ የፖሊስ ሪፖርት፣ 3 . የኦዲተር ሪፖርት ማቅረብ፣ 4 . ዕምነት ያጐደለው ሠራተኛ መተማመኛ ካልሰጠ የፍርድ ቤት ውሳኔ፣ 5 . ለዕምነት አጉዳዩ የሚከፈል ገንዘብ ካለ ምሳሌ ደመወዝ አበል ወዘተ የተያዘ መሆኑን ማረጋገጫ ጽሁፍ፣ 6 . የዕምነት አጉዳዩ ትክክለኛ አድራሻ፣ ከተማ፣ ከፍተኛ፣ ቀበሌ፣ የቤት ቁጥር 7 . የዕምነት አጉዳዩ ተንቀሳቃሽ ወይም የማይንቀሳቀስ ንብረት ካለው እንዲገለጽ ማድረግ፣ 8 . ለጠፋው ገንዘብ ለድርጅቱ የመዳረግ መብት (Subrogation Right) መስጠት፣ · ሌሎች መረጃዎች ወይም ሰነዶች እንደ አስፈላጊነቱ ሊጠየቁ ይችላል፡፡
|