የግል ተሽከርካሪ የመድን ዋስትና ውል
መድን ገቢው የዚህ ውል አካል በሆኑት የውል መጠየቂያ እና የውል ማረጋገጫ ቅፅ መሠረት ዋስትና ለመግዛት ለኢትዮጵያ መድን ድርጅት ከዚህ በኋላ ድርጅት እየተባለ ለሚጠራራው ጥያቄ በማቅረቡና ተገቢውን አረቦን በመክፈሉ ወይም ለመክፈል በመስማማቱ ይህ ዋስትና ለሚሰጠው ሽፋን ተጠቃሚ ይሆናል፡፡
ይህ ፖሊሲ በውሉ ውስጥ የተካተቱት ገደቦች፣ የሚሟሉ ሁኔታዎች፣ ብያኔዎች ከዚህ በኋላ በጥቅሉ የፖሊሲው ውሎች የሚባሉት እንደተጠበቁ ሆነው በውሉ ወቅት ለሚፈጠሩ ክስተቶች ማስረጃ ይሆናል፡፡
ክፍል አንድ
የተሽከርካሪ ዋስትና
1.የመድን ዋስትና በተገባለት ተሽከርካሪ ላይ ጉዳት ወይም ውድመት መድረስ፣
ድርጅቱ የመድን ዋስትና በተገባለት ተሽከርካሪና ተጓዳኝ /accessories/ መሣሪያዎች ላይ በሚከተሉት ሁኔታዎች ለሚደርስ ጉዳት ወይም ጥፋት የካሣ ክፍያ ይፈጽማል፤
ሀ.በድንገተኛ ግጭት ወይም መገልበጥ ወይም በመካ��ካል ብልሽት ወይም በእርጅና ምክንያት ለደረሰ ግጭት ወይም መገልበጥ፣ ይሁንና የመድን ዋስትና የተሰጠው ተሽከርካሪ አብሮ ካልተጎዳ በስተቀር በጐማዎች ላይ የሚደርስን ጉዳት ወይም ውድመት አይሸፍንም፤
ለ.በእሳት፣ ከውጭ በደረሰ ፍንዳታ፣ በውስጣዊ አካል መቀጣጠል፣ በመብረቅ፣ በሌብነት ወይም በሌብነት ሙከራራ፣ ሐ.ባለንብረቱን ለመጉዳት ሆን ብሎ ተሽከርካሪውን በማውደም /በመጎዳት
መ.በመጓጓዝ ላይ እያለ ማጓጓዙ በማጓጓዝ ሂደት የማይቀረውን የመጫንና የማውረድ ሂደትንም ይጨምራራል በመንገድ ላይ፣ በባቡር፣ ወን/ማንኛውንም ውኃ በማሻገር ላይ፣ በሊፍት ወይም በአሳንሰር በመጓጓዝ ላይ እያለ፣
ሠ.የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ የአውሎ ነፋስና የእሳተ ጐሞራራ ፍንዳታ፣ የመሬት መንቀጥቀጥና የመሳሰሉትን ከሰው ልጅ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ የተፈጥሮ ክስተቶችን ሳይጨምር በተሽከርካሪው ላይ በወደቀ አካል ለደረሰ ጉዳት ወይም ጥፋት፣
2.የኃላፊነት መጠን
በውል ሠንጠረዡ ውስጥ የተጠቀሰ ማንኛውም ተሽከርካሪ ጉዳት ወይም ጥፋት ቢደርስበት ድርጅቱ በራራሱ ምርጫ ተሽከርካሪውን ወይም ተለዋጭ ዕቃዎቹን ማደስ፣ መተካት ወይም የጉዳቱን ወይም የጥፋቱን መጠን በጥሬ ገንዘብ መክፈል ይችላል፡፡ ሆኖም የድርጅቱ ኃላፊነት አደጋው በደረሰበት ወቅት የተጐዱ ወይም የጠፉ ተለዋጭ ዕቃዎችን ትክክለኛ ዋጋ ዕቃዎቹን በተሽከርካሪው ላይ ለመግጠም ከሚጠየቀው ተቀባይነት ካለው የእጅ ዋጋ አይበልጥም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የተሽከርካሪው ዋጋ/መለዋወጫ ዕቃዎችን ጨምሮ/ በማንኛውም ሁኔታ መድን ገቢው በሠንጠረዡ ላይ ከገለጹት ግምት ወይም የገበያ ዋጋ መብለጥ የሌለበት ሲሆን ድርጅቱ የሚከፍለው አነስተኛ ሆኖ ያገኘውን ይሆናል፡፡
3.ከአደጋ በኋላ ስለሚከናወን የጥበቃና የማጓጓዝ ሥራ
በውሉ ውስጥ የመድን ዋስትና ሽፋን እንደሚሰጠው በተጠቀሰ ድንገተኛ አደጋ ምክንያት ጉዳት ወይም ውድመት የደረሰበት ተሽከርካሪ በአደጋው ምክንያት መንቀሳቀስ ባይችል ድርጅቱ ለጥበቃና በቅርብ ወደሚገኝና ብቃት ወዳለው ጋራራዥ ለማጓጓዝ የሚያስፈልገውን ወጪ ይሸፍናል፡፡ ሆኖም ይህ ወጪ ለተሽከርካሪው ጥገና ከሚያስፈልገው ወጪ ከ20% አይበልጥም፡፡
4.በዱቤ የተገዛ ወይም በዕዳ ማስከበሪያነት የተያዘ ተሽከርካሪ
ዋስትና የተገባለት ተሽከርካሪ በዱቤ የተገዛ ወይም ለዕዳ ማስከበሪያ በዋስትና የተያዘ ከሆነ ማንኛውም ክፍያ በውል ሰነዱ ውስጥ በባለቤትነት ለተጠቀሰ ወገን በጥሬ ገንዘብ ይፈፀማል፡፡ የክፍያው መፈጸም ድርጅቱን በደረሰው ጉዳት ወይም ውድመት ምክንያት ይኖርበት ከነበረው ኃላፊነት ሙሉ በሙሉ ነፃ ያደርገዋል፡፡
5.የማስጠገን ስልጣን
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሁኔታዎች እስከተሟሉ ድረስ መድን ገቢው በአደጋ ምክንያት ጉዳት ለደረሰበት ተሽከርካሪ ጥገና እንዲደረግለት የማዘዝ ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡
ሀ.የጥገናው ወጪ ግምት በሠንጠረዡ ውስጥ ከተጠቀሰው የሥልጣን ገደብ ያልበለጠ ከሆነ፣ ለ.ዝርዝር የጥገና ወጪው ግምት ወዲያውኑ ለድርጅቱ ከቀረበ፣ ሐ.መድን ገቢው ጥገናው አስፈላጊና ሂሳቡም አግባብነት ያለው ስለመሆኑ ድርጅቱ እንዲያውቀው ካደረገ፤
6.በገበያ ላይ ስለማይገኙ የመለዋወጫ ዕቃዎች
ዋስትና ተገብቶለት ጉዳት የደረሰበት የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃ ወይም አካል ጊዜ ያለፈበትና ከአስመጭው ድርጅት የማይገኝ ከሆነ አግባብነት ያለውን የማስጠገኛ ዋጋና አስመጪው ድርጅት ለመለዋወጫ ዕቃዎች ለመጨረሻ ጊዜ ከሰጠው ዋጋ ያልበለጠ የገንዘብ መጠን ይከፍላል፡፡
የክፍል አንድ ማግለያዎች
ድርጅቱ ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ሁኔታዎች ክፍያ የመፈጸም ኃላፊነት የለበትም
1.በሠንጠረዡ ላይ የተጠቀሰውን የአደጋ መነሻ ክፍያ፣
2.በሠንጠረዡ ላይ የተጠቀሰው ተሽከርካሪ በደረሰበት ጥፋት ወይም ጉዳት ምክንያት ለሚከሰት የጥቅም እጦት፣
3.በሠንጠረዡ ላይ የተጠቀሰው ተሽከርካሪ ወይም የተሽከርካሪ አካል በሥራራ ወይም በአገልግሎት ብዛት ለደረሰበት ጉዳት ወይም ዋጋ መቀነስ፣
4.ማንኛውም በውል ሠንጠረዡ ላይ የተጠቀሰ ተሽከርካሪ ለደረሰበት የመካ��ካል፣ ኤልክትሪካል፣ ኤሌክተሮ��ክስ ወይም ኮም��ዩተር ብልሽት፣
5.ፍሬን በመያዝ፣ በመበሳት፣ በመቆረጥ ወይም በፍንዳታ ምክንያት በጐማዎች ላይ ለሚደርስ ጉዳት፣
6.በተሽከርካሪው ላይ በተገጠመ ማንኛውም የመገናኛ መሣሪያ ላይ ለሚደርስ ማንኛውም አይነት ጥፋት ወይም ጉዳት፣
7.በውሉ መሠረት በቀረበ የካሣ ጥያቄም ሆነ ወይም በሌላ ለተሽከርካሪው በተደረገ ጥገና የተነሳ በተሽከርካሪው ላይ ለደረሰ የገበያ ዋጋ መቀነስ፣
8.በአምራራቹ ድርጅት ከተገጠሙትና በግልፅ ተጠቅሰው ዋስትና ከተሰጣቸው በስተቀር ለማንኛውም ራራዲዮ፣ ሬከርደር መጫወቻ ወይም ቴኘ ሪከርደር ላይ ለደረሰ ጥፋት ወይም ጉዳት፣
ክፍል ሁለት
· የሦስተኛ ወገን ኃላፊነት · ለመድን ገቢው የሚሰጥ ማካካሻን በሚመለከት፡-
1.በሠንጠረዡ ላይ የተጠቀሰው የድርጅቱ የኃላፊነት መጠን እንደተጠበቀ ሆኖ መድን ገቢው ኃላፊ ለሚሆንበትና የተጐዳው ሰው ያወጣውን ወጪ ጨምሮ
ሀ.በማንኛውም ሰው ላይ ለደረሰ የአካል ጉዳት ወይም፣ ሞት፣ ለ.በንብረት ላይ ለደረሰ ውድመት፣ ማካካሻ ይከፍላል፡፡
2.ሞተር ብስክሌትን ሳይጨምር መድን ገቢው በዱቤ ሽያጭ ውል መሠረትያልተከራየውንና ማንኛውንም የራራሱ ያልሆነ ተሽከርካሪ በሚያሽከረክርበት ወቅት አደጋ ወይም ጉዳት ቢደርስ የሚከተሉት ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆነው ውሉ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
ሀ.የመድን ዋስትና የተሰጠው ተሽከርካሪ በአገልግሎት ላይ ካልሆነ፣ ለ.የድርጅቱ የኃላፊነት መጠን ከተገለጸው የማካካሻ ክፍያ ገደብ ካልበለጠ፤
3.ድርጅቱ በጽሑፍ ያረጋገጠውን ማንኛውንም ወጪ ይከፍላል፤ 4.ድርጅቱ በራራሱ ምርጫ
ሀ.በዚህ ክፍል ውስጥ ለተጠቀሰ ለማንኛውም የካሣ ክፍያ ለሚያስጠይቅ የሞት አደጋ ማንኛውንም የአሟሟት ምርመራራና ጥያቄ ሊያከናውን የሚችል ወኪል ማዘጋጀት ይችላል፣ ለ.በዚህ ክፍል ውስጥ ለተጠቀሰውና የካሣ ክፍያ ለሚያስጠይቅ ማንኛውም ድርጊት ወይም ወንጀል ነው ለተባለ ድርጊት በማንኛውም የፍርድ ቤት ሂደት ላይ ትብብር ሊያደርግ ይችላል፤
ለሌሎች ስለሚደረግ ማካካሻ፣
የሚከተሉት ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆነው መድን ገቢው ዋስትና የተገባለትን ተሽከርካሪ እንዲጠቀምበት ለፈቀደለት ለማንኛውም ሰው ድርጅቱ ተመሳሳይ የካሣ ክፍያ ይፈጽምለታል፡፡ ሆኖም የተፈቀደለት ግለሰብ፡- ·በሌላ በማንኛውም ውል ካሣ ክፍያ የማይከፈለው ከሆነ፣ ·በዚህ ውል ለተጠቀሱት አንቀጾች፣ ገደቦችና፣ የሚሟሉ ሁኔታዎች፣ በተጨማሪ ለሚካተቱ ነጥቦች ተገዥ መሆን ይጠበቅበታል፡፡
የክፍል ሁለት ማግለያዎች
ድርጅቱ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሁኔታዎች ኃላፊነት አይኖርበትም፡-
1)የመድን ገቢው ሠራራተኛ የሆነ ማንኛውም ሰው በሥራራው ላይ እያለ ለሚደርስበት የአካል ጉዳትና ሞት፣
2)በዚህ ውል አማካኝነት የካሣ ክፍያ የሚጠይቅ ማንኛውም ሰው የራራሱ ለሆነ፣ በአደራራ ለያዘው፣ ወይም በራራሱ ቁጥጥር ሥር ለሚገኝ በማንኛውም ንብረት ላይ ማንኛውንም ተሽከርካሪ ይጨምራራል ለሚደርስ ጥፋት ወይም ጉዳት፣
ክፍል ሦስት
የግል ንብረትና አልባሳት
የመድን ዋስትና የተሰጠው ተሽከርካሪ በደረሰበት አደጋ ምክንያት በተሽከርካሪው ውስጥ ወይም ላይ የነበሩ የግል ንብረቶች፣ አልባሳት ወይም የእግር መርገጫ ምንጣፎች ጉዳት ከደረሰባቸው ወይም ከጠፉ ድርጅቱ በሠንጠረዡ ላይ በዝርዝር ከተገለጸው መጠን ያልበለጠ የካሣ ክፍያ ይፈጽማል፡፡
የክፍል ሦስት ማግለያዎች
ድርጅቱ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሁኔታዎች ኃላፊነት አይኖርበትም፡-
1.ጥፋቱ ወይም ጉዳቱ ሀ.የገንዘብ፣ ቴምብር፣ ቲኬት፣ መረጃ ወይም ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው ጌጣጌጦች እና
ለ.ለማንኛውም ንግድ ወይም ቢዝነስ የተጫኑ ዕቃዎች ወይም ናሙናዎች ከሆነ፣
2.ከአገልግሎት ብዛት ለደረሰ ጉዳት ወይም ዋጋ መቀነስ፣
3.ዋስትና በተሰጠው ተሽከርካሪ ላይ በተጫነ ማንኛውም ንብረት ላይ ለተፈጸመ ሌብነት፣
ክፍል አራት
በግል ስለሚያጋጥም አደጋ
1.መድን ገቢው፣ አሽከርካሪው ወይም ማንኛውም የመድን ዋስትና በተሰጠው ተሽከርካሪ ውስጥ የነበረ ሌላ ተሳፋሪ በኃይል፣ በአደጋ፣ በውጭና በሚታይ ምክንያት የአካል ጉዳት ከደረሰበት በሠንጠረዡ ላይ ለአንድ አደጋ ከተገለጸው የኃላፊነት ክፍያ መጠን ያልበለጠ ድርጅቱ በግል ለደረሰው አደጋ ካሣ ይፈፅማል፡፡
2.የደረሰው ጉዳት ከማንኛውም ሌላ መንስኤ ነፃ ሆኖ የመድን ዋስትና ከተሰጠው ተሽከርካሪ ጋር በቀጥታ የተገናኘና የሞት፣ የአንድ አይን ወይም የሁለቱም አይኖች ሙሉ በሙሉ መጥፋት ወይም የማንኛውም የሰውነት አካል ጉድለት ቀጥተኛና ቅፅበታዊ ምክንያት መሆን አለበት፡፡
የክፍል አራት ማግለያዎች
1.በዋስትናው የተገለጹት ጥቅሞች በሚከተሉት ሁኔታዎች ለደረሰ ጉዳት አይከፈሉም፡፡
ሀ.የአካል ጉዳቱ ራራስን የማጥፋት ወይም ራራስን ለማጥፋት የተደረገ ሙከራራ ውጤት ከሆነ፣
ለ.የደረሰው የሞት፣ ቋሚ የአንድ አይን ወይም ሁለቱም አይኖች መጥፋት ወይም ለማንኛውም የሰውነት አካል ጉዳት ምክንያት የሆነው ድርጊት ከተከሰተ ከስድስት ወራራት በላይ ከሆነ፣
2.መድን ገቢው፣ አሽከርካሪው ወይም ማንኛውም ተሳፋሪ ሌላ በግል ለሚደርስ አደጋ የግል አደጋ የመድን ዋስትና ሽፋን ከድርጅቱ የተሰጣቸው ከሆነ የግል አደጋ ጥቅም ጥያቄ በአንደኛው ውል ሥር ብቻ የሚስተናገድ ይሆናል፡፡
3.የመድን ገቢው፣ ሹፌር ወይም መድን ዋስትና በተሰጠው ተሽከርካሪ ውስጥ ያለ ማንኛውም ተሳፋሪ እድሜው ከ14 አመት በታች ወይም ከ65 አመት በላይ ከሆነ፣
ክፍል አምስት
የሕክምና ወጪዎች
የድርጅቱ ኃላፊነት በሠንጠረዡ ውስጥ ከተጠቀሰው የኃላፊነት መጠን በላይ እስካልሆነ ድረስ በመድን ገቢው፣ በአሽከርካሪው ወይም በውሉ ሠንጠረዥ ላይ በተጠቀሰው ማንኛውም ተሽከርካሪ ውስጥ ባለ ማንኛውም ተሳፋሪ ላይ በኃይል አደጋ፣ በውጫዊና በሚታይ ቀጥተኛና ቅጽበታዊ በሆነ ምክንያት በአካል ላይ ለሚደርስ ማንኛውም ጉዳት ድርጅቱ ለመድን ገቢው ተገቢውን የሕክምና ወጪዎች ይከፍላል፡፡
ጠቅላላ ሁኔታዎች
1.የካሣ ጥያቄ ባለመቅረቡ የሚገኝ ቅናሽ
በዋስትና ዘመኑ ውስጥ የውል እድሳት ከመደረጉ በፊት በዚህ ውል መሠረት ምንም አይነት የካሣ ጥያቄ ካልቀረበ፣ ደንበኛው የካሣ ጥያቄ ባለማቅረባቸው በውል ዕድሳት ወቅት በድርጅቱ የቅናሽ ስኬል መሠረት ተገቢው የአረቦን ቅናሽ ይደረግላቸዋል፡፡
2.ሽፋን ስለማቋረጥ
በውል ከተሰጠው ሽፋን ውጪ በሆነ ጉዳት ወይም ጥፋት ምክንያት የመድን ዋስትና የተሰጠው ተሽከርካሪ ሥራራ ስለማቋረጡ ለድርጅቱ በጽሑፍ ማስታወሻ ከተሰጠው፣ ማስታወሻው ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ሽፋኑ እንዲቆም የሚደረግ ሲሆን ሽፋኑ ቢያንስ ለ4 አራራት ተከታታይ ሣምንታት ከተቋረጠ ድርጅቱ በዚያው ልክ የውሉን ሽፋን ያራራዝማል፡፡
3.የባለቤትነት ለውጥ ዋስትና በተሰጠው ተሽከርካሪ ላይ የባለቤትነት ለውጥ ከተደረገ የሚሰጠው ሽፋን እንደሚከተለው ይሆናል፡
ሀ.ይህን የሚከለክል ማንኛውም አንቀፅ ቢኖርም እንኳን ዋስትናው ተሽከርካሪውን እንዲጠቀምበት ለተሰጠው ወገንም ያገለግላል፤ ለ.ጥቅሙ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በሦስት ወራራት ጊዜ ውስጥ ተጠቃሚውና ድርጅቱ ውሉን ሊያቋርጡ ይችላሉ፤
4.ለአደጋ የመጋለጥ ሁኔታን ስለመለወጥ መድን ገቢው ማንኛውንም ለአደጋ የመጋለጥ ሁኔታን ለውጥ ለድርጅቱ ያሳውቃል፡፡ ሆኖም መድን ገቢው ለአደጋ የመጋለጥ ሁኔታውን ለውጥ ካላሳወቀና ድርጅቱ በውሉ ላይ በተጨማሪ ሽፋን ተሰጥቶት እንዲካተት ካላደረገ በስተቀር በለውጡ ምክንያት ለደረሰ ጥፋት፣ ጉዳት ወይም ኃላፊነት የሚቀርብ ጥያቄ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
5.የመንጃ ፈቃድ ድርጅቱ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሰዎች ወጣትና ልምድ የሌላቸው አሽከርካሪዎች ብሎ ስለሚቆጥራራቸው ተጨማሪ መዋጮ (excess) እንዲከፍሉ ያደርጋል/ ያስገድዳል፤ G)እድሜያቸው ከ21 ዓመት በታች የሆኑ፣ K)የመንጃ ፈቃድ ካገኙ ከ12 ወራራት በታች ለሆኑ አሽከርካሪዎች፣
6.ዕድሳትና ጥገና ከሦስተኛ ወገን ከሚቀርብ የኃላፊነት ጥያቄ በስተቀር ዋስትና የተሰጠው ተሽከርካሪ በተሽከርካሪ ንግድ ድርጅት ውስጥ ለዕድሳት ወይም ለጥገና በሚቆምበት ወቅትም ሽፋኑ ይቀጥላል፡፡
ሽፋን የሚሰጥበት ሁኔታ
1.የተሰጠው የመድን ሽፋን ..አጠቃላይ.. ከሆነ የዚህ ውል ክፍሎች/አንቀጾች በሙሉ ተግባራራዊ ይሆናሉ፡፡
2.የተሰጠው የመድን ሽፋን ..ለሦስተኛ ወገን፣ ለእሳትና ለስርቆት.. ከሆነ ክፍል 3፣4 እና 5 እንደተሰረዙ ይቆጠራራል፤ ክፍል "አንድ" የሚያገለግለው በቀጥታ በእሳት፣ በራራስ መቀጣጠል፣ በመብረቅ በውጭ ፍንዳታ በስርቆት ወይም በስርቆት ሙከራራ ለሚደርስ ጥፋት ወይም ጉዳት ብቻ ይሆናል፡፡
3.የተሰጠው የመድን ሽፋን ..ለሦስተኛ ወገን ብቻ.. ከሆነ የዚህ ውል ክፍል 1፣3፣4 እና 5 እንደተሰረዙ ይቆጠራራል፡፡
* አጠቃላይ ማግለያዎች በውሉ የማይሸፈኑ
ድርጅቱ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሁኔታዎች ማንኛውንም ክፍያ የመፈፀም ኃላፊነት አይኖርበትም፡፡
1.
ሀ.ከኢትዮጵያ የድንበር ክልል ውጭ፣
ለ.ማንኛውም በውል ሠንጠረዡ ውስጥ የተጠቀሰ ተሽከርካሪ በእሽቅድምድም፣ በእሽቅድምድም ሥፍራራ አሽቀዳዳሚነት በፍጥነት ፍተሻ፣ በአስተማማኝነት ሙከራራ ወይም ዋስትና የተሰጠው ተሽከርካሪ በሠንጠረዡ ውስጥ ከተገለፀው አገልግሎት ውጪ ሌላ አገልግሎት የሚሰጥ ከሆነ፣
ሐ.የመድን ዋስትና የተሰጠውን ተሽከርካሪ የሚያሰክር መጠጥ ወይም አደንዛዥ ዕጽ ከወሰዱ በፃላ በማሽከርከር፣ ለደረሰ ማንኛውም አደጋ፣ ጥፋት፣ ጉዳት ወይም ኃላፊነት፣
2.ከማንኛውም ኮንትራራት ወይም ስምምነት ለመነጨ ኃላፊነት፣
3.አሽከርካሪው ተሽከርካሪውን ለመንዳት የሚያስችል መንጃ ፈቃድ ከሌለው ወይም መሰል ፈቃድ እንዳያገኝ ወይም እንዳይዝ የተከለከለ ከሆነ፣
4.በጎርፍ፣ በማዕበል፣ በእሳተ ገሞራራ ፍንዳታ፣ በመሬት መንቀጥቀጥ ወይም በሌላ የተፈጥሮ መናወጥ ምክንያት በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ለማንኛውም ጥፋት ወይም ኃላፊነት መንስኤ ለሆነ ወይም አስተዋጽኦ ላደረገ፣
5.በጦርነት፣ በወረራራ፣ በውጭ ጠላት እንቅስቃሴ፣ ጦርነት ቢታወጅም ባይታወጅም በእርስ በርስ ጦርነት፣ በረብሻ፣ በሥራራ ማቆም አድማ፣ በብጥብጥ፣ በወታደራራዊ ረብሻ ወይም በሕዝብ መነሳሳት፣ በአብዮት፣ በወታደራራዊ ወይም በሥልጣን ንጥቂያ፣ ወይም ማርሻል ሕግ እንዲታወጅ ወይም እንዲራራዘም ምክንያት ለሆነ ድርጊት፣
6.በዚህ ውል ውስጥ ሽፋን ያልተሰጠ ውን ማንኛውንም ተጐታች ወይም ብልሽት ያጋጠመውን ተሽከርካሪ ሲጐትት የመድን ውል ዋስትና በተሰጠው ተሽከርካሪ ላይ ጥፋት ወይም ጉዳት ቢደርስ፣
7.መድን ገቢው እያወቀው ፍቃድ ሰጭው ባለሥልጣን በባለቤትነት ደብተሩ ላይ ከገለፀው የጭነት ልክ በላይ በመጫን ወይም በማስጨነቅ ወይም ከመቀመጫው ልክ በላይ የተሳፋሪዎች ቁጥር በመብዛቱ በውል ሠንጠረዡ ላይ የተገለፀው ተሽከርካሪ ለሚደርስበት ማንኛውም ጥፋት፣ ጉዳት ወይም ኃላፊነት፣
8.በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ መንስኤ ለሆነ ወይም አስተዋጽኦ ላደረገ በማንኛውም ንብረት ላይ ለደረሰ ጥፋት፣ ውድመት፣ ጉዳት ወይም በምንም አይነት ለደረሰ ማንኛውም ጥፋት ወይም ወጭ ወይም ማንኛውም የጥቅም እጦት ወይም ማንኛውም ሕጋዊ ኃላፊነት፣
ሀ.አዮናይዜሽን ጨረር ወይም ከማንኛውም ¾��ውክሊየር ነዳጅ ብክለት ወይም ራራዲዮ አክቲቭ ብክለት ወይም u��ውክሊየር ነዳጅ መቀጣጠል ወይም ከማንኛውም ��ውክሊየር ዝቃጭ፣
ለ.ከማንኛውም ¾��ውክሊየር ፈንጂ ወይም ��ውክሊየር አካል የመነጨ ራራዲዮ አክቲቪቲ፣ መርዛማ ፈንጅ ወይም ሌላ አደገኛ ፀባይ፣
ጠቅላላ የሚሟሉ ሁኔታዎች
1.የመድን ገቢው ተግባር
መድን ገቢው ወይም የካሣ ጥያቄ የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው በዚህ ውል ውስጥ በተቀመጡ ማግለያ አንቀጾችና በሚሟሉ ሁኔታዎች ውስጥ የሚተገበሩና የተከለከሉ ሁኔታዎችን ማክበርና ማሟላት እንዲሁም በውል መጠየቂያው ወይም በአደጋ ማሳወቂያ ቅጽ ላይ የተሰጡት ቃሎችና መልሶች እውነት መሆን ድርጅቱ ማንኛውንም ኃላፊነት ወስዶ በውሉ መሠረት ክፍያ ከመፈፀሙ በፊት ሊሟሉ የሚገባቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡
2.ስለ ተሽከርካሪ ደህንነት/ጥበቃ/
መድን ገቢው፣ የእሱ ሠራራተኛ ወይም ማንኛውም የተፈቀደለት ሹፌር ወይም ዋስትና ለተሰጠው ተሽከርካሪ ኃላፊ የሆነ ማንኛውም ሰው፣ ተሽከርካሪውን ከጥፋት ወይም ከጉዳት መጠበቅና እንዲሁም ዋስትና የተሰጠው ተሽከርካሪ ተግባሩን ለማከናወን ብቁ እንዲሆን ተገቢውን እርምጃ ሁሉ ይወስዳሉ፡፡ ድርጅቱ በማንኛውም ጊዜ ተሽከርካሪውን ወይንም ማንኛውንም አካል ወይም የመድን ገቢውን ማንኛውንም ሹፌር ወይም ሠራራተኛ በማንኛውም ጊዜ ለመመርመር ነፃና ሙሉ መብት አለው፡፡ በአደጋ ወይም በብልሽት ወቅት ዋስትና የተሰጠው ተሽከርካሪ ተጨማሪ ጥፋት ወይም ጉዳት እንዳይደርስበት ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል፡፡ ተሽከርካሪው ተገቢው ጥገና ሳይደረግለት ከተነዳ የሚደርስበት ማንኛውም ተጨማሪ ጉዳት ወይም ሌላ አደጋ በውሉ ከተሰጠው ሽፋን ውጪ ስለሆነ በዚህ ሁኔታ ለሚደርስ ጉዳት ወይም ጥፋት ድርጅቱ ሽፋን አይሰጥም፡፡
3.ማጭበርበር
አንድ የካሣ ጥያቄ በማንኛውም መንገድ የተጭበረበረ ከሆነ፤ እንዲሁም ዋስትና የተሰጠው ተሽከርካሪ ዋጋ የተጋነነ ከሆነ ወይም በውሉ መሠረት ጥቅም ለማግኘት መድን ገቢው ወይም በእሱ ምትክ ማንኛውም ሰው በተጭበረበረ መንገድ ከተጠቀመ ወይም ዋስትና በተሰጠው ተሽከርካሪ ላይ በግትርነት ወይም በመድን ገቢው ቸልተኝነት ጥፋት ወይም ጉዳት ከደረሰ ውሉ የሚያስገኛቸው ጥቅሞች በሙሉ ይሠረዛሉ፡፡
4.አደጋን ስለማሳወቅ
በማንኛውም አደጋ ጥፋት ወይም ጉዳት እንደተከሰተ ወዲያውኑ ለድርጅቱ የጽሑፍ ማስታወቂያ መስጠት ያስፈልጋል፡፡ በማንኛውም የካሣ ጥያቄ ወቅት ማንኛውንም ደብዳቤ፣ የካሣ ጥያቄ፣ ትዕዛዝ፣ መጥሪያ ወይም ሂደት መድን ገቢው እንደደረሰው ወዲያውኑ ለድርጅቱ ያስተላልፋል፡፡ በዚህ ውል አማካኝነት ካሣ የሚያስጠይቅ የክስ ጉዳይ በሂደት ላይ መሆኑን መድን ገቢው እንዳወቀ ለድርጅቱ በጽሑፍ ወዲያውኑ ያሳውቃል፡፡ በዚህ ውል መሠረት ካሣ ሊያስጠይቅ የሚችል ስርቆት ወይም ሌላ የወንጀል ሥራራ ከተከናወነ መድን ገቢው ለፖሊስ ወዲያውኑ ያሳውቃል፡፡ አጥፊውም እንዲቀጣ ለድርጅቱ ትብብር ያደርጋል፡፡
5.ስለ ካሣ ሂደት/መዳረግ መብት
መድን ገቢው ወይም የካሣ ጥያቄ የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው ከድርጅቱ የፅሑፍ ማረጋገጫ ከማግኘቱ በፊት ክፍያዎችን ማመን፣ ማዘጋጀት፣ ቃል መግባት ወይም መፈፀም አይችልም፡፡ ድርጅቱ ከፈለገ በራራሱ ስም ማንኛውንም የካሣ ጥያቄ መከታተል፣ በፍትሐብሄር ጉዳዮች ወይም በድርድሮች መከራራከር እና ክፍያ መፈፀም ወይም በራራሱ ስም በማንኛውም የካሣ ጥያቄ ወይም ጉዳት ወይም በሌላ ሦስተኛ ወገን ላይ ለራራሱ ጥቅም ሲል ክስ መመስረት ይችላል፡፡ በተጨማሪም ማንኛውንም የክስ ሂደት መከታተልና ማንኛውንም የካሣ ክፍያ የመፈፀም ሙሉ ሥልጣን ያለው ሲሆን እንደ ድርጅቱ ጥያቄ ማንኛውንም መረጃና እገዛ መድን ገቢው ይሰጣል፡፡
6.ሌላ የመድን ዋስትና
በዚህ ውል መሠረት ማንኛውም የካሣ ጥያቄ ሲቀርብ ሌላ ዋስትና ሰጪ ድርጅት ይህንኑ ጥፋት፣ ጉዳት ወይም ኃላፊነት ሸፍኖ ከተገኘ ድርጅቱ ለማንኛውም ጥፋት/ጉዳት ማካካሻዎችና የካሣ ወጪዎች በስሌት የሚደርስበትን ከመሸፈን በስተቀር ሌላ የመክፈል ወይም የማዋጣት ኃላፊነት አይኖርበትም፡፡
7.ውል ስለመሰረዝ
በመጨረሻ በሚታወቀው አድራራሻው መሠረት ለመድን ገቢው በተመዘገበ ደብዳቤ አማካኝነት ድርጅቱ ውሉን እንደሚሰርዝ የአሥራራ አምስት ቀናት ማስጠንቀቂያ መስጠት ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ውሉ ለሰራራበት ወቅት መቶኛውን በማስቀረት ልዩነቱን ድርጅቱ ለመድን ገቢው ይከፍላል፡፡ የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ በመስጠት መድን ገቢውም ውሉን በማንኛውም ጊዜ መሠረዝ ይችላል፡፡ በዚህ መሠረት በውል ዘመኑ ውስጥ የካሣ ክፍያ እስካልቀረበ ድረስ ውሉ ለሠራራበት ወቅት በድርጅቱ የአጭር ጊዜ ሂሳብ ማስያ መሠረት አረቦኑን ቀንሶ ልዩነቱን ለመድን ገቢው ይከፈላል፡፡
8.ስለ ግልግል
ኃላፊነት መኖሩ ከታመነ በኋላ በፖሊሲው መሠረት ሊከፈል በሚገባው የካሣ መጠን ላይ ልዩነት ከተፈጠረ፣ አለመግባባቱ በሁለቱም ወገኖች በፅሑፍ በሚሾም አንድ አስታራራቂ ውሣኔ እንዲሰጥበት ይደረጋል፡፡ በዚህ ላይ ልዩነት ከተፈጠረ ወይም በአንድ ላይ ስምምነት መድረስ ካልተቻለ አንደኛው ወገን ለሌላኛው ወገን ባሳወቀው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ የየራራሱን አንድ አንድ አስታራራቂ መርጦ በፅሑፍ ያሳውቃል፡፡ ሁለቱም ወገኖች ሰብሳቢ የሚሆነውን ሰው ለመምረጥ ስምምነት ላይ መድረስ ካልቻሉ ከሁለቱ ወገን የተሾሙት አስታራራቂዎች አንድ ላይ ሆነው ሰብሳቢ የሚሆነውን ሰው በፅሑፍ ይመርጣሉ፡፡ ሰብሳቢውም ከአስታራራቂዎቹ ጋር በመቀመጥ ሽምግልናውን ይመራራል፡፡ በኮርፖሬሽኑ ላይ ማንኛውንም ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ በቅድሚያ በሸምጋዮቹ የተሰጠ ውሣኔ ሊኖር ይገባል፡፡
9.ስለመዋጮ
በዚህ ውል ውስጥ የተገለፀውና የመድን ዋስትና የተሰጠው ተሽከርካሪ ማንኛውም አካሉ ከጠፋ ወይም ከተጎዳ፣ በእንግልት፣ በፍትጊያ ወይም በዋጋ መቀነስ ምክንያት አዲስ ተጓዳኝ ወይም መለዋወጫ ዕቃ የሚተካ ከሆነ መድን ገቢው ተገቢውን መዋጮ የመክፈል ኃላፊነት አለበት፡፡
10.መተካት ሙሉ ውድመት
ውድመት ደርሶ ጥገና የሚካሄድ ከሆነ ወይም ተሽከርካሪው በጥገና በማይስተካከልበት ሁኔታ በመውደሙ ምክንያት የሙሉ ውድመት ክፍያ የሚከፈል ሆኖ ሲገኝ መድን ገቢው ምትክ የተደረገላቸውን አሮጌ የመለዋወጫ ዕቃዎች ወይም ሙሉ ውድመት የደረሰበትን ተሽከርካሪ ከሕጋዊ ሰነዶች፣ ከባለቤትነት መብቶችና ከሌሎች ሰነዶች ጋር በማድረግ ለድርጅቱ ያስረክባል፡፡ ድርጅቱ እነዚህን የመለዋወጫ ዕቃዎች ወይም ሙሉ ውድመት የደረሰባቸውን ተሽከርካሪዎች የራራሱ የማድረግ፣ የመሸጥ እና የመለወጥ ሙሉ መብት አለው፡፡
11.አደጋ ከደረሰበት ቦታ ተሽከርካሪን ስለማንሣት
ድርጅቱ አደጋ ስለመድረሱ የፅሑፍ መረጃ እንደደረሰው ውድመት የደረሰበትን ተሽከርካሪ ከተጨማሪ ጉዳቶች ለመከላከል ከአደጋው ቦታ ያነሳል፡፡ ድርጅቱ ይህንን በማድረጉ ኃላፊነትን እንደተቀበለ ተደርጎ መታሰብ የለበትም፡፡ በኢንሹራራንስ ፖሊሲው መሠረት ተጨማሪ ምርመራራዎች ከተካሄዱ በኋላ የካሣ ክፍያ ጥያቄው ውድቅ ሊደረግ ይችላል፡፡ የካሣ ጥያቄው ውድቅ ከተደረገ ድርጅቱ ለጥበቃ እና ተሽከርካሪውን ለማንሣት ያወጣቸውን ወጪዎች መድን ገቢው ይተካለታል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ይህ ጽሑፍ ስለ የግል ተሽከርካሪ የመድን ዋስትና የቀረበ ማብራራሪያ እንጂ በሕግ ፊት የሚፀና ውል አይደለም፡፡ |