About Us Financial Service Publication Branches News Forms Contact Us Articles FAQ
 

Side Menu



Proposal Forms
----------------------------
Motor Insurance
Fire Insurance
Personal Accident Insurance 
Workmens Compesation 
Burglarly and House Breaking
Contractors All Risk
Contractors Plant & Machinery
Deterioration of Stock
Electronic Equipment Insurance
Erection All Risk
Inland Carriers Liability
Machinary Loss of Profit
Machinary Insurance
Public Liability
Professional Indemenity
Product Liability 
Fidelity Guaranty
Money Insurance

Claim Notification Forms 
-----------------------------
Motor Insurance
Marine Insurance
Accedent and Disease

 
የትርፍ እጦት ዋስትና

1.መግቢያ

መደበኛው የእሳት ቃጠሎ ዋስትና ውል በእሳት፣ በመብረቅና ለግል መገልገያ በሚውል ቦይለርና በጋዝ ፍንዳታ ምክንያት የደረሰን የንብረት ጥፋት ወይም ጉዳት ይሸፍናል፡፡ ይህ ዋስትና በአግባቡ በተገቢው መንገድ ከተዘጋጀ ጉዳቱ ወይም ጥፋቱ ከደረሰ በኋላ የወደመውን ንብረት ለማስጠገን ወይም ለመተካት የሚያስፈልገውንም ወጪ ይሸፍናል፡፡ የወደመውን ንብረት ለማስጠገን ወይም ለመተካት የተወሰነ የጊዜ ይወስዳል፡፡

በዚህ ለጥገና በሚወሰድ ጊዜ ውስጥ ደግሞ የንግዱ አንቅስቃሴ በሚከተሉት ምክንያቶች የአደጋ ሥጋት ሊኖርበት ይችላል፡፡ እነዚህም

ሀ.የደንበኞችን የሥራ ትዕዛዝ አለማጠናቀቅ፣
ለ.ትርፍ አለማግኘት፣
ሐ.የኪራይ፣ የባንክ ወለድ፣ የኢንሹራንስ አረቦን፣ ወዘተ የመሳሰሉ ቀጣይነት ያላቸው ወጪዎች፣
መ.አስፈላጊና ወሳኝ ለሆኑ ሠራተኞች የሚከፈል ደሞዝና የጉልበት ዋጋ ናቸው፡፡

እነዚህ ንብረት በመውደሙ ምክንያት የደረሱ የአደጋ ሥጋቶች በእሳት ቃጠሎ ዋስትና አይሸፈኑም፡፡

እነዚህን የአደጋ ሥጋቶች የሚሸፍነው ትክክለኛው ውል የትርፍ እጦት የመድን ዋስትና ውል ነው፡፡ ስለዚህ የትርፍ እጦት የመድን ዋስትና ውል የንግዱ እንቅስቃሴ ባይቋረጥ ኖሮ ሊገኝ የሚችለውን ገቢ/ትርፍ የሚተካ ውል ነው፡፡ ይሁን እንጂ ማንኛውም በትርፍ እጦት የመድን ዋስትና ውል አማካይነት የሚቀርብ የካሣ ጥያቄ ተግባራዊ የሚሆነው ዋስትና በተገባለት ንብረት ላይ ጥፋት ወይም ሕጋዊ ኃላፊነት ከመድረሱ በፊት ንብረቱ በሌላ ዋስትና ሽፋን ያለው ከሆነ ብቻ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡

2.ዋስትና የሚገባለት ንብረት

የትርፍ እጦት የመድን ዋስትና፣ የእሳት ቃጠሎ ዋስትና ለተገባለት ቋሚ ንብረት ህንፃ፣ በህንፃው ውስጥ የሚገኙ ቁሳቁሶች፣ ወዘተ በተጨማሪነት የሚገዛ የውል አይነት ነው፡፡ ለትርፍ እጦት ዋስትና ሽፋን የሚሰጠው በቅድሚያ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ አደጋ ሽፋን የሚሰጥ ዋስትና ካለ እና ዋስትናው በማንኛውም ምክንያት ያልተቋረጠ ከሆነ፣ እንዲሁም በዋስትናው መሠረት ንብረቱ ላይ ለደረሰው የንብረት ጉዳት ካሣ ከተከፈለ ወይም ለመክፈል ኃላፊነት ከተወሰደ ብቻ ነው፡፡

በንብረት ላይ በደረሰ ጉዳት/ውድመት መንስዔነት በሚፈጠር የሥራ መቋረጥ ምክንያት ለሚከሰት የትርፍ እጦት ለመድን ገቢው የሚፈፀመው የክፍያ መጠን፣

1.የሥራ እንቅስቃሴው በተቋረጠ ጊዜ ይገኝ የነበረውን አጠቃላይ ትርፍ እና

2.የሥራ እንቅስቃሴው በተቋረጠበት ጊዜ በዋስትና ሰጪው ስምምነት ዋስትና ገቢው የሚያጣውን ትርፍ ለመቀነስ እንዲረዳው በጊዜያዊነት ለሚከራየው ድርጅትና ማሽን ወይም ቀደም ሲል የገባውን የኮንትራት ውል ለመፈፀም ለሚገዛቸው ዕቃዎች በሚያወጣው ወጪ ምክንያት የሚከሰት ተጨማሪ የሥራ ማስኬጃ ወጪ ይሆናል፡፡

3.የሽፋን መጠን

ድርጅቱ በውሉ ውስጥ የተጠቀሱት የሚሟሉ ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆነው ማንኛውም ህንፃ ወይም ሌላ ንብረት ወይም መድን ገቢው ንግዱን ለማካሄድ በቅጥር ግቢው የሚጠቀምበት ንብረት በከፊል በሚከተሉት ሁኔታዎች ብልሽት ወይም ውድመት ቢደርስበት ሽፋን ለመስጠት ተስማምቷል፡፡
3.1በእሳት
3.2በመብረቅ
3.3በፍንዳታ፤ጋዝ በማይመረትበት፣ በጋዝ የሚሰራ ሥራ በሌለበትና ጋዝ ለግል ጠቀሜታ ብቻ በሚውልበት ሕንፃ ውስጥ ከዚህ በኋላ ውድመት እያልን የምንጠራው ብልሽት ወይም ጉዳት የመጀመሪያው አረቦን ከተከፈለ በኋላ“ በውሉ ሰንጠረዥ ላይ ከተጠቀሰው የውል ዘመን ማብቂያ ጊዜ ቀን በፊት ወይም ውሉን ለማደስ አረቦን በተከፈለበትና በድርጅቱ ተቀባይነት አግኝቶ ውል ገቢው የንግድ ሥራውን በማከናወን ላይ ባለበት ወቅት በደረሰ ጉዳት ለተቋረጠ እንቅስቃሴ፣

3.4የተለዩ የአደጋ መንስዔዎች (Special Perils)& በእሳትና መብረቅ የመድን ዋስትና ለተለዩ የአደጋ መንስዔዎች የሚሰጠው ሽፋን ለትርፍ እጦት የመድን ዋስትናም ሊሰጥ ይችላል፡፡

4ማግለያዎች

ይህ ውል በሚከተሉት ሁኔታዎች የደረሰን ጉዳት፣ ጥፋት ወይም ውድመት አይሸፍንም፡፡


ሀ.በመንግሥት ባለሥልጣን ትዕዛዝ እንዲቃጠል ለተደረገ ንብረት፣
ለ.በምድር ውስጥ ለውስጥ በሚቀጣጠል እሳት ለደረሰ ውድመት፣
ሐበሽፋን መጠኑ ላይ ከተጠቀሰው ፍንዳታ ውጭ በሚደርስ ፍንዳታ፣
መ.በድንገት የተከሰተ ቢሆንም ባይሆንም ጫካን፣ ቁጥቋጦን፣ በሳር የተሸፈነ ሜዳን በማቃጠል ወይም ደንን በመመንጠር በተፈጠረ ቃጠሎ፣
ሠ. በመታመቅ፣ በተፈጥሮ ሙቀት ወይም በድንገት በሚከሰት ብክለት ወይም በማሞቅና በማድረቅ ሂደት የደረሰን ውድመት፣
ረ.ለጉዳቱ መንስዔ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የ��ውክሊየር ጦር መሣሪያ አስተዋጽኦ ካደረገ ወይም ጉዳቱ የደረሰው በ��ውክሊየር ጦር መሣሪያ ምክንያት ከሆነ፣
ሰ.በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ከማንኛውም የ��ውክሊየር ነዳጅ መንስዔ ለሆነ ራዲየሽን ወይም በ��ውክሊየር መንደድ የተነሣ ለሚከሰት የ��ውክሊየር ብክለት፤ ይሁንና ለዚህ የማግለያ ሁኔታ ብቻ የመንደድ/መቃጠል ሂደት ��ውክሊየር በራሱ የሚፈጥረውን መከፋፈል ሊያካተት ይችላል፡፡
ሸ.በሌላ የተፈጥሮ ኃይል የሚመጣ ጉዳት፣
ቀ.በመሬት መንቀጥቀጥ፣ በእሳተ ገሞራና
በ.በማዕበል፣ በአውሎነፋስ ወይም በሌላ የአየር ብክለት ምክንያት
ተ.በጦርትነት፣ በወረራ፣ በውጭ ጠላት ጥቃት፣ በግጭት ጦርነት ቢታወጅም ባይታጅም ወይም በጦርነት መሰል ድርጊቶች፣ በእርስ በርስ ጦርነት፣
ቸ.በወታደራዊ አመፅ፣ በሕግ አልበኝነት፣ በሥራ ማቆም አድማ፣ በሕዝባዊ ብጥብጥ፣ በወታደራዊ ወይም ሕዝባዊ መነሳሳት፣ በውንብድና፣ በአብዮት፣ በሥልጣን ንጥቂያ፣

5.የሚሟሉ ሁኔታዎች

ይህ የመድን ዋስትና ስለሚመለከተው ንግድ ወይም ንግዱ ስለሚካሄድበት ቅጥር ግቢ ከእውነታው የራቀ የተሳሳተ መረጃ ከተገኘ ወይም የአደጋውን ሥጋት ለመገመት የሚያስችል መታወቅ ያለበት እውነታ በትክክል ካልቀረበ ወይም ሳይቀርብ ቢቀር ድርጅቱ በዚህ ውል ኃላፊነት አይኖርበትም፡፡
የድርጅቱ ገንዘብ ተቀባይ ወይም ድርጅቱ የመረጠው ወኪል የታተመ ደረሰኝ ፈርሞ ለመድን ገቢው ካልሰጠ በስተቀር ምንም ዓይነት የአረቦን ክፍያ አይፈፀምም፡፡
ዋስትና ገቢው ማንኛውንም አስቀድሞ የገባውን የመድን ዋስትና ወይም ዋስትናዎች ወይም በዚህ ውል መሠረት ዋስትና የተሰጠውን ጉዳት በሚመለከት ዋስትና ከገባ ለድርጅቱ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ ዋስትና ገቢው ይህንን ሁኔታ ካላሳወቀና የዋስትናው ወይም የዋስትናዎቹ ዝርዝር ማንኛውም ውድመት ከመከሰቱ በፊት ቀርቦ በድርጅቱ ወይም ድርጅቱ በሚወክለው አካል በዚህ ውል ውስጥ እንዲካተት ካልተደረገ፤ በዚህ ውል አማካይነት የሚገኘው ጠቀሜታ ሁሉ ውድቅ ይደረጋል፡፡


5.4.ሀ.በዚህ ውል መሠረት የካሣ ጥያቄ የሚያስነሳ የሕንፃ መደርመስ ወይም መፈራረስ ሲከሰት፣
ለ.የሕንፃው ከፊል አካል ቢደረመስ ወይም ቢፈራርስ፣
ሐ. ጠቅላላ ሕንፃው ወይም ማንኛውም የሕንፃው አካል በከፊል ቢደረመስ ወይም ቢፈራርስ፣

በዚህ ውል መሠረት የተገባው የመድን ዋስትና ወዲያውኑ ይቋረጣል፡፡
ይህም የሚሆነው፡-
1.የህንፃው መደርመስ ወይም መፈራረስ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፍተኛ ሁኔታ ወይም የህንፃው ዋና አካል ወይም የህንፃውን ተፈላጊነት የሚያሳጣ አካል ወይም በህንፃው ውስጥ ያለ ንብረት የአደጋ ሥጋቱን መጠን ከፍ የሚያደርገው ከሆነ ወይም አደጋው ከደረሰ፤
2.የሕንፃው መደርመስ ወይም መፈራረስ በዚህ የመድን ዋስትና ውል ሽፋን በተሰጠው የአደጋ ሥጋት ካልሆነ ወይም በውሉ ውስጥ ከተጠቀሱት ንብረቶች ጋር ሽፋን እንዲሰጣቸው ተጠይቆ ቢሆን ኖሮ ሽፋን ሊሰጣቸወ በሚችሉ ንብረቶች ላይ ለደረሰ ጉዳት ወይም ውድመት ከሆነ ነው፡፡

በዚህ ውል መሠረት ሕንፃው ከመደርመሱ በፊት፣ በሚደረመስበት ወቅት ወይም ከተደረመሰ በኋላ በደረሰው ጉዳት ምክንያት ማንኛውም የካሣ ጥያቄ የሚነሣ ከሆነ መድን ገቢው ጉዳቱ አስቀድሞ የተከሰተ ወይም ውሉ በሥራ ላይ እያለ የደረሰ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ የተከሰተ ፣ ዋናው የአደጋው መንስዔ መሆን አለመሆኑን፣ መንስዔው በዋናነት የሚቆጠር መንስዔ ነው ወይስ አስተዋፅኦ ያደረገ የሚለውንና የደረሰው መደርመስ ወይም መፈራረስ አሁን የተፈጠረና ቀድሞ ያልነበረ፣ በቀጥታ ወይም በተዘዋወሪ መሆን አለመሆኑንና ዋናው መንስዔ ከሕንፃው መደርመስ ወይም መፈራረስ ጋር ያልተያያዘ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡

ማንኛውም ክስ ወይም የክስ ሂደት በሚከሰትበት ጊዜ ለደረሰው ጉዳት መንስዔውን የማጣራቱ ኃላፊነት የሚሆነው የመድን ገቢው ነው፡፡

ማንኛውም መድን ገቢ የሚሰጠው ማስታወቂያም ይሁን ከድርጅቱ ጋር የሚደረግ ግንኙነት በፅሑፍ መሆን ይኖርበታል፡፡

ድርጅቱ በሚሟሉ ሁኔታዎች ምክንያትነት በዚህ የመድን ዋስትና የማይሸፈን የአደጋ ሥጋት መኖሩን ከአሳወቀ ጉዳቱ ሽፋን እንደሚኖረው የማጣራቱ ኃላፊነት የመድን ገቢው ነው፡፡

በዚህ ውል መሠረት የተሰጠው የመድን ዋስትና

ሀ.ንግዱ የሚቆም ወይም በዕዳ በያዙት አካላት የሚካሄድ ወይም በዘላቂነት ቋሚነት የሚቋረጥ ከሆነ ወይም
ለ.የዋስትና ገቢው በዋስትናው የመጠቀም መብት ከሞት በስተቀር በሌላ ምክንያት ከተቋረጠ ወይም
ሐ. ይህ የመድን ዋስትና በሥራ ላይ ከዋለ በኋላ የአደጋውን ሥጋት የሚያባብስ ማንኛውም ለውጥ በንግዱ ወይም ንግዱ በሚካሄድበት ቦታ ወይም ንብረት ላይ ከተደረገና በድርጅቱ ወይም ድርጅቱን በሚወክል አካል በሚፈረም ስምምነት እንዲቀጥል ካልተደረገ፣
ውሉ ይቋረጣል፡፡

መድን ገቢው የተደረጉ ለውጦችን ለድርጅቱ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ተጨማሪ አረቦን ይከፈላል፡፡ በመድን ገቢው ፍላጎት በግቢው ውስጥ በሚገኘው ንብረት ላይ ለሚደርሰው ጉዳት የሚከፈለው የአረቦን ተመንም ሊጨምር ይችላል፡፡

በመድን ገቢው ጥያቄ የመድን ዋስትናው በማንኛውም ጊዜ ሊቋረጥ ይችላል፡፡ በዚህን ጊዜ ድርጅቱ ውሉ ፀንቶ ለቆየበት ጊዜ ያህል በአጭር ጊዜ ስሌት (Short period rate) በማስላት ክፍያውን ያስቀራል፡፡ ድርጅቱም በማንኛወም ጊዜ ለመድን ገቢው በማስታወቅ ዋስትናውን ሊያቋርጥ ይችላል፡፡ ውሉ የሚቋረጠው በድርጅቱ ጥያቄ በሚሆንበት ጊዜ ድርጅቱ ውሉ ከተቋረጠበት ጊዜ አንስቶ እስከውሉ ማብቂያ ጊዜ ድረስ ያለውን አረቦን በማስላት ለመድን ገቢው ይመልሳል፡፡

በዚህ ውል መሠረት የካሣ ጥያቄ የሚያስቀርብ ማንኛውም ጉዳት በሚደርስበት ጊዜ መድን ገቢው ወዲያውኑ ለድርጅቱ ማሳወቅና የንግዱን ሁኔታ ሊያቋርጡ የሚችሉ ነገሮችን ለማረጋገጥ ወይም ለመቀነስ ወይም ጉዳቱን ለማስወገድ ወይም ለመቀነስ የሚያስችሉ ተገቢ እርምጃዎች እንዲወሰዱ መፍቀድና መተግበር ይኖርበታል፡፡

በዚህ ውል መሠረት የካሣ ጥያቄ ማቅረብ በሚያስፈልግበት ጊዜ ማካካሻ የሚሰጥበት ጊዜ ባበቃ በ3ዐ ቀን ጊዜ ውስጥ ወይም ድርጅቱ በፅሑፍ ፈቃድ በሰጠበት ጊዜ ውስጥ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ድርጅቱ ወይም ድርጅቱ የሚወክለው አካል የካሣ ጥያቄውን ለማጣራት ወይም ለማረጋገጥ የሚፈልጋቸውን የሂሣብ መዛግብትና ሌሎች የንግዱ ሥራ የሚመዘግባቸውን መዝገቦች፣ ቫውቸሮች፡ ኢንቮይሶች፣ ባላንስ ሽቶችና ሌሎች ዶክመንቶች፣ ማረጋገጫዎች፣ መረጃዎች፣ ማብራሪያዎችና ሌሎች ማስረጃዎችን በቃለ መሃላ አስደግፎ ወይም የካሣ ጥያቄውን ትክክለኛነት የሚያረጋግጥ ሕጋዊ ቅፅ ሞልቶና ማናቸውንም ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ተያያዥነት ያላቸውን ነገሮች አካቶ መድን ገቢው በራሱ ወጪ በማጓጓዝ ለድርጅቱ ያቀርባል፡፡ ይህ ሁኔታ ሳይሟላ በዚህ ውል የሚስተናገድ የካሣ ክፍያ ጥያቄ አይኖርም፡፡ ሁኔታዎቹ ሳይሟሉ የተፈፀመ የካሣ ክፍያ ቢኖር ወዲያውኑ ለድርጅቱ ተመላሽ ይሆናል፡፡

በዚህ ውል የሚገኙ ጥቅማ ጥቅሞችን ለማግኘት የቀረበው የካሣ ጥያቄ የተጭበረበረ ሀሰተኛ ሆኖ ከተገኘ ወይም የማታለያ ስልቶችን ወይም መንገዶችን መድን ገቢው ወይም የመድን ገቢው ወኪል የሆነ አካል ሲጠቀም ቢገኝ በውሉ የሚገኙትን ጥቅሞች በሙሉ እንዲያጣ ይደረጋል፡፡

በዚህ ውል መሠረት ዋስትና በተሰጠው ማንኛውም ንብረት ላይ ጥፋት ወይም ጉዳት በደረሰበት ወቅት ይህ ጥፋት ወይም ጉዳት በሌላ የመድን ድርጅት ወይም ድርጅቶች ተሸፍኖ ከተገኘ ድርጅቱ በስሌት ከሚደርስበት የመቶኛ ድርሻ በላይ የመክፈል ወይም የማዋጣት ኃላፊነት አይኖርበትም፡፡

ድርጅቱ ለመድን ገቢው ማካካሻ ከመክፈሉ በፊት ወይም ከከፈለ በኋላ የመዳረግ መብቱን ተጠቅሞ በራሱ ወጪ ማንኛውንም መብቱን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ�” አስፈላጊ ጉዳዮች ውል ገቢው መፈፀምና እንዲፈፀሙ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

5.5 ማካካሻ የሚሰጥበት ጊዜ

ማካካሻ የሚሰጥበት ጊዜ የሚባለው ኪሣራው በዋስትናው ሽፋን ካሣ የሚከፈልበት ሆኖ የሥራው እንቅስቃሴ ከተቋረጠበት ጊዜ አንስቶ መደበኛው የሥራ እንቅስቃሴ እስከሚቀጥልበት ጊዜ ያለው ነው፡፡

የማካካሻው የጊዜ ገደብ በመድን ገቢው ምርጫ የሚወሰን ሲሆን የውሉም የጊዜ ገደብ ይሆናል፡፡ የመድን ገቢው ሌላ ድርጅት የማቋቋም አቅም፣ ቀደም ሲል የነበሩ ሁኔታዎችን የሚያመቻችበት፣ ማሽኖችን የሚያስጠግንበት ወይም የሚተካበትና ሥራውን ወደነበረበት ሁኔታ የሚመልስበት ፍጥነት በጊዜ ገደብ ምርጫው ላይ ተፅዕኖ ይኖራቸዋል፡፡

5.6 የዋስትና መጠን

ለማንኛውም ከ12 ወራት በታች ለሆነ ጊዜ የሚሰጥ የዋስትና መጠን መሠረት የሚያደርገው በመድን ገቢው በራሱ ተሰልቶ የሚቀርበውን አጠቃላይ ዓመታዊ ትርፍ ነው፡፡ የማካካሻ ጊዜው ከ12 ወራት ከበለጠ የዋስትና መጠኑ ስሌት በዚያው መጠን የሚጨምር ይሆናል፡፡

5.7 የማካካሻ መመዘኛ

በውሉ የተሸፈነ የሥራ መስተጓጎል ሲከሰት ለመድን ገቢው የሚከፈለው ማካካሻ መጠን ስሌት በሚከተሉት ሁኔታዎች ይሆናል፡፡


ሀ.አደጋው ከመድረሱ በፊት የነበረው በጀት ዓመት አጠቃላይ የትርፍ መጠንን መነሻ በማድረግ የሚሰላ ይሆናል፡፡
ለ.ከላይ የተደረሰበት የአጠቃላይ ትርፍ ስሌት በአደጋው ምክንያት ለተፈጠረው የንግድ ልውውጥ መጠን እጥረት መተኪያ ይውላል፡፡ እጥረቱም ከአደጋው በኋላ ባሉት ወራት ያለውን የንግድ ልውውጥ መጠን ከአደጋው በፊት ካሉት ተመሳሳይ ወራት ጋር በማነፃፀር የሚገኝ ይሆናል፡፡
ሐ.ከላይ የተሰራው ስሌት በአጠቃላይ ትርፍ ላይ የደረሰውን ኪሣራ የሚሰጥ ሲሆን ስራ በሚሰራበት ጊዜ የወጣ ማናቸውንም ተጨማሪ ወጪ ያካትታል፡፡
መ.ከላይ የተጠቀሰው የአንድ ዓመት የአጠቃላይ ትርፍ መጠን ስሌት ሁሉንም ነገሮች እንደማይለወጡ በመገመት ነው፡፡ ይሁንና ባልተገመቱ ሁኔታዎች መፈጠር ወይም በተለዩ ክስተቶች ወይም በንግድ እንቅስቃሴው አካሄድ ምክንያት ቀደም ሲል የነበረው አሁን በተግባር ሊታይ አይችልም፡፡ ስለዚህ እነዚህን እውነታዎች ከግንዛቤ በማስገባት በስሌቱ ላይ አንዳንድ ማስተካከያዎች ሊደረጉ ይችላሉ፡፡
ሠ.በመጨረሻም ከአደጋው የተረፈ ወይም ዋስትና ሊገባለት ከሚገባው በታች በአነሰ ዋጋ ዋስትና የገባ ከሆነ ገንዘቡ በአማካይ ስሌት ይቀነሳል፡፡

5.8 ስለግልግል

1.የጉዳቱን መጠን በተመለከተ በመድን ሰጪውና በመድን ገቢው መካከል ልዩነት ከተፈጠረ ልዩነቱን የፈጠሩት ጥያቄዎች በሁለቱም ወገኖች በፅሑፍ ወደተመረጡ የግልግል ዳኞች ይተላለፋሉ፡፡ ሁለቱ ወገኖች በተመረጡት የግልግል ዳኞች መስማማት ካልቻሉ ተጨማሪ ዳኛ እንዲመርጡ በፅሑፍ ከተጠየቁበት ጊዜ ጀምሮ በሁለት ተከታታይ ወራት ጊዜ ውስጥ ተጨማሪ ዳኛ በፅሑፍ እንዲመርጡ ይደረጋል፡፡ አንደኛው ወገን ዳኛ እንዲመርጥ ጥያቄው ከቀረበለት በኋላ በሁለት ወር ውስጥ ለመምረጥ ባይፈልግ ወይም መምረጥ ባይችል አንደኛው ወገን ብቸኛ ዳኛ የመምረጥ ነፃነት ይኖረዋል፡፡ በግልግል ዳኞች መካከል የሃሣብ ልዩነት ቢፈጠርና ስምምነት ላይ ሳይደርሱ ቢቀር ጉዳዩ በሁለቱ ወገኖች ዳኞች በፅሑፍ ተመርጠው ስብሰባ ላይ በመገኘት የሁኔታውን አግባብነት ሲከታተሉ ለቆዩት ዳኞች ይቀርባል፡፡

ከሁለቱ ዳኝነት ከሚፈልጉት ወገኖች የአንደኛው በሞት መለየት የዳኛውን፣ የዳኞቹን ወይም የሕግ ተከታታዩን ሥልጣን ወይም ኃይል አይገድበውም፡፡ የዳኛ ወይም የሕግ ተከታታይ አካል በሞት መለየት በሚያጋጥምበት ጊዜ በምትኩ ሌላ ዳኛ ወይም የሕግ ተከታታይ በተከራካሪዎቹ አካላት ወይም በግልግል ዳኞች ይህ እንደሁኔታው የሚወሰን ነው ይመረጣል፡፡
የዳኝነትና የፍርድ ውሣኔው ወጪ በዳኛው፣ በዳኞቹ ወይም በሕግ ተከታታዩቹ በሚወሰነው መሠረት ይሆናል፡፡

2.ድርጅቱ በሚከተሉት ሁኔታዎች ለሚነሳ ማንኛውም የካሣ ክፍያ ጥያቄ በምንም መንገድ ኃላፊነት አይኖርበትም፡፡
ድርጅቱ በዚህ ውል መሠረት


ሀ.በዚህ ውል መሠረት ማካካሻ የሚሰጥበት ጊዜ ካበቃ ከአንድ ዓመት በኋላ
ለ. የካሣ ክፍያ ጥያቄው ሳይፈፀም የሚቆይበት ምክንያት ከሌለ ወይም ለግልግል ዳኞች የሚቀርብ ካልሆነ በስተቀር የካሣ ክፍያው ከተፈፀመ፣ ወይም መድን ሰጪው የካሣ ክፍያ ጥያቄ ያስነሳውን ጉዳት ለመሸፈን ኃላፊነቱን ከወሰደ ከሦስት ወር በኋላ'


ማሳሰቢያ፡- ይህ ፅሑፍ ስለየትርፍ እጦት የመድን ዋስትና የቀረበ ማብራሪያ እንጂ በሕግ ፊት የሚፀና ውል አይደለም፡፡

   

Home  About Us Financial Indicator Life Insurance Non-Life Insurance Main Branch Forms Contact Us